የዱባ ጥጋብ ሰ ሎ ሞ ን አ በ በ 6 7 የነጯ “ክር” ቀይ መሥመር ለዚህ ጽሑፍ ጥንስስ የኾነውን የመነሻ ሐሳብ በምጽፍ ጊዜ ምቾት የሚነሣ አሮጌ የካፌ አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጬ ነበር። የአካባቢው ግር ግርና ጫጫታ አይጣል ያሰኛል። ቀልብ ለመሰብሰብ አይመችም። ከወንበሩ መቈርቈር ብቻ ሳይኾን ሰላምና እርጋታ ከሚነሣው ውክቢያ በላይ ምቾት የነሣኝ ቍጭ ባልሁበት ያየሁት አሳዛኝ ድርጊት ነበር። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት፥ ምክንያቱን በማላውቀው አለመግባባት የተነሣ፥ ዕድሜው ከኹለት ደርዘን እንደማይበልጥ የገመትሁት “ጐበዝ” ክፉኛ ያበሻቀጣቸው አንድ ሽማግሌ ከካፌው በረንዳ ጥግ ቍጭ እንዳሉ በብርቱ ትካዜና መብሰልሰል ተውጠው አያለሁ። በዘመን ብዛት የተኰማተረ የፊት ገጽታቸው በጥልቅ ሐዘን እንደ ተከደነ ከፊታችን ተዘርግፏል። ታታሪ ገበሬ እንደ ሸነሸነው ለም መሬት በረድፍ የተደረደሩ መሥመሮች የወረሩት ግንባራቸው “ነጭ ላብ” አጢዞበታል። ከሲታ ናቸው። ማሠሪያው እንደ ላላ ጆንያ ያዘበዘበና የተጣጠፈ ቈዳቸው ክፉኛ ረግቧል። አካላዊ ጥንካሬያቸውንም ኾነ ሥጋዊ ወዘናቸውን ችግርና እርጅና በብርቱ ክንዱ እንደ ከሰከሰው ግልጥ ብሎ ይታያል። እርሳቸውን መመልከት ብቻውን “ሥጋ ባዳ” የመባሉን ምሥጢር በገቢር ይተርካል። (ውበትም ደም ግባትም እንደ ማለዳ ጤዛ አላፊና ረጋፊ ነው።) አለባበሳቸው “እንደ ነገሩ ኾነ” ከሚባል,ለው በላይ ተዝረክሯል። በሸሚዝ ምትክ የለበሱት የኮት ቅርፅ ያለው ነገር ሲኾን ከወዝ ዐደር የሥራ ልብስ ላይ የተነቀለ ሳይኾን አይቀርም። “ከሸሚዛቸው” በላይ ሹራብ ደርበዋል፤ የጐበጠ ትከሻቸው ላይ ያረፈው ክፍሉ ክፉኛ የነተበና ያረጀ ተካፋች ሹራብ። ምን ዐይነት ቀለም እንደ ነበረው ለማሰብ እንዳይቻል አሮጌነት እና እድፍ ከሹራብነት ተራ አውጥተውታል። ጭቅቅት የተደገደገበት ዳለቻ ሱሪ ታጥቀዋል። ጕልበቱ አካባቢ በእጅ የተጠቀመ እራፊ በሰፊው ተጥፎበታል። (ስንትና ስንት ሱሪዎች ለባሽ ዐጥተው በየቁም ሳጥኑ ታፍነው በሚኖሩበት ዓለም አንድ አረጋዊ ይኸን ለብሶ ይመላለሳል።) ለምቦጩን ከጣለው የእግር ሹራባቸው (ካልሲያቸው) እና በሱሪያቸው ጫፎች ከመሸፈን ያመለጡት የቅልጥሞቻቸው ክፍሎች በቆዳ የተሸፈኑ ድብልብል በድኾች የሚያፌዝ ፈጣሪያቸውን ይንቃል። (ምሳሌ 17፥5) *** በዚህ ዓለም ላይ ልጆች ባይኖሩ ኖሮ ዓለም ምን ያህል አሳዛኝና አስጨናቂ ቦታ ሊኾን እንደሚችልና አዛውንቶች ባይኖሩበት ደግሞ ምን ያህል ሰብአዊነቱን የተቀማ አስፈሪ ስፍራ ሊኾን እንደሚችል ዘወትር ዐስባለሁ። – ሳሙኤል ቴለር ኮሌሪጅ (እንግሊዛዊው ባለቅኔ) *** “በቀኑ መጨረሻ ዋጋ ኖሮት ከቍጥር የሚገባው በሕይወታችሁ የኖራችኋቸው ዓመታት ሳይኾኑ በዓመታቱ ኖራችሁት ያሳለፋችሁት ሕይወት ነው።” – አብርሃም ሊንከን የዱባ ጥጋብ ሰ ሎ ሞ ን አ በ በ 8 9 የሚበቃ ዘውዳቸው ኾኖላቸዋል። የምናከብራቸው ጕልበታቸውን ፈርተን ሳይኾን “አክሊላቸውን” አይተን ነው። ጠቢቡ በምሳሌው “የሽማግሌዎችም ጌጥ ሽበት ነው” ማለቱ ለዚህ ነው። መጽሐፈ ምሳሌ የጥበብ ጽሑፍ ሲኾን፥ ጠቅለል ባለ አነጋገር፥ ኹለት የተለያዩ የአኗኗር መንገዶችን መኖራቸውን ለማሳየት ተጽፏል። የጥበብን መንገድ ከስንፍና (ወይም ከሞኝነት) መንገድ ጋር ያነጻጽራል። በዚህ አጠቃላይ የሕይወት አተያይ መሠረት ሞኞች እግዚአብሔርን ከማወቅ ባፈነገጠው ሕይወታቸው መጥፎ ውሳኔዎችን ያደርጋሉ፤ ውሳኔያቸውም የሚያስከትላቸውን መዘዞች ለመቀበል ይገደዳሉ፤ በወጣትነት ይሞታሉ። አስተዋዮች እግዚአብሔርን በመፍራት በምትገኝ ጥበብ ጥሩ ውሳኔዎችን ያደርጋሉ፤ ውሳኔያቸው በሚያስከትላቸው መልካም ፍሬዎች ይደሰታሉ፤ በመኾኑም፥ እስከ ብስለት ዕድሜ ድረስ ሳይዋረዱ ይኖራሉ። 1 እንግዲህ፥ በዚህ ዐይነቱ የጥበብ ንጽረት ተመልክቶ ጠቢቡ ሽበትን የሽማግሌዎች ጌጥ ብሎ ጠርቶታል። በመኾኑም፥ ብሉይ ኪዳን በዕድሜ የገፉ ሰዎችን እንደ “ተራ አዛውንት” ወይም “ያረጀ የዕድሜ ባለ ጠጋ” ብቻ ሳይኾን፥ እንደ “ሽበት ባለ ጠጋ” ይቈጥራቸዋል። “ሽበታሙ ሰው” ወይም “ሽበታም” ብሎ ይጠራቸዋል (ዘሌ. 19፥32፤ ኢዮ. 15፥10)። ሽበት ከረጅም ዕድሜ ጋር የተቈራኘ ነው፤ ዕድሜም በፈንታው ከብስለት (ጥበብ) ጋር ተሳስሯልና “ሽበታም” ማለት የክብር ስም እንጂ ስድብ አይደለም። በዕድሜው ብዛት የሸመገለ ኹሉ አስተዋይ፥ በሳልና ክቡድ ባይኾንም፥ የሽበት የክብር አክሊልነቱ ግን አሌ ሊባል አይችልም። እንግዲያስ፥ የእኒያ አባት ሽበት በዚያ ወጣት ፊት እንዴት ሊቀልል ቻለ? ምርቃታቸውን ሊፈልግ ሲገባው በኀዘናቸው እንፋሎት መታፈንን እንደ ምን መረጠ? ሽበታቸው ስለ ረገፈ እንደ ምንም ታለፈ? በፊቱ ያስናቃቸው መጐሣቀላቸው ነው? አዳፋ መልበሳቸው ነው? ወይስ ዐቅም ማጣታቸው? ሺህ ጊዜ ዐቅም ቢያጡ፥ የቈሸሸ ቢለብሱና ጐሥቋላ አካላቸውን እየጐተቱ ቢታዩም፥ ሽምግልናቸው ለምን 1 የጥበብ ጽሑፎች የሚያነሧቸው ሐሳቦችና ጥበባዊ አባባሎች ጠቅለል ያሉ (general) አተያዮች ላይ የተመሠረቱ መርሖዎችና መመሪያዎች ናቸው እንጂ፥ ኹል ጊዜና በየትኛው ቦታ የማይለወጡ፥ ቋሚ እና ኵላዊ (universal) እውነታዎች አይደሉም። ዐጥንታቸውን አጋልጠዋል። የጫማቸውን ቅርጽና ዐይነት ለመናገር ያስቸግራል። ከመቈርፈዱ፥ ከመጣመሙና ከመጨማደዱ ብዛት ከወዳደቀ የቈርቈሮ ቍራጭ በብረት ዘነዘና እየተቀጠቀጠ የተሠራ ሰንዱቅ ይመስላል (እግሮቻቸው እዚህ ውስጥ እንዴት ይኾን የሚውሉ?)። በተጨማደዱ መዳፎቻቸው ላይ ያረፉት ጣቶቻቸው (ዐጥንታቸው ማለት ይቀላል) አንድ ውልግድግድ ከዘራ ለመጨበጥ ተቈላልፈዋል። እሳት እንደ ገባ ላስቲክ የተኰማተረች የራስ ቆባቸውን ጕልበታቸው ላይ ጥለው በክርናቸው ተጭነዋታል። ምናቸውን እንደያዙባት ባላውቅም አንዲት ከረጢት ከእግራቸው ሥር ተወሽቃለች። በእርሷ ላይ ደግሞ የታጠፈች ጃንጥላ። ራሰ በራ ናቸው፤ ሙሉ ራሰ በራ። በጭንቅላታቸው ላይ የተረፈ ምንም ጸጕር የለም። ኖረውም ከኾነ፥ ከጨረፍታ በላይ ላያቸው ስላልቻልሁ በእኔ ዐይን አልገቡልኝም ይኾናል። (እንኳን እኒህን መሳይ አዛውንት ይቅርና በማንኛውም ሰው ላይ አተኵሮ ለማፍጠጥ ጽናቱ የለኝም።) ለምን እንደ ኾነ ግን ባላውቅም በጨረፍታ ካየሁት ገጽታቸው በአእምሮዬ ተቀርጸው የቀሩት በባዶ አናታቸው ላይ የቀሩት በጣት የሚቈጠሩ ሽበቶች ናቸው። በተለይም (በተተከለችበት የራስ ሜዳ ላይ) ነፋስ ጎንበስ ቃና ያደርጋትና ያውለበልባት የነበረች አንዲት ዘለላ ረጅም ሽበታቸው ትኵረቴን ሰረቃው ቈየች። አንዲት ቅንጣት ሽበት ናት። እርጅናና ጕሥቍልና ሽበታቸውን ጭምር የነጠቃቸው መሰሎ ተሰማኝ። ኾኖም፥ ከሌሎች ጥቂት ቅንጣቶች ጋር፥ የሽበት ዘለላዋ ብቻዋንም እንኳ የራሷን ምስክርነት ከመስጠት አትቦዝንም። ቢያንስ ለእኔ መስክራለች፤ በለሆሳስ፤ ግን በጥልቀት። የክብር ጌጥ ሽበታቸው መጀመሪያ ያስታወሰኝ ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ነበር። “የጐበዛዝት ክብር ጕልበታቸው ናት፥ የሽማግሌዎችም ጌጥ ሽበት ነው” (ምሳ. 20፥29) የሚለው። አዛውንቶች የወጣትነት ክብር የነበረው ጕልበት ከድቷቸው ቢኼድም፥ ሽበት በተባለ ጌጥ ተሸልመዋል። ሽበታቸው አክሊላቸው ነው። አረጋውያንን መናቅ ጌጣቸውን ማጕድፍ ነው። ሽምግልናቸው ክብር ሊያጐናጽፋቸው የዱባ ጥጋብ ሰ ሎ ሞ ን አ በ በ 10 11 የሚከብዱ፥ ጥፋቶች እዚህም እዚያም ይታያሉ። በ2011 የተወሰኑ ጋጠ ወጥ ጐረምሶች ሽማግሌዎችን እያሯሯጡ ሲወግሩ የሚያሳይ አንድ የቪዲዮ ምስል በየማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀኑ ሲዘዋወር ከርሟል። ቪዲዮውን ለማየት ስለ ከበደኝ እንደምንም ታግሼ የፎቶግራፍ ምስሎቹን ብቻ ተመልክቻለሁ። ደብዳቢዎቹ ያንን መሳይ የዕብደት ሥራ ለማከናወን ያመካኙበትን ሰበብም ኾነ የጭካኔ ተግባሩ የተፈጸመበትን ቦታ አላውቅም። በርግጥ ማወቅም አልፈልግም። ነገር ግን፥ አንድ ማኅበረ ሰብ በግብረ ገባዊ ድኽነት ክፉኛ ተቀጥቅጦ በቍልቍለት መንገድ ሲንከወከው ለማመልከት እንደ ምሳሌ ሊወሰድ እንደሚበቃ ማስተባበል አይቻልም። አዛውንት እያሯሯጠ በቡጢ የሚነርት የጐረምሳ ሠራዊት አይተን አቤት አቤት ስንል ወጣቱ “መብቱን ለማስከበር የወሰደው እርምጃ” እንደ ኾነ ምስክርነት ሊሰጡ የሞከሩ ሰዎችንና አስተያየቶቻቸውን ተመልክተናል። “አገር ሲያረጅ ጃርት ይፈላበታል” ሲባል ተረት ብቻ ይመስለኝ ነበር። እንዲህ ዐይነቱን ድርጊት፥ አሰፋ እንደሻው፥ “የባህል መሸራረፍ እና የስብእና መሰባበር” ኹነኛ ማስረጃ አድርጎ እንዲህ አቅርቦታል፤ በመንገድ ላይ፥ በአደባባይ፥ በሕዝብ መገናኛዎች ውስጥና ሕዝብ በተሰ በሰበበት አካባቢ ኹሉ የሚተላለፈው ዘለፋና እዚህ ለመድገም የሚቀፍ አስቀያሚ የስድብ ዐይነት ብሎም ለሰዎችና ለኅብረተ ሰቡ የሚሠነር ንቀትና ያስተሳሰብ ትውከት ምን ልክ አለው? ምንስ አመልካች ነው? አጕራ ዘለል ወጣቶችና ለፍላፊዎች ሕዝቡን በየሰበቡ ሲያሸማቅቁት፥ በተለይ የፈረደባቸው እናቶች ላይ የሚወረወረው የብልግና ናዳ አየሩን ሲሞላው፥ ከሰው መኻል ብድግ ብሎ ይህን ማቆም የሚችል እየጠፋ ዘመኑን ብቻ በመርገም ማለፍ እንዴት ይቻላል? መፍትሔውስ ምንድር ነው? 2 ችግሩ ሰፋ ያለ ነው። ቀጥ ያለውን ለማስጐንበስ የመጣርን ነገር ኾነ ብለን ሳንያያዘው አልቀረንም። ግለ ሰብ ሽማግሌዎችን ብቻ ሳይኾን ቀድሞ የኖረ የትኛውንም ምሰሶ መገፍተር ወይም መነቅነቅ እንደ አዋጭ ምርጫ ተወስዷል። ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን “ጴጥሮስ ያችን ሰዓት”ን 3 የጻፈው በአንድ ከባድ 2 አሰፋ እንደሻው፥ ኢትዮጵያ ዛሬና ነገ፥ ቍጥር አራት (አዲስ አበባ፥ አልፋ ማተሚያ ቤት፥ 2009)፥ 51። 3 ጸጋዬ ገብረ መድኅን፥ “ጴጥሮስ ያችን ሰዓት”፥ እሳት ወይ አበባ (አዲስ አበባ፥ የጸገመ ቤተ ሰቦች፥ 1999 ዓ.ም.)፥ አልታፈረም? ትልቅነታቸው እንዴት ተደፈረ? ሽበታቸውስ? የክብር አክሊላቸውስ? ሞገሳቸው እንደ ምን ተረሳ? ማኅበራዊ ጕልላትነታቸው ስለ ምን እንደ አልባሌ ግትቻ ተቈጠረ? አጠገባቸው በነበርሁበትም ይኹን በኋላ ያቺ የሽበት “ዛላ” ሰው ብትኾን ስንቱን ትንግርት በመሰከረች እያልሁ ማሰቤ አልቀረም። እንደ ሞኝ ኹኜ የሰው ሽበት ዐስባለሁ። እገረምባታለሁ። እርሷ በቆመችበት የራስ ቅል ላይ ምን ምን ማዕረግ ኖሮ ያውቅ እንደኾን እጠይቃለሁ። ያ ራስ ብዙ ባርኔጣ ተፈራርቆበት ይኾናል። ስንት ኮፍያዎች ዐርፈውበት እንደ ነበር መገመት ይቻላል? ወታደራዊ መለዮ ደፍቶ ያውቃል? ከከፍተኛ ትምህርት ያገኘው የመመረቂያ ቆብ ኖሮት ያውቃል? ባለ ማዕረግ ቆብ ይኾን? ይህ ራስ ምን ሲንተራስ ኖረ? እንደ ያዕቆብ ድንጋይ ተንተርሶ ይኾናል። ወይም የሣር ጕዝጓዝ። ምናልባትም በላባ ትራስ ላይ ዐድሮ ያውቅ ይኾናል። ... ይህ ራስ አእምሮ በተባለው ዕልፍኙ ውስጥ ስንት ትዝታ አሽጓል። የእኒያ አባት ጥረትና ትጋት እንዴት ያለ ነበር? የቱ ጋ ተደናቅፈው ይኾን? መቼም የራሳቸውን ከፍታና ዝቅታ አያጡም። የግላቸው የፍቅርና የኀዘን ታሪክ ይኖራቸዋል። ከዚህ አእምሮ ኅብረተ ሰቡ ምን ሲጠቀም ኖረ? በበተነው ልክ ሰብስቧል? የደበቀው ሐቅ አለው? የሚሸሸው ታሪክስ? ስንት አሳፋሪ ድርጊት መዝግቦ ይኾን? የተሸከመው ትዝታ ቀና ብሎ በድፍረት እንዲኖር የሚያስችል ነው ወይስ በፍትሕ ብርሃን ፊት ዐንገት የሚዘልስ? አላውቅም። የኾነ ኾኖ እኒያ አባት የደረሰባቸው ግልምጫና ንቀት ከባድ የኅሊና ሸክም ዘርግፎብኝ ኼዷል። ... ሽበት የመዳፈር መደዴነት ላለፍንባቸውና እያለፍንበቸው ለሚገኙ መከራዎቻችን ኹሉ ብቸኛ መነሻ ባይኾንም፥ በማኅበራዊ ትስስራችን፥ ሥልጣኔያችንና ዐብሮነታችን ላይ ፈጥጦ ለተጐለተ ቍስላችን አንዱ መንሥኤ ቀዳሚ ባለውለታዎችን መናቅ መኾኑን በይፋ ማጋለጥ ለኅሊናችን የቀረበ ጥያቄ ነው። ሽማግሌን ማቃለል፥ ታላቆችን ማዋረድና ፊተኛ ጕልሐንን በግፍ ማጕላላት በጋራ ሥርዐታችን ላይ የተቃጣ በደል መኾኑ ችላ የተባለ ይመስላል። ስለዚህ አረጋውያንን በማዋረድ ረገድ ለመስማትና ለማየት የዱባ ጥጋብ ሰ ሎ ሞ ን አ በ በ 12 13 አወዳደቅ በሐቅም ኾነ በክፋት ያልተባለ የለም። 5 በታሪክ የሚጻፈውና የሚነገረው አወዛጋቢ ዝክንትል እንደ ተጠበቀ ኾኖ፥ “ልጅነት የተጫነው እና ብስለት የጐደለው” ቀዳሚዎቻቸውን የመፈታተን አድራጎታቸው ለውድቀታቸው እንደ ሰበብ ሳያገለግል እንዳልቀረ ሲጠቀስ አንብበናል። ይህ ስሕተት በዘመን ተጋሪ የዐይን እማኞችና በታሪክ ተመራማሪዎች የተመሰከረ ኾኖ አግኝቸዋለሁ። ነቃፊዎቻቸው ብቻ ሳይኾኑ ለእርሳቸው ቀና አመለካከት የነበራቸው አስተያየት ሰጭዎች ጭምር ይኸን የልዑሉን ድካም ሳይጠቅሱት አላለፉም። ድካማቸው ምን ነበር? ቀዳሚዎቻቸውን ከልክ ባለፈ ንቀት መገዳደር፤ የዕድሜ ታላላቆቻቸውን በግዴለሽነት መዳፈር። ለምሳሌ ከፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ገጠመኝና ትዝብት ያገኘሁትን ላስቀድም። ልጅ ኢያሱ ለክብራቸው በማይመጥን አኳኋን እዚህም እዚያ ሲሉ፥ ከዕድሜ አቻዎቻቸው ጋር ሲጫወቱና መሥመር የሳተ ነገር ሲከውኑ ይውሉ እንደ ነበር የሚተርኩት ተክለ ሐዋርያት፥ ከጠቀሷቸው ነገሮች መካከል አንዱ በራሳቸው ቤት የተከሠተ ነበር። ልጅ ኢያሱ ከተሰማ እሸቴ (ነጋድራስ) ጋር ኾነው በውድቅት ሌሊት ተክለ ሐዋርያት ቤት በድንገት ይመጣሉ። ተክለ ሐዋርያት በኹኔታው ተከፉ። ልዑሉ ለክብራቸው የማይመጥን ይህን ዐይነቱን ልማድ ማድረግ እንደሌለባቸው ለማስረዳት ቢሞክሩም ኢያሱ ከቁብ አልቈጠሩትም። ከነጋድራስ ጋር እየተንሾካሾኩ በቤቱ ያለውን ዕቃ እያገላበጡ ይመለከታሉ። ቀጥለው፥ በጠረጴዛዎቻቸው ላይ የተደረደሩትን የፎቶ አልበሞች ምንጥር አድርገው ካዩ በኋላ ስለ ፎቶዎቹ ትንታኔ እንዲቀርብላቸው ፈለጉ። በነገሩ ያዘኑትና የተከዙት ተክለ ሐዋርያት እየኾነ ያለው ነገር ኹሉ ልክ አለመኾኑንና የፎቶዎቹ መግለጫ ካስፈለገ እንደማንኛውም ሌላ ጊዜ በቀን ሲገናኙ ሊያስረዱ እንደሚችሉ ገለጹ። ከዚህ ቀጥሎስ ኢያሱ ምን አደረጉ? ጠረጴዛ ላይ የነበረውን መድ አንሥተው ቀለሙን በተክለ ሐዋርያት አናት ላይ አፈሰሱት። ልብሳቸው ኹሉ ተበከለ። መዱን ከጠረጴዛው ቢመልሱት ተደፋ። የተረፈውም ቀለም ፈስሶ ከወለሉ ተንጣለለ። 5 አቤቶ ኢያሱ የዳግማዊ ምኒልክ ሕጋዊ ዙፋን ወራሽ ኾነው ሳለ፥ ሥልጣናቸው በ6 ዓመት ብቻ ተገድቦ የቀረበትና ልዑሉ ለአሳዛኝ ውድቀት የተዳረጉበት ሰበባ ሰበብ ብዙ፥ ውስብስብና የበርካታ ኀይሎች ተሳትፎ የነበረበት ነው። እኔ የተነሣሁበት ዓላማ ያ ባለመኾኑ አልገባበትም። የኅሊና ፈተና በጽኑ ተፈትሮ በተያዘበት ቍጭት ተቀስቅሶ ነበር። ይኸውም፥ በአንድ ምሽት ጸጋዬ ወደ ቤቱ ሲያቀና ሳለ አንድ ጥንብዝ ብሎ የሰከረ ጀብራሬ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ምዕራብ አቅጣጫ በቆመው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሥር በግዴለሽነት ሲሸ* ያየዋል፤ ይሳደብም ነበር። ከነውረኝነት በላይ ያገጠጠ ዕብደት ሲፈጸም ያየው ጸጋዬ ልቡ በሐዘንና ንዴት እንደ ጋየ ከቤቱ ደርሶ የቅኔውን ሰይፍ መዘዘ። ነባርና ዘመን ጠገብ ማኅበራዊ ውርሶችንና ዕሴቶችን መናድ አዲስ ግኝት እንደ መፈልሰፍ ተወሰደ። ውጤቱ ግን “ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ” ከመኾን አላለፈም። ከቀደምት ዘመናት ገጾች ላይ አቧራውን ማራገፍ ተገቢ ቢኾንም፥ “ከታሪኩ በጎ በጎ የኾኑትን መልካም ነገሮች ሳይወስድና የታሪክ ስሕተቶቹን መርምሮ ሳይማርባቸው የገዛ አባቶቹን ታሪካዊ ልምድ በጅምላ አፈር አስግጦ የሚያድግም ኾነ ያደገ አገር የለም።” 4 ትናንትን በመርገም የነገ ሥንቅ አይዘጋጅም። ጽኑ መሠረት የሌለው ቤት ጸንቶ አይቆምም። ባለውለታዎችን ለማክሰምና ልፋታቸውን ለማጥፋት መጣር የራስን ሥረ መሠረት መንቀል ነው፤ ወደ ራስ እግር እንደ መተኰስ ያለ ድንግርግር አለበት። ትናንትን የዛሬ መሠረት እንጂ ባሪያ ማድረግ አይቻልም። ያለፈውን አስተዋጽኦ ክዶ ወደ ፊት ለመራመድ መሞከር በራስ ከመቀለድ አይለይም። ምንም ዐይነት ዕድል፥ አጋጣሚ፥ ጕልበትና ሥልጣን ብናገኝ ቀዳሚዎቻችንን ከማክበር መጕደል የለብንም። ውጤቱ ራሳችንን የሚጐዳ ይኾናልና። የከረሙ ማሳያዎች ሐሳባችንን ለማጐላመስ ከታሪክ ስንክሳራችን ውስጥ አንድ ሌላ ጐምቱ ሰው እንመዥርጥና እንያቸው፤ አቤቶ ኢያሱ። ከኢትዮጵያ ቀደምት ታዋቂ መሪዎች መካከል ስለ ልጅ ኢያሱ አነሣሥና 4 ተፈሪ ዓለሙ፥ በጸጋዬ ገብረ መድኅን፥ ታሪካዊ ተውኔቶች (አዲስ አበባ፦አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ፥ 2003 ዓ.ም)፥ መግቢያ 2፥ xxi ላይ እንደ ጻፈው። የዱባ ጥጋብ ሰ ሎ ሞ ን አ በ በ 14 15 እየኼዱ 9 እንዲያጅቧቸው እስከ ማድረግ ድረስ ተጭነዋቸው ነበር። 10 “ከዚህም ዐልፎ፥” ይላሉ የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ፥ “ኢያሱ የምኒልክን መኳንንት ‘የአባቴ ሙክቶች’ ብለው እስከ መጥራትና አንዳንዴም ሚስቶቻቸውን እስከ ማማገጥ ደርሰው ነበር።” 11 አምባሳደር ዘውዴ ረታ እንደሚተቹት፥ ይህን ዐይነቱ “የማን አለብኝ ዕብሪት” 12 መንፈስ የኢያሱን መጨረሻ አከፋው። “በዕድሜያቸውም ኾነ በአእምሯቸው ያልበሰሉት መስፍን ብቻቸውን በሥልጣን ባሕር ውስጥ እንዲዋኙ” 13 ከመተዋቸው የተነሣ፥ መጨረሻው ሳያምር ቀረ። “በዐሥራ አራት ዓመት ዕድሜው እንደ ልጅ ኢያሱ የአንድ ሰፊ ባህልና ታሪክ ያለው አገር መሪ ኾኖ፥ በሙሉ ሥልጣን ... ብቻውን የጋለበ የለም።” 14 ይህን እዚህ ላይ ቋጭተን፥ ዘመናዊ ትምህርት ቀሰምሁ ያለው ፈር ቀዳጅ ትውልድ ከኖረበት ሌላ የታሪክ ዘመን (1960ዎቹ) እንሻገርና እንጨልፍ። አቢዮት ያቀጣጠለ ትውልድ ዘመን ነበር። ንጉሣዊ ሥርዐትን ላይደገም(?) ሽሯል። ከዘመን ተጋሪ ወታደሮች ጋር መሳ ለመሳ የዘውዳዊውን ሥርዐት ቢታገልም በወታደሮቹ ተገለለ። የጦር ኀይሉ ከአገር ጠባቂነት ተነሥቶ አገር አስተዳዳሪ ኾነ (ወይም ተደረገ?)። አቢዮቱን ከወጣቱ ቀማ ተብሎ በተማሪዎቹ የሚከሰሰው ወታደራዊ ደርግ የመጨረሻውን ንጉሥ በአሮጌ ቮልስ ዋገን ጭኖ ከቤተ መንግሥት እያዋከበ ካወጣ በኋላ ወደ 4ኛ ክፍለ ጦር መምሪያ አጋዘ። 15 9 ከፈረሳቸው ወርደው ወይም በፈረሳቸው ጀርባ ሳይጫኑ ማለት ነው። 10 Richard Pankhurst, “The Reign of Lij Iyasu-as Avedes Terzian Saw It”, in Elois Fiquet and Wolbert Smidt, eds., 93. 11 ባሕሩ ዘውዴ፥ ሀብቴ አባ መላ፦ ከጦር ምርኮኛነት እስከ አገር መሪነት (አዲስ አበባ፦ አልቦ አሳታሚ፥ 2008 ዓ.ም.)፥ 185። 12 ዘውዴ ረታ፥ ተፈሪ መኰንን፦ ረጅሙ የስልጣን ጕዞ (ዐዲስ አበባ፦ ሻማ ቡክስ፥ 2006 ዓ.ም.)፥ 288 13 ዘውዴ፥ ተፈሪ፥ 288 14 ዘውዴ፥ ተፈሪ፥ 280. 15 ንጉሡ ከሥልጣን መውረዳቸውን ለመንገር ወደ ኢዩቤልዩ (በኋላ ብሔራዊ) ቤተ መንግሥት የመጡት የደርግ ልዑካን ዓላማቸው ምን እንደኾነ በንጉሡ ሲጠየቁ የመለሱት “ከፍ ያለውን ዝቅ፥ ዝቅ ያለውን ከፍ ማድረግ” መኾኑን ፈክረዋል። ይኸን ገደብ የለሽ ንቀትና ተንጠራርቶ የማዋረድ ተግባር የታዘቡት ተክለ ሐዋርያት ኢያሱን ለመግራት የሞከሩትን ነገር ኹሉ ከዘረዘሩ በኋላ ሳይሳካ መቅረቱን ያወሳሉ። የመጨረሻ ትዝብታቸውም፥ ኢያሱ ኹልጊዜ “እንደ ማሙዬ [ሕፃን] ኾኖ መኖር የሚቻል መስሏቸው የማይመከሩ በመኾናቸው ዕድላቸውን አበላሽተው፥ በመጨረሻ ፍዳቸውን ተቀበሉ” 6 የሚል ኾነ። ሌላ ተጨማሪ አስረጂ እንመልከት። የኾነ ቀን ልጅ ኢያሱ ለሥራ ወደ ደሴ ለመኼድ ጕዞ መጀራቸውን የሰሙ የዐፄ ምኒልክ መኳንንት ጌታችን ኢያሱን አጅበን እንኼዳለን በማለት ገሥግሠው ይመጣሉ። እንደ ደረሱ ኢያሱ፥ “እኔ ጐልማሶች አስከትዬ ... በተነሣሁ ጊዜ ያለ ፈቃዴ መከተል የለባችሁም። እናንተ እንግዲህ ከእኛ ጋር ለመሮጥ አትችሉም። ወፍራችኋል፤ ሸምግላችኋል። ... ሸሽታችሁ አታመልጡም። አባርራችሁ አትጨብጡም ...” 7 ብለዋቸው ዐረፉት። እነዚያ ኹሉ “ለመሬት የከበዱ” መኳንንት ምን ቋጥረው እንደ ተመለሱ አላውቅም። በሌላ ጊዜ፥ ነገሮች ከቍጥጥር ውጪ እየወጡ በነበረበት የሥልጣናቸው የመጨረሻ ወራት ሐረር ላይ ነበሩ። የሸዋ መኳንንት እርሳቸውን ከምኒልክ ዙፋን ለማንሣት እየመከሩ እንደ ነበር ይነገራቸዋል። በዚያን ጊዜ ልጅ ኢያሱ የሰጡትን ምላሽ የዘመን ተጋሪያቸው መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ በትዝታቸው አስፍረዋል። ኢያሱ ምን አሉ? “የሸዋን መኳንንት አንጋልዬ በአፉ ላይ ብሸናበት እንኳ የሚናገረኝ የለም።” 8 የሸዋ መኳንንት ምላሽ ምን እንደ ነበረ ለታሪክ እንተወው። በልጅ ኢያሱ ዘመን የኖሩትን አርመናዊው የአቬዳስ ተርዚያን ምስክርነት መሠረት አድርገው ሪቻርድ ፓንክረስት እንደ ጻፉት ከኾነ፥ ልጅ ኢያሱ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስን “ልክ ለማስገባት” ያሰቡ በሚመስል አኳኋን አባ መላ በእግራቸው 6 ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም፥ ኦቶ ባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ) (አዲስ አበባ፦ አአዩፕ፥ 2004 ዓ.ም.)፥ 249፥ 252። 7 መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፥ የሐያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ፦ የዘመን ታሪክ ትዝታዬ ካየሁትና ከሰማሁት፥ 1896-1922 (አዲስ አበባ፥ አአዩፕ፥ 2002 ዓ.ም)፥ 93። 8 መርስዔ ኀዘን፥ የሐያኛው ክፍለ ዘመን፥ 136። የዱባ ጥጋብ ሰ ሎ ሞ ን አ በ በ 16 17 ራቅ ወዳለው የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ልውሰዳችሁና በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ ከወረደው መዓት መካከል አንድ ጕድ ላስታውሳችሁ። ዕድሜያቸው ከገፋ በኋላ አባ እስጢፋኖስን የተከተሉ አባ በርተሎሜዎስ የተባሉ አባት ነበሩ፤ በጽኑ ገድልና ተአምር የኖሩ። ለንጉሡ ስገዱ በሚል በተነሣባቸው መንግሥታዊና ቤተ ክህነታዊ ጣምራ ስደትና ጫና ቁም ስቅላቸውን ካዩ የደቂቀ እስጢፋኖስ ወገኖች አንዱ ነበሩ። ንጉሡ ቀልቡ በተቈጣና በነሸጠው ቍጥር ልዩ ልዩ ግርግሮችን እያስነሣ ግፍና በደል ሲፈጽምባቸው መክረሙን የደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ገድላት መስክረዋል። ገድላቱ የንጉሡንና የግብረ በላዎቹን የግፍ አድራጎት ካነጸሩባቸው ግብረ ገባዊና ምግባራዊ መለኪያዎች አንዱ (ዝቅ ብዬ ከምጠቅሰው እንደሚታይ) ሽበታሙን የማክበር ማኅበራዊና ኅሊናዊ ሚዛን ኾኖ እናገኘዋለን። ገድላቱ እንደሚመሰክሩት፥ እስጢፋኖሳውያን ግፍ፥ እስራት፥ እንግልት፥ ድብደባ፥ ግድያና በዘመኑ ማሰብ የተቻለው የጭካኔና የሥቃይ አደራረጎች ኹሉ ተፈጽመውባቸዋል። ከእነዚህ የጭካኔ ተግባራት መተግበሪያ ቀናት በአንዳኘው በነዲድ እሳት ጣዕራቸውን የማብላት ሥቅይት ተደገሰላቸው። ጣዕር ሥቃያቸው እንዲበዛ ከእሳቱ ያቀርቡና ይለበልቧቸዋል፤ ወደ እሳቱ ግን ጨርሰው አይጨምሯቸውም። ሙሉ ለሙሉ ለመግባትና ከዚህ ዓለም ለማረፍ ሲፈልጉ በዐንገታቸው ባስገቡባቸው ማነቆ ይጐትቱና ወደ ዳር ይስቧቸዋል። በእንደዚህ ያለ አድራጎት ብዙ አሠቃዩአቸው። ... አባ በርቶሎሚዎስን ብዙ አሠቃዩት። ከፍም ላይ ወረወሩት። የራሱ ጠጉር ነደደ። ሥጋው ተቃጠለ። ጭንቅላቱ አዠ። ሽምግልናው አላስፈራቸውም፤ ግርማው አላስደነገጣቸውም። ሽበቱ፥ የዐይኖቹ ከባድነት፥ ቃለ መለኮት የሚናገሩ ደስተኛ ከንፈሮቹ፥ የአፉ ቃል እንቅስቃሴ፥ የእጆቹ ቅድስት በረከት አላሳዘኗቸውም። እሱ ግን በራስ ሺበት ጊዜ የጐልማሳነት ጸጋ አግኝቶ ይኸንን ኹሉ ታገሠ። 17 በዚህ የግፍ አድራጎት ውስጥ የገድሎ ዋነኛ ወቀሳ እንዲህ የሚለው ነው፤ የሽምግልና ሞገስ አልተፈራም፤ የአረጋዊ ግርማ አልታፈረም፤ ሽበትም 17 ጌታቸው ኀይሌ (ተርጓሚ)፥ ደቂቀ እስጢፋኖስ፦ በሕግ አምላክ፥ 2ኛ ዕትም (አዲስ አበባ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ፥ 2002)፥ 141፤ በተጨማሪ ገጽ 123 ይመ.። የቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ወታደሮች ሥዒረ-መንግሥት አካኺደው በግፍ ያገቷቸውን ንጉሥ ከሥልጣን መፈንገሉ አልበቃቸውም። ለጭካኔያቸው “አብዮታዊ ርምጃ” የተባለ የቍልምጫ ስም አውጥተው ሽምግልናቸውን የረባ ቦታ ሳይሰጡት፥ በትራስ አፍነው በግፍ ጭጭ አደረጓቸው። በኋላ እንደ ተጋለጠው፥ ለመቀበሪያቸው የሚኾን ስድስት ክንድ መሬት ነፍገው አስከሬናቸውን ከመጸዳጃ ቤት ሥር ወረወሩ። 16 በዚህ ሳያበቁ፥ አብዮቱን ያዋለዱበት ዕልፍኝ በአደስና በጥንጁት ሳይኾን በእጅ ብልጫ በተሰጠ የፍጅት ውሳኔ ባፈሰሱት ወደ ስድሳ የሚኾኑ መኳንንት የደም ትንፋጎት ተቈራሰመ። ይህን በመሳሰሉ ዕጥፍ ድርብ ግፎች ላይ የተመሠረተ አገዛዝ እንዴት ብሎ ሊጸና ይችላል? ያው የወታደሮቹም መንግሥት የኾነውን ኾኖ ከታሪክ መዝገብ ተሻጠ። የ1960ዎቹ ወጣቶች ትግል መንጠሪያው የአገርና የወገን ፍቅር እንደ ኾነ በሚገባ አምናለሁ። መቼም ያ ኹሉ ወጣት ለውድ ሕይወቱ ሳይሳሳ እስከ ሞት ድረስ የተዋደቀው ከምኒልክ ቤተ መንግሥት ገብቶ ዙፋን ሊቈጣጠር አይደለም። ነገር ግን፥ በጥድፊያና እንደ ዘበት በቃረመው ኮምኒስታዊ የንድፈ ሐሳብና ርእዮተ ዓለማዊ ግሳንግስ ነባሩን ምግባራዊና ግብረ ገባዊ አዕማድ በዘፈቀደ ደርምሶ እርስ በርሱ ተፋጠጠ። በጕርምስና፥ በትቢትና በስሜት የገነፈሉ ወጣቶች፥ እንዲሁም ንጉሡን ከነሽማግሌዎቹ ከሥልጠን ያወረዱ ወታደሮች አገሪቱን ጭምር ፈንችረው አልወረወሯትም ለማለት እንዴት ይቻላል? ይኸው መቅኖ እንዳጣች ግማሽ ምእት ዓመት ዐልፏል። አዛውንትን ማሽቀንጠር ባህል ወደ መኾን ተሸጋግሮ ነበርና የእነርሱ አረጋዊነት ሲደርስ ውርወራው በራሳቸውም ላይ ተራ በተራ ተፈጸመ። 16 የንጉሡን አሟሟትም ኾነ የተቀበሩበትን ቦታና ኹኔታ አስመልክቶ በአብዛኛው ሰው ለመታመን የበቃውን ታሪክ አስመልክቶ ልዩ አቃቤ ሕግ በመሠረተው ክስ ፍርድ የተሰጠበት ሲኾን፥ ከወታደራዊው መንግሥት መውደቅ በኋላ ኮሎኔል መንግሥቱን ጨምሮ በሕይወት የነበረ አንድም የደርግ አባል ሲያምን አልተገኘም። ንጉሡ በብዙ ኩኔታ “ዐመድ አፋሽ” ናቸው፡ ፡ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሠረት ቀኀስ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ተብሎ ተብሎ ያለቀለት ወሬ ነው። ነገር ግን፥ ድርጅቱ 25ኛው ዓመት የብር ኢዩቤልዩ በዓሉን ሲያከበር (ዐመድ አፋሽነት የሚከታተላቸው ሾተላይ ነው መሰል) ስማቸውን እንኳ ሳይጠቅስ ዐለፈው። እንደ ገናም፥ ድርጅቱ ወደ አፍሪካ ኅብረትነት ራሱን ቀይሮ ዋና ጽሐፈት ቤቱን በቻይና እርዳታ አስገንብቶ አስመርቋል። በዚያ ወቅት በቅጥር ግቢው የመሥራች አባቶቹን የመታሰቢያ ሐውልት ለማቆም ፍላጎቱን ባሳየ ጊዜ ንጉሡ በድጋሚ “ዐመድ እንዲያፍሱ” የአገራችን መሪዎች በቸልተኝነት ገሸሽ አደረጓቸው። የዱባ ጥጋብ ሰ ሎ ሞ ን አ በ በ 18 19 እርጅና በሕይወት መሥመር ላይ አይቀሬው ጫፍ ነው። ልናስቀረው አንችልም። በርግጥ እርጅናን ለመዋጋት ያልተደረገ ጥረት የለም። ፈጽሞ ማስወገድ ግን አልተቻለም። እንዲያውም መድኀኒት እንደሌለው በሽታ ሲቈጠር ኹሉ ይታያል። በተለይ በአንዳንድ አገራትና ባህሎች፥ እርጅና የተጫናቸውን ሰዎች ከማኅበረ ሰቡ በመነጠልና በማግለል በጠብቆ ማቈያ ማኖር እየተለመደ መጥቷል። አንዳንዶች እንዲያውም እንደማይጠቅሙ የቤተ ሰብና የማኅበረ ሰብ ሸክሞች ይቈጥሯቸዋል። አኹን አኹን እየቀረ እንጂ፥ ጠና ደዎ እንደ ጻፉትማ፥ “ያረጁና የታመሙ ሰዎችን መግደል የጤነኞችንና የወጣቶችን ሸክም ይቀንሳል የሚል እምነት የነበራቸው ማኅበረ ሰቦች እንደ ነበሩ ታሪክ ይመሰክራል።” 19 በልደት በበዓላትና ሌሎች ማኅበራዊ መሰባሰቦች ካልኾነ በቀር ደብዛቸውን የሚያጠፉባቸው ኹኔታዎችም ይታያሉ። አረጋዊነትን በሚመለከት ይህ መጥፎው አተያይ ነው። ሌላኛው አተያይ ደግሞ አረጋዊነትን ከነውበቱ የሚመለከት ነው። እርጅና አክብሮትና ሞገስ ይሰጠዋል። በዚህኛው አተያይ አዛውንቶች የጫካው ውስጥ ግዙፋን ዛፎች፥ የአገር ዋርካዎችና የኀብረ ተሰቡ አክሊሎች ናቸው። እዚህ ጎራ ውስጥ አረጋውያን የሕይወት ልምድና ተሞክሯቸው የዳበረ መኾኑ አይዘነጋም። የካበተ ልምድ ባለቤቶች፥ በጥበብ የበለጸጉ መዝገቦችና የካበተ ልምድ ባለቤቶች አድርጎ ይቈጥራቸዋል። መጽሐፍ ቅዱሳዊው ንጽረት ይኸኛውን አመለካከት ይፈጥራል፥ ያበረታታልም። በኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ የምናገኘው አስተዋዩ ወጣት ኤሊሁ ጥበብን ተሞልቶ ለኢዮብ ቃል ሊናገር በፈለገ ጊዜ አልተንቀዠቀዠም ነበር። ተሽቀዳድሞ ለመናገር ያልቻለው በኢዮብ ዙሪያ ሦስት ሽማግሌዎች በመኖራቸው ነበር። ሰዎቹ የሚናገሩት ከንቱነት በግልጽ ታይቶታል። በንግግራቸው ጥበብንና ማስተዋልን ባይመለከትም ግን በሽምግልናቸው ምክንያት ክብር በመስጠቱ ተናግረው እስኪጨርሱ ታግሦ ጠበቃቸው (ኢዮ. 32፥4፡6 ይመ.)። አልተጋፋም። ሲያንጓጥጣቸውና ሲያዋርዳቸው አናይም። በርግጥ ከንግግራቸው የራቀውን እውነትና ጥበብ በማስተዋል አቅርቦ ገሥጿቸዋል። 19 ጠና፥ አልተከበረም። ሰቆቃወ ኤርምያስ የይሁዳ ቤት በባቢሎናውያን የደረሰበትን የዘመነ ምርኮ ግፍ በሙሾ የሚያትት መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ከዘረዘራቸው የባቢሎን የጭካኔ እርምጃዎች መካከል በእግዚአብሔር ሕዝብ አዛውንቶች ላይ የተፈጸመውን ግፍ ያወሳል። “የሽማግሌዎች ፊት አልታፈረም” (ሰቆ. 5፥12) በማለት። አሕዛብ ኢየሩሳሌምን ባወደሙ ጊዜ፥ የተቀደሰ መቅደሷን ባረከሱ ወራት፥ ጐበዛዝቷን በፈጁበት ቀን፥ አለቆቿ ሲሰቀሉ የአረጋውያኑ ሽበት ተነጨ፤ ጺማቸው ተጐተተ። ጨርሶ አልታፈሩም፤ አልተከበሩም። አረጋዊነት ይከበር የትውልዶች ትስስር፥ የቤተ ሰብ ታሪካዊ ግንኙነት፥ የትውልድ ሐረግ ሰንሰለትና የእርስ በርስ የፍቅር መጋራት ለሕይወት ትርጕም ይሰጠዋል። አዛውንቱ አያት ከገዛ ልጁ ጋር እኩል ለመሯሯጥ የሚችልበትን ዐቅም በዕድሜ ጕልበት ስለ ተነጠቀ አይሞክረውም። ነገር ግን ከልጅ ልጁ ጋር ዳዴ ለማለት ሳያቅማማ ወደ ታች ተመልሷል። የሰው ልጅ የመጀመሪያና የመጨረሻው የሕይወቱ አንጓዎች ላይ ተመሳሳይ ነገር ሊፈጽም ይችላል። በኹለቱም ላይ እያለ የሌሎችን ድጋፍ በሚፈልግበት ጊዜ አክብሮትና እንክብካቤ ሊነፈገው አይገባም። እንደየሕዝቡ ባህል ልዩነት ቢኖረውም፥ “ለአዛውንቶች ... የሚደረግ ግብረ ገባዊ አያያዝ አለ። ... በአገራችን ያረጁና የታመሙ ሰዎችን መርደት ወይም መንከባከብ መልካም ተግባር ነው። ይህ እምነት ዛሬም ጠንካራ ነው።” 18 ጠንካራ እንደ ኾነ መቀጠልም አለበት። አረጋዊነትን በሚመለከት ግልጽ ማኅበራዊና ምግባራዊ ዐቋም ሊኖረን ግድ ይለናል። መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ከሰጣቸው ትእዛዛት መካከል አረጋውያንን አስመልክቶ ያቀረበውን ግልጽ መርሕ አቅርቧል። እንዲህም ይላል፤ “በሽበታሙ ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ” (ዘሌ. 19፥32)። 18 ጠና ደዎ፥ ሰው ግብረ ገብና ሥነ ምግባር (አዲስ አበባ፦ አአዩፕ፥ 2008 ዓ.ም.)፥ 93። የዱባ ጥጋብ ሰ ሎ ሞ ን አ በ በ 20 21 በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ የነበረው የካህኑ ኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ እግዚአብሔርን ባለመታዘዛቸውና የተቀደሰውን በመዳፈራቸው እግዚአብሔር አሳዘኑ። ኤሊም ከአምላኩ ክብር ይልቅ የልጆቹ ነገር ስለ በለጠበት አልገሠጻቸውም ነበር። እግዚአብሔር በአሌ ቤት ላይ ተቈጥቶ ሞገሡን ከዘር ማንዘራቸው እንደሚያርቅ ዐወጀ። በምትኩም፥ በፈቃዱ የሚኼድ ሰው እንደሚያዘጋጅ በተናገረው መሠረት፥ ሳሙኤልን አስነሣ። የኤሊም ፍጻሜ አሳዛኝ ኾነ። በለይም የእግዚአብሔር ታቦት መማረክ በሰማ ጊዜ በደረሰበት ድንጋጤ “በበሩ አጠገብ ካለው ከወንበሩ ወደቀ፤ ... ሸምግሎ ደንግዞም ነበርና ዐንገቱ ተሰብሮ ሞተ” (1ሳሙ. 4፥18)። የኤሊ በደል ቀላል አይደለም። ፍርዱም ብርቱ ነበር። ብዙ ጊዜ ይህ ታሪክ ሲነሣ፥ ወጣቶች ተሽቀደድመው የሚሽከረከሩት በሳሙኤል መጠራትና በካህኑ ኤሊ መውደቅ ላይ ኾኖ፥ ኤሊን ክፉኛ በሚያበሻቅጥ አዘንብሎት መጠመዳቸው ይገርማል። ራሳቸውን የዘመኑ “ሳሙኤሎች” በማድረግ “የኤሊዎች ዘመን አብቅቷል!” ሲሉ ይደመጣል። “ብላቴናው ሳሙኤል ይነሣል! ኤሊዎች ይዋረዳሉ!” የሚሉና ተመሳሳይ ሐሳብ ያላቸው መፈክር መሰል ኀይለ ቃላት በቀላሉ ሲሰነዝሩ እንሰማለን። ነገር ግን ሳሙኤል በኤሊ ላይ ሲያምፅ አልታየም። እግዚአብሔር ስለ ኤሊ ቤት ምስጢር ቢነግረውም፥ ኤሊን ሊያዋርደው አልሞከረም። በታሪኩ ውስጥ እንደምናየው፥ እግዚአብሔር ሳሙኤልን በጠራው ጊዜ ከሳሙኤል ይልቅ ቀድሞ የተረዳው ኤሊ ነበር። ለሳሙኤልም ያንን የከበረ እውነት ያስረዳው እርሱው ነው። ይኸን የምለው ካህኑ ኤሊን ለማሞገስ አይደለም። የሳሙኤልን ትክክለኛ ዐቋም ለማጕላት ነው። እግዚአብሔር ያዘነበትን ሽማግሌ ካህን ሳሙኤል አልተዳፈረም። እንዲያውም፥ በኤሊም ፊት እግዚአብሔርን በታማኝነት ማገልገሉን ቀጥሎ ነበር (1ሳሙ. 3፥1)። ኤሊ እግዚአብሔርን ባለመታዘዙ ምክንያት ራሱ እግዚአብሔር እንጂ ሳሙኤል አልቀጣውም። በእርጅናው ፈጽሞ ፈዝዞና ደንዝዞ የነበረው ኤሊ ተሰብሮ እስኪሞት ሳሙኤል በእርሱ ላይ በግንፍልተኝነት አልተነሣም (1ሳሙ. 4፥18)። ልጅ ሳለሁ፥ “በስምንተኛው ሺህ በሽንብራ ጣላ ሥር ተቀምጠን እንፍረድ የሚሉ ልጆች ይነሣሉ” የሚባል ትውፊታዊ ይትበሃል ሰምቻለሁ። እንደኔ ገጠር ቀመስ ትንሽ ከተማ ውስጥ ተወልዶ ላደገና የሽምብራን አዝርዕት ለሚያውቅ ሰው ተምሳሌቱ ለጕድ ነው። ይመጣል የተባለውን ምጣትና መዓት አጕልቶ ያሳያል። ሐሳቡ እውነት ነው ማለቴ አይደለም። የሐሳቡ ባለቤት በተምሳሌቱ ማሳየት የፈለገው በዘመን ፍጻሜ ክፋት ምክንያት ማኅበራዊ አክብሮት ደብዛው ጠፍቶ ውጥንቅጥ ሊፈጠር መቻሉን ነው። በወጣትነት ብቻ ተገፋፍተን የቀዳሚዎቻችንን ጥበብና ብልኀት ከመካፈል እንዳንርቅ መጠንቀቅ ብልኅነት ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 23፥22 ላይ ጠቢቡ ሰሎሞን “የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት” በማለት ይመክራል። ከአቻዎቻቸው ጋር በሚነጋገሩ ጊዜ የሚያሳዩትን ትሕትና እና አክብሮት ያህል እንኳ ለሽማግሌዎች ማሳየት ተስኗቸው በአዛውንቶች ላይ ሲያሾፉ ስናይ መደንገጣችን አይቀሬ ነው። ጥጋብና ወጣትነት እያካለበ ሲነዳን መርሳት የሌለብን ነገር እኛም አንድ ቀን (ያውም ካደለን) አረጋውያኑ ለቀውት በሚኼዱት የሽምግልና ቦታ መድረሳችን ተጠባቂ መኾኑ ነው። “ያኹኑ ትውልድ ያለፉት ጀግኖችን አለማክበርና ላነሰ ተግባር መሰለፍ፥ ’ወይራ ዶግ ይወልዳል’ እንደሚባለው ከአያትና ቅድመ አያት ማነስ ይኾናል። ... የጀግኖችን ምልክት ስንከተል ነው ራእይ የሚኖረን። ካለፉት ጀግኖች የተሻለ ታሪክ ለማስመዝገብ ሥራዎቻቸውን ዕውቅና ሰጥተን መመርመርና ለመማር ዝግጁ መኾንን ይጠይቃል።” 20 አረጋውያን የማኅበረ ሰባችን መዝገቦች እንጂ ፈላሲ (ምርኮኛ) ተደርገው መወሰድ የለባቸውም። ሽበት የክብር ዘውድ ሲኾን፥ ፍጻሜው በጽድቅ አኗኗር ያማረ ይኾናል። እግዚአብሔርም ለእውነተኛ አማኞቹ እንዲህ የሚል ተስፋ ሰጥቷል። “እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፥ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ” (ኢሳ. 46፥4)። ኤሊ እና ሳሙኤል 20 ባይለየኝ፥ “የብሔራዊ ጀግኖቻችን፥” የኢትዮጵያን ማን ነው? ፕሮፌሰር ጌታቸው ኀይሌና ሌሎች አሰናጆች ደረጀ ይመርና ተስፋዬ ሽብሩ (አዲስ አበባ፦ አልቦ አሳታሚ፥ 2012 ዓ.ም.)፥ 149። የዱባ ጥጋብ ሰ ሎ ሞ ን አ በ በ 22 23 የረጅም ጊዜ የትውልዶች ውርርስ ውጤቶች [ናቸው]። ድንገት መሠረት አይዙም።” 21 ወጣቶች አኹንን እና እዚህን ይኖራሉ፤ ሊመጣ የሚችለው የሽምግልና ዘመን ከሩቁ በጭላንጭል የሚታይ ወይም ጨርሶውኑ የማይታሰብ ነው። ውልብታው የደበዘዘና የሕልም ዓለም ዐይነት ይኾንባቸዋል። አረጋውያን ማኅበራዊ ጥድፊያን በስክነት ለመግራት የሚጫወቱት የራሳቸው ሚና አለ። ስለዚህ፥ ዘማሪው እንዲህ ሲል አምላኩን ተማጽኗል፤ “በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፥ ጕልበቴም ባለቀ ጊዜ አትተወኝ” (መዝ. 71፥9)። የሰዓት ቈጣሪውን ወደ ኋላ መጠምዘዝ አንችልም። እሱ በእኛ እጅ ውስጥ አይደለም። ጊዜ ወደ ፊት ገሥግሦብናል። ነገር ግን በተሰጠን ጊዜ ለእኛ በተሰጠን መለኮታዊ ባርኮትና ምሕረት መጠን ወደ ተተለመልን ፍጻሜ በጸጋው መገሥገሥ አለብን። አረጋውያን ከስኬታቸውና ውድቀታቸው የተማሩትን ነገር ለተከታዩ ትውልድ የማስተላለፍ ጸጋና ዐደራ አላቸው። ልጆች (ወጣቶች) እግዚአብሔርን ማወቅንና ለአባቶቻቸው የተደረገውን መለኮታዊ ቸርነት ከአባቶቻቸውናና እናቶቻቸው መስማት ይኖርባቸዋል። ሐሳቡ ሰፋ ያለ ዐውድ ያለው መኾኑ እንደ ተጠበቀ ኾኖ፥ ሙሴ ለሕዝቡ ተመሳሳይ ሐሳብ እንደ ነገራቸው በዘዳግም 32፥7 እናገኛለን፤ የዱሮውን ዘመን አስብ፥ የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል። መቋጫ፥ ነጭ መስመር አትርገጡ ጐጂና ጐታች ባህሎች መታረምና ሲብስም መወገድ እንደሚኖርባቸው ባያከራክርም፥ አንድ ማኅበረ ሰብ በተዋሓደው ሠናይ ማኅበራዊ ባሕርይ የጋራ 21 ባይለየኝ ጣሰው፥ “የብሔራዊ ጀግኖቻችን ታሪክ እየተቦረቦረ ነው፥” ደረጀ ይመር እና ተስፋዬ ሽብሩ፥ አዘጋጆች፥ የኢትዮጵያ ተጠሪ ማነው? (አዲስ አበባ፥ አሳታሚ የለም፥ 2012 ዓ.ም)፥ 144። ከሕይወት ጡረታ አይወጣም አረጋውያንስ ምን ያድርጉ? በዕድሜያቸው መግፋት ተስፋ አይቍረጡ። ዕድሜ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው (ዘፍ. 15፥15፤ ኢዮ. 5፥26፤ 42፥17)፤ “አብርሃም በጠቅላላው መቶ ሰባ ዐምስት ዓመት ኖረ። ከዚያም ዐረፈ፤ ዕድሜ ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ” (ዘፍ. 25፥8)። በዕድሜ መግፋት የሚገኘውን የሕይወት እርከን ያላገኙ ብዙዎች ናቸውና አረጀሁ ብሎ ማዘን ትክክል አይደለም። ሰዎች በምድር የሚያረጁት ረጅም ዕድሜ ስለ ተሰጣቸው ነው። በመኾኑም፥ እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜ ኖረን ፈቃዱን እንድናደርግ ከፈቀደ ትንፋሻችን እስካለ ድረስ ከግሥጋሤአችን መታቀብ የለብንም። ጸጸት የበላው ሕልም የአሉታዊ እርጅና ምልክት ነው። ረጅም ዕድሜ የተሰጠው ሰው በረጅም ዘመኑ ባላከናወናቸው ነገር ከሚጸጸተው በላይ መጨነቅ ያለበት ሌላ ብርቱ ጕዳይም አለ። ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ግንኙነት። ካለፈው ይልቅ በመጪው ላይ ማተኰር አለበት። አንድ አረጋዊ ሰው ምን ስንቅ ቋጥሮ ነው የምድር ሕይወቱን የሚያጠናቅቀው? የዕድሜ መግፋት ይዟቸው የሚመጣው ጓዞች አሉት። እንደ ቀድሞው በቀላሉ መንቀሳቀስ ያስቸግራል። ምርኵዝ መጨበጥ ይከተላል። ወገብና ጕልበት በቀላሉ አይታዘዙም። መገጣጠሚያዎች በቍርትማት ይበግናሉ። ጅማቶች ይዝላሉ። አንድም ነገር ቀድሞ እንደ ነበረው አይሰነብትም። በትንሣኤ በምንቀበለው የአዲስ ፍጥረት መታደስ ኹሉ አዲስ እስከሚኾን ድረስ ይህ ኹሉ ድከምና ዝለት ባለንበት ዓለም ሥርዐት አይቀሬ እንዲኾን ኀጢአት በሰበብነት በውስጣችን ተደንቅሯል። ኾኖም፥ ዕድሜን የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው። መቈየታችን ፋይዳ ባይኖረው ኖሮ እግዚአብሔር ኹላችንንም በዕድሜያችን ማለዳ ይሰበስበን ነበር። ማንኛውም ማኅበረ ሰብ አንጋፋ የዕድሜ ባለጠጎች በኖሩት መጠን የነባር ሐሳቦቹና ዕሴቶቹ ባለ ዐደራዎች ይኖሩታል። አንድ ትውልድ ድንገት ብድግ ብሎ ፈጥሮና አሳድጎ የሚያጐለብተው ዕሴት አይኖርም። ዶክተር ባይለየኝ ጣሰው ጥሩ አድርገው እንደ ገለጹት፥ “ዕሴቶች ለአንድ ማኅበረ ሰብ ጌጦች ናቸው። የሚዋቀሩትም በባህልና በረጅም ጊዜ የታሪክ ኺደት ነው። አንድ ማኅበረ ሰብ ዕሴቶችን መፍጠር [ቢችልም፥] የዱባ ጥጋብ ሰ ሎ ሞ ን አ በ በ 24 25 መንገድ ተሳስረናል። ሰብአዊ ትስስራችንንና አንዱ ለሌላው ማስፈለጉን መገንዘብ የእርስ በርስ አክብሮታችንን ይጨምራል። ቢሊ ግራሐም፥ “ለሌሎች ያለን አክብሮት እያደገ የሚኼደው እኛ ራሳችን በሌሎች ላይ መደገፋችን እየጨመረ ሲኼድ ነው” 24 የሚሉት ይኸን ከግምት አስገብተው ነው። ለውጥ አይቀሬው የሕይወት ዕጣ ነው። ልጅነት፥ ዐፍላ ጕርምስና፥ ወጣትነት፥ ጕልምስና፥ በሳል ዐዋቂነት እና አረጋዊነት መሥመራቸውን ጠብቀው ተሰድረዋል። ከአንዱ ወደ አንዱ ከመሸጋገር የምናመልጥበት ዕድል የለም። ተራ በተራ እንሻገራለን። አንዳንዶቹ የለውጥ ኹኔታዎች ተጠባቂ ናቸው። ሌሎቹ እንደ መጤ-ደራሽ ድንገት ከተፍ ይላሉ። ቸሩ አምላክ ከፈቀደልን አረጋዊነት ልንደርስበት የምንችለው የዕድሜያችን ክፍል ነው። እግዚአብሔር ከዕድሜው ብቻ ሳይኾን ከጥበቡም፥ ከሽበቱ ብቻ ሳይኾን ከክብሩም እንዲያድለን መለመን አለብን። ያ ክብር ዝም ብሎ በዘፈቀደ አይገኝም፤ በጽድቅ ሕይወት በመመላለስ እንጂ። አዛውንቶቹ ጸጕራቸው የነጣው በዋዛ አይደለም። ቅንጣቶቹ በጊዜና በልዩ ልዩ ፈተናዎች ብዛት ደማቅ ቀለማቸውን ቢያጡም በብዙ ትንግርቶችና ታሪኮች ወዝተዋል። ደካማ መስለው የነፋስ ኀይል ቢያወዛውዛቸውም ሥር ሰደዋል፤ ልትነቅለው በሞከርህ ጊዜ የምታወዛውዘው የቆምህበትን ምድር ጭምር መኾኑን አስተውል። በተጐነበሰ ትከሻ ላይ የደረጃ መሰላልህን አታስደግፍ። አርቀህ ማየት ችለህ ከኾነ በግዙፋኑ ትከሻ ላይ አሻግረህ ነው። ጡንቻህን ለማፈርጠም ደካሞችን አትድፈቅ። ሽበት ነጭ መሥመር ነው፤ የሚያስከትለውን አታውቅምና፥ ተዳፍረህ አትርገጠው። 24 Billy Graham, Nearing Home: Life, Faith and Finishing Well (Nashville: Thomas Nelson, 2011), 130. አኗኗሩን እንዲመራ መተባበርና ሲቻልም ያ ባህሉ እንዲበለጽግ መጣር ያስፈልጋል። ይህን አለማድረግ ጦሱ ለራስም እንደሚተርፍ በእኛ የደረሰው ምስክር ነው። በሕይወት እያሉ ያላከበርናቸውን ሲሞቱ ጠብቀን ብንንጫጫላቸው የምንፈይደው ብዙም አይደለም። አለበለዚያ ሚካኤል ሺፈራው በአንድ አሊጎሪያዊ ተረኩ ሲወቅስ (ምናልባትም ሲወቅሰን) “በዚህ ሕያው ከሳሽ ሙት አወዳሽ መንደር ነቢይ በተረት እንጂ በሕይወት እንዲኖር አይፈቀድለትም” 22 ማለቱ እድፋም መለያችን ይኾናል። ቀዳሚ የአገር ባለውለተኞችን የማክበር ጕዳይ በየትኛውም ማኅበረ ሰብ ውስጥ እንደ አንድ ወሳኝ ግብረ ገባዊ መገለጫ ሲወሰድ መኖሩ የከረመና የተከበረ ነገር ነው። በእኛ የተጀመረ አይደለም። ግብዝነት በተጫነው ትሕትና ሳይኾን ልባዊ አክብሮት በወለደው ምግባር በርካታ ቁም ነገሮች በተለያዩ ማኅበረ ሰቦችና አገራት እንደሚፈጸሙ ግልጽ ነው። እኛ ታዲያ ስለምን ብለን እናቃልለዋለን? በዕድሜ ታላቅ የኾነውን ማክበር፥ አረጋውያንን መንከባከብና ማገዝ ጠቅለል ባለ አነጋገር በማኅበራዊ ልማድና ሥውር ወግነቱ ዘመናትን ዘልቋል። ይህ ዐይነቱ አስተሳሰብ፥ ወግና ባህል ተጽፎ የተደነገገ ሕግ አይደለም። ይልቅስ፥ “ከግዙፉና ቍሳዊው ባህል ጀርባ የማኅበረ ሰቡ አባላት የሚያምኑትና የሚሠሩበት ያልተጻፈ ሕግ ነው። ግለ ሰቡም ይህ አስተሳሰብ ከልጅነቱ ጀምሮ በአስተዳደጉ በተለይ በቤተ ሰቡና ባህል መሪዎቹ አማካይነት ይዋሓደዋል።” 23 ያንን ሳያራክሱ ጠቃሚና በጎውን በመውሰድ የማኅበራዊ ግንኙነት መሠረቶችን ማጠባበቅ ይበጃል። ጽኑ መሠረት እስካላገኘ ድረስ የሕይወት ሸክም ይከብዳል። በዚህ ዓለም ልዩ ልዩ ማዕበል ሳንናወጥ ለመቆም ጠንካራ የእምነት ዐቋምና ዕሴት ከሌለ በቀር እንናወጣለን። በመኾኑም፥ በራሳችን ብቻ እንደምንቆም ሌሎችም እንደማያስፈልጉን ማሰብ ተጐጂ ያደርገናል። ሰዎች ስንባል በአንድም ይኹን በሌላ 22 ሚካኤል ሺፈራው፥ የወፍ ማስፈራሪያ እና ሌሎች ዐጫጭር ታሪኮች (አዲስ አበባ፥ 2000 ዓ.ም.)፥ 112። 23 ኀይለ ገብርኤል ዳኜ፥ ባህልና ትምህርት በኢትዮጵያ (አዲስ አበባ፦ አዲስ አበባ ዩኑቨርሲቲ ፕሬስ፥ 2007)፥ 3። የዱባ ጥጋብ ሰ ሎ ሞ ን አ በ በ 26 27