ሰላም እና ነፃነት ለሁሉም Copyright © 2017 E.C Self-published E-Book Book Cover Design By: Bety Bety Printed in EFDR/Ethiopia Available on ፡ https://t.me/MesobMagazine First Printing E-Book s Edition, 2017E.c Mesob Magazine / መሶብ መጽሔት Edited and Written by Robel Eyoab / ሮቢን ኢዮዓብ Printed By: Mesob Magazine & Bety Design’s መታሰቢያነቱ ሰሚ አተው ውስጣቸውን ያራደውን ጩኸት በሞት ለማስቆም ህይወታቸውን ለቋጩ ውድ ነፍሶች !!! ምንም የተገፋ ቢሆን የተናቀ ምንም የተገፋ ቢሆን የተናቀ በእኔም ልቦና በእኔም ልቦና ያልጸደቀ ያልጸደቀ ጎዳና ነው የሄድኩት ያልረቀቀ ጎዳና ነው የሄድኩት ያልረቀቀ የጸሐፊው የምስጋና ቃል ይህ ፅሁፍ በመጀመሪያ ተጠናቆ የተቀመጠው በኢትዮጵያን ዘመን አቆጣጠር 2014 ዓ ም ሲሆን አሁን እንደ ዲጂታል ህትመት እንዲወጣ ምክንያት የሆኑኝ ሁል ጊዜ በፅሁፎቼ የሚያበረታቱኝ ወንድም እና እህቶች ስላሉ ነው ድፍረቱን ያኘውት፡፡ ሁሉንም ጠቅሼ መጨረስ ባልችልም የተወሰኑ ቀጥታ በዚች የግል ጉዞዬ ላይ ተመስርቼ የፃፍኩትን ያበረታቱኝ መካከል ኤፍሬም ልገልፀው ከምችለው በላይ ጓደኝነትህ እና የቀና ምክርህ የድጋፍ ቃልህ ከምንም ነገር በላይ ትልቅ ቦታ ምሰጠው ነው እና ላመሰግንህ እወዳለሁ፣ የመጀመሪያው ነው በ 2014 የመጀመሪያውን የተጠናቀቀ ፅሁፍ አንበቦ ልባዊ ማበረታቻውን እና ድጋፉን ለሰጠኝ ኢሚርን ከዛም በላይ ድንቅ ወዳጅነቱን ሁሌ ላመሰግነው ወዳለው፣ በመቀጠል ቾምቤ የሁልጊዜ ድጋፍ ሰጪዬ መካሪዬ እና ወዳጅ ስለሆነኝ ድጋፍ እና ወዳጅነቱ ድፍረት ስለሰጠኝ ላመሰግነው ወዳለው እንዲሁም ደግሞ ቃልአብ አንብቦት ሀሳቡን እና ምክሩን ያጋራኝ ድንቅ ጓደኛዬ ነው ለእሱም ለማይቀንስ ፍቅርህ አመሰግናው በመቀጠል ሀሳቡን በነገርኳት ጊዜ የመፅሐፉን ገፅ ሽፋን እና ለግሌ የሚሆን እትም በግሏ አዘጋጅታ የሰጠችኝ የተወደደች እህቴን ቤቲን ላመሰግን ወዳለው የሁላችሁም አብሮነታችሁ እና ድጋፋችሁ በልቤ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ እንዲሁም ለማንበብ በማውረድ ድጋፋችሁን ያሳያችሁኝ ብርቱው በበይነ መረብ የተዋወቅን ድንቅ ኢትዮጵያዊያን ለጂቢቲኪው + ማህበረሰብ ሁላችሁ ምስጋናዬ የላቀ ነው ፈጣሪ ያክብርልኝ፡፡ የቃላት ግድፈት ካለ ይቅርታ መጠየቅ እንወዳለን እንዲሁም ግልፅ ያልሆኑ አገላለፆች ካሉ በነፃነት በፌስቡክ ገፄ (Robin Eyoab) እንዲሁም በኢሜል ( robeleyoab@gmail.com ) ልታናግሩኝ ትችላላችሁ፡፡ በድጋሚ አመሰግናለሁ ! ሮቢን ኢዮአብ 2017 ዓ ም / ኢትዮጵያ ROBEL EYOAB / ሮቢን ኢዮዓብ 3 መግቢያ ይህን መጽሐፍ መፃፍ ስጀምር ለመጽሐፍትነት ልፅፈው አስቤ አልነበረም እንደ ማስታወሻ እንጂ፡፡ሰሚ ያጣ ከብዕሩና ከደብተሩ ውጪ ሌላ ምን ጓደኛ አለው ? አማርኛ ቋንቋ ሊያነበንባቸው ያልተገቡ ገጠመኞቼ በየትኛው ቋንቋ ልተርካቸው ይቻለኛል ? ህዝቡ ያወገዘውን በየትኛው ልናገረው እችላለው ? ይህንንም ለመጠቀም መብት እንዳለኝ አስባለው እኔም አካል ነኝና የዚ ማህበረሰብ፡፡ አንድ ብዬ ብጀምር ሊያደምጡት ሊያነቡት የመጨረሻዋን ገፅ ድረስ የሚዘልቅ ማን እንደሚሆን አላቅም፡፡ምክንያቱም ለመስማት በአስተዳደጋችን ለባህላችን ተስማሚ ያልሆነ ታሪክ ገጠመኞቼን አጋራችኋለውና፡፡ከተለመደው የተለየ አብዝቶ ከሚነገር፣ ከሚሰበክ ጽሕፈት የተለየች ናት፡፡ምዕራፋቱ በየግላቸው የእኔን እና የሌላን ሰው ታሪክ ቢያወሱ የተወገዙ የተጠሉ እና አድማጭ ጆሮውን አንባቢም ዐይኑን ሚነሳው እንዳይሆን ፈራለው ነገር ግን ማድመጥን ለመሚመርጥ ውሸት ያልገባበትን እውነታዬን በገጠመኝ መልክ እዲሰማ ይህን ለማበርከት ፈቅጃለው፡፡ ነፃነትን ያጣ ከገጠመኝ አልፎ የማንነት ክፍል ሊሆን የበቃ እንደ ገጠመኝ አይነገርም፡፡እኔም ተወልጄ ባደኩበት ማህበረሰብ፤ባደኩበት ሀይማኖት፤ቤተሰብ፤አከባቢ በፅኑ አምሬ ያደኩ ሰው ነኝ፡፡ነገር ግን እኔነቴ እና የህይወት መንገዴ ከማህበረሰቡ ተቃራኒ፣ከቤተሰቤም ሲለየኝ በኖርኩበትና በተወለድኩበት አከባቢ ባይተዋር እስኪያደርገኝ ሌላ መንገድ ሆኖ ፈተና ውስጥ ከተተኝ ብዙው ትረካዬ ስለ ፈተናዬ አይደለም ገጠመኝ ስል እንዳልኩት ገጠ - መኝ ነው ያታገለኝ ወስዶ የባህርን ወጨፍ ከአለት እንደሚያላትም ነፋስ መነሻ መድረሻዬን ልዩ ያደረገብኝ ነው፡፡ ገጠ - መኝ እንደመሆኑ ለእኔ ብቻ የቀረ አይደለም ግን ሰውን ወደ እኔ ያመጣ እኔንም ወደ እነሱ የወሰደኝ ኩነት ነው፡፡ ፆታዊ ፍላጎቴ ነው ከተባለው መስመር የተለየ በመሆኑ ስህትት ሆኖ ለሰው ለቤተሰቤ ለጓኞቼ በነፃነት አልናገረው ነገር ድብቅ ሽሽት ፣በጨለማ ስኖረው የነበረ ግን ሚስጥራዊው እኔነቴ የተሰየመበት እውነታዬ ነው፤ ነው የተባለው ብዙ ስለሆነ የእኔ ነው ግን አድማጭ አቷል፡፡ ሁሉ ያወቀው የማንነቴ ክፍል ሳይሆን በሮቤል ኢዮአብነቴ ያወቁኝ ናቸው፡፡ያልተደበቀ የተገለፀ ማንነቴን የሚያውቁ ጀምሬ በፊታቸው እኔን ስሆን ግን ሮቤልንም ሆኜ የተመላለስኩባቸውን ታሪኮቼን አወሳው፡፡ሰላምታ ሲሰጡኝ የምቀበለው መደበኛ በታወቀው ስሜ ነው ነገር ግን ያወራቸው የነበረው እኔ ውስጥ ያለው ሌላው እኔነቴ ሮቤልም ነበር፡፡ይሃን ግን ማወቅ አይችሉም ምክንያቱም አንድ ብመስላቸው መንታ ነኝ መንታ ሆኜ የኖርኩት በመገለጥ እንጂ እኔስ ሁለቱንም የሆንኩ አንድ የተዋሃድኩ የማልለያይ ሰው ነበርኩ እኔን እያናገሩ ሮቤልን አለማናገር አይቻልም፣ ሮቤልንም እያወሩ እኔን አለማናገር አይቻልም እኔ እና ሮቤል አንድ ነን፡፡ ያልገለጥኩት ግን ያለፍኩት ብዙ ብዙ አለ ነገር ግን ወደ እኔ የመጡትን አስፍሪያለው፡፡ብርሃን ሲሉ ያከበሩት ጨለማ ሲሉ የኮነኑት ሰው አንድ ሆኜ በጓደኞቼ፤በቤተሰቤ፤በማህበረሰቤ፤በቤተ - ሃይማኖቴ ተጉዣለው ምክንያቱም ሮቤልን ከእኔ እኔንም ከሮቤል መለየት አልተቻለም ነበርና ብርሃንም ስሆን ጨለማ፤ፃድቅ ሲሉኝ ኃጢአተኛ ያሉትንም ነበርኩ፤መልካም ሲሉ ክፉም፤ጨዋ ሲሉ ባለጌም ነበርኩ፡፡ነገር ግን ይህ ሁሉ የሰው ምደባ እንጂ እኔ ምንም አልነበርኩም እኔ እኔኑ ብቻ ነበረኩ ግን በሰው ገለፃ በሰውም ማብራሪያ ተጠምጄ አሳር፤ስቃይ የማይወጡት ትግል፤መልስ የማያገኙለት ፍለጋ፤የማይበርድ ጦርነት ውስጥ ኖሪያለው፡፡ እኔ ፃድቅ ወይ አመፀኛ ነኝ ብዬ አልናገርም፤መልካምም ወይም ክፉም ነኝ ብዬ አልናገርም ምክንያቱም አንዱንም ለመሆን ፈልጌ ሳይሆን ሆኜ የተገኘው ነኝ፡፡ነኝነቴ ግን እንደ ሰው፤እንደ ማህበረሰቡ፤እንደ ሃይማኖቴ፤እንደ ቤተሰቤ እንጂ ነኝ የምለው ምንም ነገር የለም ሰው ደግሞ ነው ብሎ ካስቀመጠው ያልሆንኩትም የለም፡፡ ‹‹ አንተ ፃድቅ ነህ ኃጢአተኛ ብትሉኝ ?›› እኔ ሁለቱን ነኝ አልላችሁም እንደ ሰው ገለፃ እና ምደባ ከጠየቃችሁኝ ግን መልሴ የተለየ ነው ‹‹ አዎ ጻድቅም ነኝ ደግሞም ኃጢአተኛ ነኝ ›› እላችኋለሁ፡፡ እንግዲህ የተከፈተ ልቦና ያሰፈልጋል ኢትዮጵያዊ ለሆነ ልቦና ለማንበብ ታሪኬን ወግ ማህበረሰብ ቅድመ - እውቀት እንዲያቅለሸልሽ ሊያደርግ ጥላቻንም ልብ ውስጥ ሊያቀጣጥል ይችላል ግን ልቅ የሆነን ነገር ደግሞ አልፃፉኩም ልቅ ሊሆን የሚችለው ፈጥሬ ባወራው ነው ነገር ግን እንዳልኩት የሆነ ሆኖ ያለፈ ነገር ብቻ ነው የፃፍኩት፡፡ A short intro or kicker of the article will go here. This part acts as a bridge between the headline and the article itself. 5 By Margarita Perez | Photography by Hannah Morales ክፍል አንድ ላይጋሩ ስሜት እኔነቴን ላይሰጡ ፈዋሽ መድኃኒት የህመሜን ምዕራፍ አንድ እኔ እና ሜሮን 2010 ዓ ም በህይወቴ እንኳን ለሌላ ለራሴ እንኳ ለወንድ ያለኝን ስሜት ደግሜ ተናግሬ አላቅም ፆታዊ ፍላጎቴን ማወቅ ከጀመርኩ ወዲህ ያለኝ ነገር በሙሉ ለወንድ ነው ለሴት ትልቅ ክብርና ፍቅር ያለኝ ቢሆንም በፃታዊ መንገድ ለማሰብ አቅሙ ኖሮኝም አያውቅም ለምን እኔም አላቅም ..... ይህ አመት እኔ የ 12 ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ከመጣ በኋላ ጊቢ የተባለ መካነ አዕምሮ የገባውበት ነበር ብዙም ምጠብቀው ነገር ስለሌለ የተሰጠኝን ነገር በፀጋ ተቀብዬ አስፓልት ሆነ ኮብልስቶን የሌለበት ካለውበት ከተማ እጅግ የሚርቅ ጠረፍ ድንበር ገብቻለው መንገዱ አዛ ነው አድካሚ ነው የአካባቢው ሙቀት አንደኛ ነው ቢሆንም ግን ለእኔ ምንም ነበር ሁሉ መቻል ስንፈለግ እንችለዋለን ጊቢ ከገባው በርካታ ጊዜያት በኋላ በርካታ ሰዎችን በአንድ ጊዜ ለመተዋቅ ጊዜ አልፈጀብኝም ተጫዋችነቴ እና ተግባቢነቴ እንኳን ፍሬሽ የሲኒየር ሲኒየር ነበር ያስመሰለኝ ቤተ ክርስቲያን ላይ ክላስ ላይ እንዲው ከመላው የጊቢው ሰው ጋር ተዋወኩ ( እንደ ጋደኞቼ ከሆነ ጊቢ ውስጥ 5 ሺ ሰው ቢኖር 3 ሺውን ያውቃል ይላሉ ) ሜሮን ቤተ ክርስቲያን ላይ ከተዋወካቸው ሰዎች አንደኛዋ ናት ሲበዛ ለሰው ፍቅር ያላት የዋህና ትሁት ንፁህ ሴት ናት በእድሜ ታላቄም ብትሆን ልጅነት አለባት ነገር ግን ሰው ስትወድ ከልቧ ነው፡፡ አንድ ቀን ማታ ስለፍቅር እየተወራ በነበረበት የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ጊዜ በእኛ ቡድን ስር ያሉት ራሳቸውን እየደበቁ አንዳንድ ነገር ገልጠው ተናገሩ እኔ ምናገረው ምንም ነገር አልነበረም ብቻ ልጅ ሳለው እወዳት ስለነበረች የእቃቃ ሚስቴ አወራው .. ፍቅር እጅግ ጥልቅና ኃያል ነገር ነው መኃልየ መኋልዬ ፍቅርን ሲገልፀው “ በልብህ እንዳለ፣ በክንድህም እንደምትይዘው ማኅተም አስቀምጠኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች፣ ቅናቷም ( ጥልቅ ስሜት ) እንደ መቃብር ( ሲኦል ) ጨካኝ ነትና፤እንደሚንቦገቦግ እሳት፣እንደ ኀይለኛም ነበልባል ትነዳለች፡፡የውሃ ብዛት ፍቅርን ሊያጠፋ አይችልም፣ ፈሳሾችም አያሰጥሟትም .” በዚ ክፍል ለበርካታ ሰዓታት ስንመካከር ቆይተን ወደ ጊቢ ገባን እኔና ሜሪ እንደ ለመድነው ቀደም ቀደም እያልን እያወራን እንሄዳለን ሜሪ ለኔ የአንድ አመት ሲኒየሬ ናት ቢሆንም እንደ ጓደኛ ቀለል ያለችም ናት አንድ ነገር ሂንት ነግራችኋት ሙሉ ነገሩን ካልሰማች አትፋታችሁም አወራቸው ስለነበረች የልጅነት ሚስቴ እየጠየቀችኝ ወደ ጊቢ አመራን እኔም የመጣው ይምጣ መናገር አለብኝ ስሜቴን ስል ላወራት እንደ ምፈልግ ነገርኳት፡፡ ሁሉንም ተሰናብተን በላውንቹ ፊት ጨለም ካለው ስፍራ ተቀመጥን .. ምን ተብሎ ነው ሚጀመረው ግራ ገባኝ መናገር እንደጀመርኩ ማልቀስ ጀመርኩ አሁን ስስቅ የነበርኩት ልጅ በአንዴ እንባ በእንባ ንፍጥ በንፍጥ ሆንኩኝ ለስሜቴ ይሄን ያህል ቅርብ ነበርኩ ለረጀም ጊዜያት ማንንም ሳላወራ የታፈነው ብቸኝነቴን የዛን ቀን ማታ አፈረጥኩት ... ለወንድ ልጅ ስሜት እንዳለኝም ነገርኳት ጊቢ ከገባው አይቼ ማላቀው የወንድ ልጅ እርቃን ገላ በየቀኑ ዶርሜ ፊት ራቁታቸውን ሻወር የሚወስዱ ወንዶች ሰለም ነስተውኛል ማታ በህልሜ ሁሉ ድንገት ብቅ እያሉ ያስጨንኩኝ ጀምረዋል ዶርም ውስጥ ወንድ ለወንድ አይተፋፋር የተባለ ይመስል መለመላቸውን ፓንት ሲቀይሩ አንዴ ቂ ** ውን ቁ ** ውን ሳይ ድንግጥ እላለው ነገር ግን የዶርሙን እንኳ ለመከላከል ችያለው ማንም እኔ ስኖር እንደዛ እንዲቀይሩ እንደማልፈለግ በግልጥ ነው የተናገርኩት ሁሉም ስለሚወዱኝና ሲለሚያከብሩኝ ታዘዙልኝ ፡፡ሜሪ የምነግራት ነገር ፈፅሞ ሰምታ የማታቀው እንግዳ ነገር እንደሆነ ተረዳው ለማን ምን መናገር እንዳለብን ማውቅ ትልቅ ብልሃት ነው ምክንያቱም እናንተ አውርታችሁ ቀለል ሊላችሁ ይችላል ይሃ ሰው ግን ምንም ማድረግ በለመቻሉ የሚሰማውን ስቃይ መረዳት አንችልም ፡፡ ፡፡አብራኝ ማልቀስ ጀመረች coming out እንደዚ መሆኑን መቼ አወኩ ስናለቅስ ድምፃችን ሁሉ ይሰማ ነበር ብቻ ኃይሏን አሰባስባ ‹‹ እሺ አባ ኪያ አድርገህ ታቃለህ ..›› ስትል እንባ ባነቀው ድምፅ ጠየቀችኝ ‹‹ በየሱስ ስም ሞቻለው እንዴ ይሃን የማደርገው ....›› እውነት ነው አሁን ላይ ከዚ ቃሌ የተነሳ ሞቻለው ከወንድ ጋር ወሲብ ማድረግ ያነፃፀርኩት ከሞት ጋር ነበር ይህም ከተጨመረብኝ አስተሳሰብ የተነሳ እንደሆነ መለስ ብዬ ሳስበው እገረማው ምን ያህል ማህረሰቡ ሆነ ያመናቸው ያከበርናቸው ሰዎች ራሳችንን እንድንጠላ የማድረግ አቅም እንዳቸው እረዳለሁ፡፡ ብዙም አልቆየንም አለቀስን በምትችለው መንገድ ከዚ ነገር መውጣት እንድችል ልትረዳኝ ቃል ገባችልኝ የዋህነቷ ሻወር ውጪ እንድወስድ ሁላ ሃሳብ አቅርባልኝ ነበር፡፡ አንዳልፈተን ቤት ውጪ ልትከራይልኝ ሁሉ ነበር ምንም እንኳ 2011 የአመቱ መጨረሻ ላይ በዚ ነገር አሳንሳ እንደምታየኝ እስከምረዳ ድረስ ጥሩ ወዳጅነት አሳይታኛለች ምንም እንኳ ባልጠላት ለሷ መንገሬን እፀፀትበታለው ክፉ ሆና አይደለም ነገር ግን መፍትሄ የሌለውን ነገር መፍትሄ ለመፈለግ የማትወጣው ጉድ ውስጥ ስለጨመርኳት በራሴ እናደዳለው ... የዛን ቀን ማታ እኔ ወደ ዶርም እፎይ ብዬ ስገባ ሰዎች እንደነገሩኝ ስታለቅስ እንዳመሸች እና ቤተ ክርስቲያን ላይ አብሯት የሚያገለግለውን በተለምዶ DAD የምንለውን ሰው ጠርታ ነገሩን ነገረችው ልንገረው ስትለኝ እሺታዬን ገልጬ ስለሆነ በፍቃዴ ነው ከዛ ቀስ በቀስ እያለ በህይወቴ ያማልረሳው ጠባሳ ጥሎ ለመሄድ በቃ 2011 የአመቱ መጨረሻ ላይ 10-15 የሚደርሱ የቤተ ክርስቲያን የወጣቶች ህብረት መሪዎቸ እና አንዳንድ ሰዎች ስለ እኔ ለማወቅ በቅተዋል፡፡ከዚ ቀደም ብሎ ባለው 2010 ክረምት ቤት መታ ለቤተሰቤ ካልተናገርኩ ብላ አስደንግጣኝ ነበር፡፡ እሷ መታ ለእናቴ እንደ ምትናገር ስለነገረችኝ ሳልወድ በግዴ ለቤተሰቤም HALF COMING OUT ለማድረግተገድጄ ነበር እነሱ ባደረሱብኝ ነገር ከትምህርት ገባታ ሁሉ አቋርጬ ሁሉ ለመሄድ እስከመወሰን ደርሼ ነበር ነገር ግን ይሃ አልሆነም እነሱ ተመርቀው ሲወጡ የተሰበረውን ልቤን ደብቄ ጠንካራ መስዬ ለመኖር ሞክሪያለው ጓደኞቼ ለእነሱ ነግሬ ለነሱ ያልተናገርኩት ነገር ምን እንደሆነ እስከዛሬ ባለማወቃቸው ነገሩ ሲነሳ ጥፋቱ የእኔ እንደሆነ ይወቅሱኛል ልክ ናቸው ጥፋቱ የእኔ ነው ፡፡ ምዕራፍ ሁለት እኔ እና ጆን ጥር 1 ፤ 2011 ዓ ም ወልቂጤ ስናደርገው ከነበረ ረዥም ጉዞ የማይደርስ የለም ለምሳ ወልቂጤ የሹፌሮች ሆቴል ስንደርስ መኪናው ከዋናው መንገድ ወጣ ብሎ ባለው ስፍራ አቆመ፡፡ ከለሊቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ያለማቋረጥ ስንጓዝ ስለነበር ድክምክም ያላለ ፊቱ በእንቅልፍ ያላባበጠ አንድም የለም እኔም በበኩሌ መንገዱን ያማከለ አለባበስ ለብሻለው ለዝነጣ ስላልወጣው አንድ ወፍራምና አስቀያሚ ሰፋ ያለ ግራጫ ቀለም ያለው ቱታ ለብሻለው ከላይ ደግሞ ለለሊቱ ብርድ መከላከያ ምን የሚያክል ወፍራም ሹራብ ... ለሚያየኝ ከበረዶ ስፍራ የምምጣ ነው፡፡ ወዲያው ሰው መውረድ ሲጀምር ጠበኩና ከሹራቤ ስር ለዚ ሰዓት በለበስኩት ቲሸርት ብቻ ቀረው ታታው ከፊትም ከዋላም ያሉት በሮቹ ተከፍተው በሙቀት ላብ በላብ የሆነው ሁላችን እየተገፋፋን መውረድ ጀመርን ከመጨረሻው ወንበር ስለተቀመጥኩ ፈጠን ብዬ ሙቅ ሙቅ የሚለውን አየር በንጹህና ቀዝቃዛ አየር ስስብ ሲያዞረኝ የነበረው ሁሉ ምቾት ማጣት ውልቅ ብሎ ከላዬ እንዳልነበር በነነ፡፡ ከሁሉ በላይ ግን አይኔን ከፊት በኩል የሚወርደው ወጣት ልቤን በድንጋጤ ሞላው ... አዎ ቆንጆ ሳይ የዚ አይነት የመፍዘዝ ባህሪ አለኝ ቀጠን ብሎ ረዘም ያለ ቀይ ፈዘዝ ያለ ጥቁር መነፅር ከላይ ጅንስ ጃኬት ሱሪውን በውል አላስታውስም ምክንያቱም አይኔ በፊቱ ውበት ሌላን ላለማየት ፈዘዋልና ... ከጀርባው ካለ አንድ ልጅ ጋር የሆነ ነገር አያወሩ ነበር ሚወርዱት ድንገት እሱን እያየው ፈገግ ስል የሚያምሩት ነጫጭ ጥርሶቹ ፈገግ አስባሉኝ ሳቁ ንፁህና የዋህ ነው ( ይሃን እንዴት አወክ አትበሉኝ ምናልባት በሰዓቱ የተሰማኝ ስሜት ይሆናል ) ከወረድኩ ጀምሮ ሳልንቀሳቀስ እሱ ላይ ማፍጠጤን አላስተዋልኩትም ነበር መኪና ውስጥ ያሉት ተማሪዎችሁሉ እርስ በርሳቸው ምሳ ፍለጋ በየቦታው ገባ ገባ አሉ ድንገት ከጀርባዬ ‹‹ ሮቢ የት እንግባ ..›› ሲል አንዱ ጓደኛዬ ሲናገር ከሄድኩበት የፍዘት ዓለም መለስ ብዬ አይኔን ከልጁ ላይ ነቀልኩ .... ይሃ የተመታ ሹፌር መንገደኞች መሆናችንን እንደማያውቅ ነገር ስጋ ብቻ ያለበት ቤት አቁሞናል ማን መሰልነው ተማሪዎች እኮ ነን ገንዘብ መቆጠብ አለብን ..... ብዙዎች በአከባቢው ወደነበሩ ሽሮ ቤቶች ሮጥ ሮጥ እያሉ ቦታ ቦታ ያዙ አይኔ የተተከለበት ልጅ ከፊቴ ተሰወረ ብቻዬን ብሆን በተከተልኩት ነገር ግን የአምስቱን ጓደኞቼን ፍላጎት ተከትዬ አንዱ ሽሮ ቤት ገባን ከጠዋት ጀምሮ እስከ 4 ሰዓት አንድ መኪና ውስጥ ሆኜ ልጁን አለማየቴ እያንገበገበኝ ነው ተመልሼ ስገባ የአይን ሻወር እየወሰድኩ ለመሄድ ወስኜ ነበር ነገር ግን እኔ የተቀመጥኩበት ቦታ እሱ ካለበት ፊተኛ ወንበር በስተመጨረሻ ነበር ጀርባውን እንጂ ፊቱን ሳላይ ጊቢ ደረስን ..... አንደ መስቀል ወፍ በአመት አንዴ ታይቶ እንደጠፋ ሰው ጊቢ ከገባን በኋላ አንድም ቀን መንገድ ላይ ተያይተን አናውቅም ይሃን ያህል ትልቅ ጊቢ ይመስል ማየት የፈለኩትን ሰው አለማየቴ የጊቢውን ምቀኝነት አደነኩ ..... ጊቢ ለመግባት ዘግይተን ስለነበር ትምህርቱ አናት በአናት የእንካ በእንካና የማግበስበስ ሆኖ ነበር ቀኑን ሙሉ ላይብረሪ ስናጠና ነው የምንውለው፡፡ ፈተና የደረሰ ሰሞን ላይብረሪ ሳጠና ድንገት ከጀርባዬ አንድ ነገር ተሰማኝ ምን እኔም አላቅም ዞር ስል ዜንጦው ልጅ እየገባ ነበር ደነገጥኩ ማደርገው ነገር ጠፋኝ ማንበብ አይበሉት ለ 30 ደቂቃ ወረቀቱን አገላብጣለው ነገር ግን እያነበብኩ አልነበረም : ... ወደ ፎቅ መውጫው ባለው አንደኛው ወንበር ስር ተቀምጧል በእኔ በስተቀኝ ትንሽ ዞር ብል ባየውት ነበር ነገር ግን ፊቴን ከእሱ አዙሬ ነው የተቀመጥኩት ውስጤ የሚነደውን እሳት ወደ ድፍረት ለውጬ ወደ ተቀመጠበት ወንበር ደብተሮቼን ይዤ አመራውና ከፊቱ አንዱን ወንበር ሳብ አድርጌ እሱ ብዙም ደንታ አልሰጠውም የለበስኩት አለባበስ ከሱ ዝነጣ ጋር ኦኦኦአ መነፃፀር የሚችል አይደለም ብዙ ለልብሴ ደንታ አልሰጥም የዛን ቀን ደግሞ ቅጥ ያጣ ተዝረክርኪያለው የለበስኩት ያረጀ ጥቁር ባለኮፊያ ጃኬት ነው ፊቴ ላይ ጢም ያለው ፂም አውሬ እንዳስመሰለኝ ተሰማኝ ቢሆንም ግን አጠገቡ ነኝ ‹ ሰላም ነው › ስል ተቀላቀልኩት ‹‹ ሰለም ..›› በስሱ ፈገግ ብሎ መለሰ አሁን ትኩረቱ እኔ ላይ ነው ‹‹ ሳይህ ደስ ስላልከኝ ነው ልተዋወቅህ ፈለኩና ተቀመጥኩ ..›› እንደ ጅል እውነቱን ተናገርኩ ፈገግ ብሎ ‹ ይቻላል ዮሐንስ እባላለው ጆ ልትለኝ ትችላልህ አንተስ ....›› ‹‹ ጆ ስላወኩህ ደስ ብሎኛል ሮቤል እባለላው ከየት ነህ ...›› ወይ ሮቤል ሌላው መንደር የለመድኩትን አጠያየቅ ጠየኩት አሁን የመጣበት ምን ያደርግልኛል ጅል ሆኖ ለመታየት ካልሆነ በቀር ‹‹ እኔ ከባህርዳር ነኝ አንተስ ...›› ጥናቱን ስላስቆምኩት ምንም አይነት ቅሬታ ነገር አላየውበትም ‹‹ እኔ ሃዋሳ ነኝ ›› ‹‹ ኦ የምር የሃዋሳ እና የሻሼ ልጆች በጣም ነው ደስ የሚሉኝ ...›› አሪፍ ሰው ለመሆን መሞከሩ ደስ ይላል ቀረብ ብዬ ሳየው ውበቱ ከርቀት ካየውት በተለየ ሁኔታ ጎልቶ ተመለከትኩት ‹‹ አመሰግናለው አንድ ቀን ባህርዳር መምጣት ፈልጋለው ›› ፈልጌ ማላቀውን ነገር ነገርኩት ቀጠል አድርጌም ‹‹ ስልክ እንለዋወጥ ›› ‹‹ እሺ ...› አሁንም ገዳይ ፈገግታውን እየመገበኝ ነበር ስልክ ተቀያይረን ትቼው ወጣው ...... ከተለየውት በኋላ ባደረኩት ነገር ገረመኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ወንድ በኣካል ፊቱ አድንቄ ስልክ ስቀበል ነገር ግን የጆ ነገር ገረመኝ በጅንጀና መንገድ እንደቀረብኩት የገመተ አይመስለኝም ወይም ደግሞ ገብቶት ላያሸማቅቀኝ እየሞከረ ነበር ብቻ የሆነው ሆኖ ስልኩን በስልኬ ይዤ ከላይብረሪ ወጣው ከሳምንት በኋላ በቴሌግራም እያወራን ለምን አልጋብዝህም ከተማ ወስጄ አልኩት ነገር ግን ፈተና ስለነበረበት እንደማይመቸው ነገረኝ 2 ጊዜ እንደሱ ሲለኝ እኔም ሰገጤነቴን ለመተው በማሰብ መደወል ሆነ በቴሌግራም እሱን ማውራት አቆምኩ ሀሙስ ማታ 12 ፡ 30 ሰዓት ( ያለወትሮው ጨለምለም ብሏል ) እራት በልቼ ከካፌ ከጓደኞቼ ጋር ስወጣ ስልኬ ጠራ ያየውት ነገር አስደነገጠኝ ጆ ነበር ከጓደኞቼ ወደኋላ ለየት አልኩና ስልኩን አነሳውት ‹‹ ሮቢ እንዴት ነህ ›› ‹‹ አለው ጆ ሰላም ነህ › ‹‹ አለን የት ሆነህ ነው ..›› ‹‹ ከካፌ እየወጣው ነው አንተስ ..› ‹‹ መስኪ ጋር ከጀለሶቼ ጋር ቡና እየጠጣው ነው ና ከፈለክ ....›› ‹‹ እሺ ምኑ ጋር ነው ...›› ቤተክርስቲያን ተሰባስበን እንሄዳለን ያልነውን ውሳኔ በአንዴ ረሳውት ለጋደኞቼ ሰው ላገኝ ነው አልኩና መስኪ የተባለውን ቡና ቤት መፈለግ ጀመርኩ ( ቡና ስላችሁ የጀበና ቡና ነው ) ጊቢው ፊት በርካታ ቡና ቤቶች አሉ የቱ እንደሆኑ ግራ ገባኝ እኔ ቡና ስለማልጠጣ የቱ ጋር እንዳለ አላቅም 3 ጊዜ እየደዋወልኩ ሳስቸግረው ያለውበት እንድቆም ነግሮኝ ወደኔ መጣ ... አዎ እንደተለመደው ነው አለባበሱ ቄንጠኛ ነው እንደደረስ ተቃቀፍን ቀጭን የመሰለኝ ጆ ደረቱ ላይ አስገብቶ እቅፍ ሲያደርገኝ ደረቱ ይሄን ያህል ሰፊ መሆኑን አላወኩም ነበር በጣም ደስ አለኝ አቅፎኝ ትንሽ ቢቆይ ደስ ባለኝ ነበር ነገር ግን ወዲያው ተላቀቅንን .. ‹‹ ምን አባህ ሆነህ ነው እዚ ድረስ የመጣኸው መስኪ እኮ ወዲያ ነው ...››› እኔ ካለውበት ቦታ በተቃራኒ አቅጣጫ እያመለከተ ተናገረ ሳቅ አልኩና ‹‹ ምን እኔ እኮ ቡና ምናመን አልጠጣም ለዛ አላወኩትም ›› መስኪ ጋር እንደደረስን 2 ጓደኞቹ ለመሄድ ተነሱ ተሰናብተውን ከእኛ እንደተለዩ እኔና ጆ ብቻ እዛ ቀረን ብዙ አላወራንም ስለ ክላስ አንዳንድ ነገሮች አወራን ከዛ የመግቢያ ሰዓት እንደደረስ ሂሳብ ከፈለና ተነስተን ወደ ጊቢ ማምራት ጀመርን እየተጨዋወትን ጊቢውን አልፈን ገባን ሳላውቀው የእኔ እጆች በእሱ እጆች ተነባብረው እየሳቅን መሄድ ጀመርን በጣም ደስ ብሎኛል ‹‹ አሁን ምን ልሰራ ነው ›› ጆ ነበር የጠየቀኝ ምናልባት ምንም ባልኩት ብዬ አሁን ላይ አስባለው እኔ ጅሉ ‹‹ አሁን ምሰራው አሳይመንት አለ እና እሱን ሰራለው ›› በእሺታ ራሱን ነቅነቅ አድርጎ በስፔስ በኩል ልንታጠፍ ስንል የጆ የክላስ ሜት የሆነችው ኤልሮኢ ( እኔም አውቃታለው ) ‹‹ እንዴ ጆ ና ሮቢ የት ተዋወቃችሁ ›› ስትል ከጀርባ ተጣራች ሰላም አላት እኔም አልኳት የሆነ የታወቀብኝ ነገር ያለ ይመስል ድንግጥ አልኩ ‹‹ ታውቂዋለሽ እንዴ ›› ‹‹ አዎ ቤተ ክርስቲያን ላይ እንተዋወቃለን ..›› 3 ታችንም ፈገግ አልን ተሰናብተናት ( እሱ 5 ኛ አመት ተማሪ እኔ ገና የ 1 ኛ አመት ነበርኩ በሰዓቱ ) ---- ሌላውን ቅያስ ይዘን ስንሄድ በድጋሚ እጄን በጆቹ ያዛቸው ‹‹ ድምፅ ደስ ይላል ታውቃለህ ›› አልኩት መሬት መሬት እያየው ‹‹ አውቃለው ›› አየውትና ፈገግ አልኩ ብታደንቁት አውቃለው ነው የሚላችሁ ባህሪው ነው በራስ መተማኑ ደስ ይላል ‹‹ ያንተም ደስ ይላል ....›› ‹‹ አረ ባክህ በስልክ ስሰማው ለራሴ ራሱ ያስጠላኛል ...›› ‹‹ እራስህን ማድነቅ መቻል አለብህ ደግሞ ውሸቴን አይደለም በስልክ ስሰማው ደስ የሚል ነው ...›› አለ እውነቱን ለመናገር እኔ የተቀዳ ድምፄን ስሰማው ሆነ በስልክ ችኩል ቀጭን የሚያስጠላ ድምፅ ነው ምሰማው ጆ ሲል ግን ደስ አለኝ ብቻ ስፔስ (LH) ድረስ ሸኘን ይሃን ሁሉ ሰዓት እጄን አለቀቀውም ነበር እርጋታ እና ደስታ ተሰምቶኝ ነበር I FEEL SECURE AROUND HIM THAT NIGHT እቅፍ አደረገኝ ይሃ ለመጨረሻም ለመጀመሪያም ጊዜ ከጆ ጋር DATE ይሁን ማላቀው ነገር የተከሰተበት ቀን ነው ከሰፊ ደረቱ መውጣት አልፈለኩም ነበር መልሼ ጠበቅ አድርጌ አቀፍኩት ጠረኑ ደስ ይል ነበር ‹‹ ደና ደር ሮቢ ›› ‹‹ ደናደር ጆ ›› ከፊት ያለውን ጨለማ መንገድ ይዤ ስሄድ ጆ ወደኋላ ተመለሰ፡፡ ከዛ በኋላ የምርቃት ክብረባዓላት ቀናቶቹ ላይ ጭብስ ብሎ ተገናኝተን ነበር አብሬው ጨብሼ በገገማው ብስመው ኖሮስ ስለማልጠጣ ሰክሬ ነው እል ነበር --- አላቅም ብቻ የዛን አመት ተመርቆ ወጣ እኔም ኦንላይ ሳየው እንዳላወራው ስልክ ቁጥሩን ደለትኩት እንግዲህ ከዛ በኋላ አይቼውም አናግሬውም አላቅም፡፡ A SHORT INTRO OR KICKER OF THE ARTICLE WILL GO HERE. THIS PART ACTS AS A BRIDGE BETWEEN THE HEADLINE AND THE ARTICLE ITSELF. የተመደብኩበት ዶርም ወደ ጦርነት ሜዳ እንዳይቀየር አቻችዬ እንዲቀጥል ያደረኩት እኔ ነኝ ማለት ማካበድ አይባልም 6 ታችንም የ 3 ኛ አመት ተማሪዎች ሆነናል ነገር ግን ጌች ካራሱ ፍላጎትና ምርጫ ውጪ ስለሌላው ምርጫ ምንም ግድ አይለውም ሁሉም ከእሱ ጋር መኖር አንፈልግም ዶርም መቀየር ነበር ሁላ ብለው ያውቃሉ አንዱን ነገር ልንገራችሁ አንዴ ጉንፋን ያዘውና ከሚተኛበት የላይኛው አልጋ ወርዶ ከመናፈጥ ሶፍት ሲያልቅበት በፊቱ ያለውን ጠረጴዛ ሙሉ በሙሉ ውሃ በውሃ አደረገው ይህን እያዩ የሰለቹት የዶርም ጓዶች ሁሌ እንደ ተጫቃጨኩት ነው፡፡ እኔ ስመጣ ደግሞ እንደልቆጣው ዶርም ስገባ ስርዓት ይዞ ነው ሚቀመጠው ለምን ብትሉ እጅግ ስለምንከባበር እና በብዙ ነገር እሱን ወክዬ ክላስ ወስጥ ስለመክራከርለት ይመስለኛል ምንም ይሁን ምን እኔን ማስቀየም ሆነ ማስቆጣት አይፈልግም ..... የሆነው ሆኖ ጌች ለእኔ ብቻ ነው የሚያቀው ተመቸህ አልተመቸህ ግድ የለውም ክላስ ወስጥ ሁሉ ከሁሉም ጋር እንደ ተኗቆረ ነው እዚ የደረስነው ... አንዴ ከዶርም ልጆች ጋር ዝም ብሎ ሲጣላ ግድ ቢለኝ ትንሽ ነገር ሳይበት ለሳምንት ዘጋውት ቢያየኝ አላወራው ሰላም አደርክ የለ በቃ ዝም ጭጭ፡፡ነገሩ ግራ ቢገባው አንድ ቀን ምሽት ሆን ብሎ ደወለልኝ እና ካፌ እንዳገኘው ቀጠረኝ ነገሩ ሁሉ ግራ ገባኝ ለሳምንት አላወራንም እቅዴ እንደተሳካ ገምቼ ደስ ብሎኝ ሄድኩኝ ከእኔ ጋር በፍቅር በመከባባር እንደሚኖር ከሌሎችም ጋር ቻል አድርጎ የራሱን ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ፍላጎት ተረድቶ በመቻቻል እንዲኖር ለማስተማር ነበር፡፡ከ 2 ሰዓት ጀምረን እስከ ምሽቱ 5 ተኩል ድረስ ያለማቋረጥ እኔን ካወቀ በኋላ በህይወቱ የመጡትን ለውጥ እየዘረዘረ ያስደራኝ ጀመር፡፡ የዛን ቀን ማታ አወቅነውም አላወቅነውም ትናንሽ ተግባራቶቻችን በሰው ህይወት ውስጥ ምን ያህል ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚችሉ የተገነዘብኩበት ነው ለሰው ሁሉ መልካም ማሰብ እና መመኘት ለውጥ የማምጫ መንገድ ነው፡፡ 8 ኛ ክፍል ሳለ ከአንድ የአጎቱ ልጅ ጋር በትንሽ ነገር ተጣልተው ቤተሰብ ሆነ ልጁ ሊታረቀው ቢሞክር በጭራሽ አሻፈረኝ ብሎ ለ 8 አመታት ዘግቶት ይኖር እንደነበር ነገረኝ ሰላምታ እንኳ ሲሰጠው ምለሽ አይሰጠውም ነበር ነገር ግን ከእኔ ጋር አንድ ዶርም ከሆንን በኋላ እኔ ለሰዎች ያለኝ መውደድ ለማላቃቸው እንኳ መንሰፍሰፌን እየታዘበ ራሱን ያይ ነበር፡፡ ጓደኛዬ የለ አንድ ሰው ከታመመ እና ማንም ከጎኑ ከሌለ እኔ አጠገቡ ነኝ፡፡ተቸግሮ ሳይ ካለኝ ሳይሆን ያለኝን ሁሉ የምሰጥ ነኝ፤ሰው ሲከፋው ሲጨነቅ ፊቱን አንብቤ የምጠይቅ ምን ሆንክ እያልኩ ሰውን ለመስማት ጆሮዬን የምሰጥ ነኝ፡፡በእኔ ዘንድ ቀለም የለ መልክ የለ መደብ የለ ሁሉም ለእኔ እኩል ናቸው ከተወሰኑት ጋር አብሬ ልውጣ ልግባ እንጂ ለሁሉም ጓደኛ ነበርኩ ይህን ሁሉ አይቶ ‹‹ ለማያቃቸው ሰዎች ዛሬ ላገኛቸው መልካም መሆን ከቻለ እኔ ለገዛ ስጋዬ ምን ሆኜ ነው ›› ብሎ ክረምቱን ወደቤት እንደተመለሰ ሄዶ ልጁን ይቅርታ ጠይቆ እንደተቀበለውና ሰላም እንደሆኑ ነገረኝ ... ምዕራፍ ሶስት እኔ እና ጌች 2012 ዓ ም ከሌሊቱ 9 ሰዓት A SHORT INTRO OR KICKER OF THE ARTICLE WILL GO HERE. THIS PART ACTS AS A BRIDGE BETWEEN THE HEADLINE AND THE ARTICLE ITSELF. እኔ ይሃን ማደርገው በሰዎች ዘንድ ተፅዕኖ ለመፍጠር ወይ መልካም ሆኖ ለመታየት ፡፡ለካ የእኔ ተራ ተግባራ ይህን ያህል ተፅዕኖ ያሳድራሉ ብዬ ገምቼ አላውቅም ነበር ምንም እንኳ በራሴ ውስጥ የመልካምነት ጥያቄ ያለ ቢሆንም ለሰው ግን መልካም ነበርኩ፡፡ ለሰው ለምን መኖር እንደተወ ሁሉ ሲያስረዳኝ እንባዬ መጣ ጓደኛው ውትድርና ሄዳለው ብሎ ሲነሳ ለብቻህም እዛ እንድትሄድ አልፈቅድልህም እኔም ወደ ምትሄድበት እከተልሃለው ብሎ የተነሳ ታማኝ ሰው አፍቃሪ ለሰው ኗሪ ነበር ነገር ግን ሁሉን ነገር አልፈው በሚሄዱበት ቀን ከቤተሰቡ ተደብቆ ልጁን በተባባሉት ቦታ ቢጠብቀው ቢጠብቀው ልጁ እሱን አጋፍጦ ዞር አለ ሳይመጣ ቀረ ያሳዝናል ውትድርና ለመሄድ ቀርቶ አስቦት ማያቀው ልጅ ለብቻው አይሄድም ባይሆን በሞት ውስጥ አብሬው ሄዳለው ብሎ የተነሳው ሰው ለሰው ያለውን እምነት ሸረሸረው መልማያቸው ቸር ሰው ነበር እና በቃ ሂድ ገና ልጅ ነህ አለው፡፡ መቼም የሰውን አሁን ላይ መጥፎ መሆን ለሰው ግድ የለሽ መሆኑን ነው ሰው የሚያየው እኔ ጌችን ከመጀመሪያውም ሳገኘውና ስተዋወቀው ሰው ያየበትን አላየውም በራሱ የሚተማመን ሰው ምን ይለኛል የማይል ጠንካራ ሰው እንጂ ለዛም ነው ሁሌ ስወደውና ሳከብረው ምኖረው፡፡ ነገር ግን እኔን ከተዋወቀ በኋላ ይሃ ሁሉ ለሰው ያለው አመለካካት በጥቂቱም ቢሆን እንደተስተካከል ነገረኝ አይ እኔን ብሎ መካሪ ለካ ሳላስበው ያደረኩትን አድርጊያለው ከዛ በኋላ ሰው የፈለገ ቢል እሱን አልቃወመውም ነበር፡፡ መጋቢት 9 በዚች እለት በጣም ደክሞኝ ስለነበር በጊዜ ነበር የተኛውት ለሊቱን ሙሉ በመብረቅ ብልጭታ ከባድ ዶቭ ዝናብ እንደዘነበ ራሱ በንጋታው ከዶርም ስወጣ ነበር ያወኩት ጌች አንዳንዴ ለብቻው ሲተኛ ስለሚቃዥ እኔ ጋር እየመጣ ይተኛ ነበር ሰላም ይሰማኛል ካንተ ጋር ስተኛ ይላል፡፡ የዛን ቀን ግን እኔ ቶሎ ስለተኛው እኔ ጋር ሊተኛ እንደመጣ አላወኩም ነበር ከሌሊት 9 ሰዓት ያዳፋኝ እንቅልፍ ንቅል ብሎ ከላዬ በነነ ከጀርባዬ ጌች ተጋድሟል ምን እንደ ሆንኩ አላቅም ሞቅ አለኝ ይሃ ነገር ያስፈለገኝ መሰለኝ ... ለረዥም ደቂቃዎች ተገላበጥኩ መልሶ እንቅልፍ እንዲወስደኝ ጨፈንኩ ግን ወፍ እንቅልፍ በፓንት ካለው ጌች ጋር አጋልጦኝ ነጉዷል ማደርገው ግራ ገባኝ እኔም በፓንት ነበርኩ ጥብቆ ፓንት ነው ያደረኩት ( እንደዚህ አይነት ፓንቶች ከብዙ ጉድ ይታደጋሉ የሚያቅ ያውቃል ) ጌች በተቃራኒው በቦክሰር ነው ያለው ቂ * ን ወደ ቁ * ው ስር ሆን ብዬ ሸጎጥ አደረኩት እንደሚገላበጥ ሰው እያስመሰልኩ እፋተገው ገባው ፡፡ ብዙም አልቆየም አንድ ነገር ጠንከር እያለ ወደኔ ሲወጠር ተሰማኝ የልብ የልብ ተሰማኝ እሱ አሁንም እንደጨፈነ ነው እኔ ፊቴን ወደ እሱ አዙሬ ቂ * ን ብቻ አሸዋለው ለረዥም ሰዓት እንደዛ ሳደርግ ፓንቴ እየረጠበ መጣ ከጌች የሚወጣው ዝልግልግ ፈሳሽ እኔንም እያረጠበኝ ነበር ምንም አላልኩም ፊቴን ወደሱ አዞርኩ እጄን ቀስ ብዬ ወደ ቦክሰሩ ከተትኩ፡፡የወንድ ብልት ስጨብጥ ይህ ሁለተኛዬ ነው፡፡ ትልቀቱ እጄ ሲጨብጠው ሚጥጥዬ እጅ ያለኝ እስኪመስል ዋጠው ጭገሩን እያፋተኩ ቁላውን ወደላይ ወደታች ማድረግ ጀመርኩ በጣም ሞቅ ሲለኝ ወደ ላዩ ወጣው ማላቀው ሰይጣናዊ ኃይል መሆን አለበት ልስመው ወደ ከንፈሩ ሄድኩ ፊቱን ዞር አደረገብኝ ድንግጥ አልኩና ከላዩ ላይ ወረድኩ ልቤ ተቀዶ ሊወጣ በፍጥነት መምታት ጀመረ አተነፋፈሴም በጣም ጨመረ .. እውነት ለመናገር ጌችን በዛ አይነት ነገር አንድም ቀን አስቤው አላውቅም ብቻ የዛን ቀን የወሲብ ቅሌት የማገናዘብ ችሎታዬን ውጦ ገሎት ነበር :: ነገ ሲነጋ ምን ልሆን ነው ቶሎ ዶርም ለመቀየር ማሰብ ጀመርኩ ግራ ገባኝ ላብ በላብ ሆንኩ እንደዛ እንደታላቅ ሰው ያከብረኝ የነበረው ሰው አሁን መሳለቂያ ሊያደርገኝ ነው ለሰው እንደማያወራ አውቃለው ነገር ግን በፊቱ የተዋረድኩና የተናኩ መሆን አሳፈረኝ ሞቴን አስመኘኝ ፡፡ ብዙ ጊዜ ስለሚያመኝ በሱ አመሃኝቼ ከጊቢ መልቀቂያ ሞልቼ ሁሉ ለመሄድ አሰብኩ በቃ ያለኝ አማራጭ ይኸው ነው አባቴ የፈለገውን ይበል ኡኡአ ብዬ ወደቤቴ መመለስ አለብኝ ጀርባዬን ለጌች ሰጥቼ እኔ በጭንቀት አለም ነጎድኩ በአልጋው ጠርዝ ላይ ብቻ ሆንኩ :: ከሱ እየራኩ ድንገት እጁን ወደኔ ሰደደና እቅፍ አደረገኝ የባሰ አታምጣ እየሆነ ያለው ግራ ገባኝ ጌች ይሄ ቁ * ው ሴቶች የሚያሳብድ እንደሆነ አውቃለው በየቀኑ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ነው እያደረገ ሚመጣው እልም ያለ የወሲብ ተጫዋች ነው አሁንም ቀስ ብሎ ቀረበኝ እኔም መልሼ ያሸሸውትን ቂ * ን ወደ ቁ * ው ሸሸኩት መተሸሸት ጀመርን እሱም ግን የደነገጠ መሰለኝ ዞረ እኔ ግን ቀጠልኩ በተራዬ ቁ * ዬን ቂ * ላይ አድርጌ አፋትገው ገባው ...‹‹ ሮቤል በቃህ ታፍርበታለህ ..›› የራሴ አዕምሮ ተቆጣኝ እኔም ዞርኩና ጀርባ ከጀርባ ተጋደምን እንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር 11 ሰዓት ሲሆን ከእንቅልፉ ተነሳና ሻወር ለመውሰድ እንደ ሁል ጊዜ ልማዱ ወጣ ....... አሁን ምን ማድረግ አለብኝ ምን የሚሉት ቅሌት ነው ያደረኩት ሴክስ አድርጌ ስለማላቅ ከዛ በፊት አምሮት አናቴ ላይ እየወጣ መሆን አለበት አዎ አንዴ ለመሞከር ከመሰሌ ጋር ተቀጣጥሬ እንቢ ብዬ ተመልሻለው ከዚ ምሽት ውጪ የወንድ ብልት የነካውት አንዴ ነው እሱም የመሰሌን ነው ግን ያለወሲብ ተመለስኩ ወይኔ ጉዴ አሁን ስናገር ቀላል ይመስላል የዛን ቀን አሳሬን በላው ታጥቦ መጣ ለባበሰና በራሱ አልጋ ላይ ወቶ ተጠቀለለ እኔ የተኛው ይመስል ተደብቄ አየዋለው .... የቁርስ ሰዓት እንደ ደረሰ ጓዶቼን በቶሎ ቀስቅሼ ከዛ ዶርም መውጣት ነበር የታየኝ .... ከቁርስ በኋላ ለአባቴ ደውዬ መምጣት እንደ ምፈልግ ነገርኩ አዕምሮዬ ትክክል እንዳልሆነ ነገርኩት ተከራከረኝ አንድ አመት ለሰይጣን ልትሰጥ ነው አለኝ ‹‹ ይብላው ከፈለገ እኔ መምጣት ነው ምፈልገው በቃ ብር አስገባልኝ ..›› ብዬ ስልኩን ዘጋው ያለብኝን ዲፕረሽን ስለሚያቅ እሺ አለና ብር አስገባልኝ በቃ አሁን መልቀቂያ መሙላት ነው ያለብኝ አልኩ ........... ፈጣሪ ሲወዳችሁ እንደ እኔ ነው በንጋታው አዲስ ማስታወቂያ ተለጥፎ አየን ‹‹ ለ 15 ቀናት በኮረና ምክንያት ወደቤታችሁ እንድትሄዱ መንግስት ባወጣው መንገድ ከነገ ጀምሮ ትራንስፖርት ይዘጋጅላችኋል፡፡ ›› ማየውን ማመን አልቻልኩም ደስ አለኝ ዶርም ስገባ አንዴም ከጌች ጋር አይን ለአይን አልተያየንም እንደ ወትሮ ቢሆንም እንላፋ ነበር ዛሬ ግን ሌላ ቀን ነው 15 ቀኑ 1 አመት ሙሉ አለያየን ወደ ጊቢ ከመመለሴ በፊት ለኮረና እንደገባው የይቅርታ ቴክስት ላኩለት እሱም ችግር እንደሌለው ነገረኝ ከዛ ቴክስት ውጪ ስለዛ ምሽት እሱም እኔም አውርተንበት አናውቅም አሁን ሁለታችንም ተመርቀን ከወጣን በኋላ እንደዋወላለን አንፎጋገራለን ግን ይሃን ምሽት ከነመፈጠሩ ለመርሳት ወስነን የተስማማን ይመስል አንስተነው አናውቅም፡፡ A SHORT INTRO OR KICKER OF THE ARTICLE WILL GO HERE. THIS PART ACTS AS A BRIDGE BETWEEN THE HEADLINE AND THE ARTICLE ITSELF. ሰላም አንገብጋቢ ነበር በጊቢ ቆይታዬ ም / ክ ያለውበት ስፍራ የሽፍቶችና የፖለቲከኛ ፅንፈኞች የሚገዙበት ስፍራ በመሆኑ ለበርካታ ወራት ከጊቢ ይልቅ ቤት የቆየውባቸው ጊዜያት ይበዛሉ፡፡ይህም ይሃ አይነት አመት ነው በየ 15 ቀኑ ከ 900 ኪሜ በላይ እየደጋጋምኩ ምጓዝበት፡፡ ብቻዬን ነበርኩ ማንንም ለመጠበቅ ልቤ አልፈቀደም እየሆነ ባለው ዝብርቅርቅታ ስለተናደድኩ ቶሎ ጊቢ መመለስ ነበረብኝ ብዬ ከጓደኞቼ ተለይቼ ነው የወጣውት፡፡ በጠዋት ሊሸኙኝ ከመጡት ወንድሜ እና እናቴ ጋር መነሃሪያ ደርሻለው እያቆራረጥኩ ለመሄድ ስላሰብኩ ቀጣዩ መዳረሻዬ ዝዋይ ነበር መኪና እስኪወጣ እየጠበኩ ሳለ አንድ ሞተር እየከነፈ እኛ ወዳለንበት ስፍራ መጣ፡፡ ከፊት ያለው ተለቅ ያለ ሰው አይደለም ትኩረቴን የሳበው ከጀርባ አፈናጥሮ ላመጣው ልጅ አባት እንደሆነ ገምታለው .... አነስ ያለ የጀርባ ቦርሳ የያዘ አጠር ያለ ለአለባበሱ ግድ ያለው ወጣት ወረደ በኮፊያ በተሸፈነ ማስክ ያጠለቀውን ፊቱን ላየው ባልችልም ግን ከቆምኩበት አንድ ሁለት ሜትር ራቅ ብሎ ሞተሩ አጠገብ ቆሟል፡፡ አንዳንዶች ሴሰኛ መስላቸው ይሆናል ያየውትን የማድነቅ አባዜ ስላላብኝ ውበት አደንቃው ነገር ግን አብሬው ለመተኛት ወይም ሌላ ነገር አላስብም ሲበዛ ደግሞ መራጭ ነኝ እይታዬ ውስጥ የገቡት ሁሉ የተመረጡ ናቸው ( በንቀት መልክ አላልኩትም ሁሉም ለራሱ በራሱ መንገድ ቆንጆ ነው ) ከስንት አንዴም ስለሆነ ሳያቸው ላውቃቸው ልቀርባቸውና ጓደኛ ላደርጋቸው እመኛለው ..... ብዙም አልቆየንም አንድ መኪና መቶ የተሰበሰብነውን መንገደኞች አፋፍሶ ጨመረን እሱ ወደሌላ ቦታ እንደሚጓዝ እየገመትኩ አንዴ ተመለከትኩትና ገባው የእኔን መግባት ተከትሎ ሰተት ብሎ ወደገባውበት መኪና ገባ ቦታ እየሞላ ነበር ስለዚህ ያለውበት የመጨረሻ መቀመጫ ከጥጉ ላይ ተነሳውና ተሸጋሸጉ እንደ ወትሮው ቢሆን መስኮቷን ይዤ ሙጥኝ ነው ምለው .. እሱ መጣና ተቀላቀለኝ ..... መንገዱ ጀምሯል ሙዚቃው ይዜማል እሱ ኢርፎኑን ለራሱ ደቅኖ በራሱ ዓለም ቦርሳው ላይ ደገፍ ብሏል እኔም በተጣበበና በማይመች ቦታ ለብቻዬ ከራሴ ጋር ተፋጠጥኩ ... ዝዋይ ልንደርስ ስንል ከተኛበት ብድግ ብሎ አከባቢውን መቃኘት ጀመረ እኔ ምንም አላወራም ብቻ ከምላችሁ በላይ የማይመች አቀማማጥ ነው የተቀመጥኩት .... እንደማስታውሰው እስከ ዝዋይ ባለን ጉዞ አንዴ ያወራነው ነገር አለ ነገር አለ ግን አላስታውስም .... እንደ ደረስን ወረድን እና መሯሯጥ ጀመርን ልጁ ባንዴ ካለውበት ቦታ ጥፍት አለ ትንሽ ቃኘት ቃኘት አደረኩ ወፍ የለም ምን ሰለበው ብቻ ቀጣዩን መኪና ለመያዝ የቡታጅራ ተረኛ መጠያየቅ ጀመርኩ አንድ ሰው ሲጎለው ቀድሞኝ ሰው ገባበትና አመለጠኝ ቀጣዩም ምስጋና ለሚያጭበረብሩት ሀይሩፍ መኪና አግኝቼ ዘው ብዬ ገባው ቁርስ የለ ምን ምናልባት ልጁ ቁርሱን ሊበላ ሄዶ ይሆናል ወይም መድረሻው እዚው ሆኖ ይሆናል ......... እሱን እያሰብኩ ሳላ ሮጦ ወደመኪናው ገባ አሁንም ክፍቱ እኔ ያለውበት ቦታ ነው ሳላውቀው ፈገግ አልኩ መቶ አጠገቤ ተቀመጠ አሁን ነቃ ብሏል ምዕራፍ አራት እኔ ና ዩኑስ ‹‹ አይ አይ እንጂ ሌላ ምን እላላው !›› A SHORT INTRO OR KICKER OF THE ARTICLE WILL GO HERE. THIS PART ACTS AS A BRIDGE BETWEEN THE HEADLINE AND THE ARTICLE ITSELF. ‹‹ ምን የሚሉት ነው ቅድምም መጨረሻ አሁንም ....›› ስል ፈገግታን አክዬ ወሬ ለመጀመር ሞከርኩ እሱም በተራው ሰልክክ ብለው የተደረደሩ ጥርሶቹን አሳየኝ ፈገግ በሚልበት ጊዜ ስርጉድ ብለው የሚገቡት ፊቱ ላይ ያሉት ዲፕሎች ደስ ይላሉ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው የወንድ ዲምፕላም ሳይ ግን ውበቱን ጨምረውታል ፡፡ ‹‹ ምን ታረገዋለህ በዛ ላይ እያጨቁን ....›› ለካ የቦታው መጥበብ ለኔ ብቻ አይደለም ‹‹ መቼም እኔ አይደለውም አንድ ቁጥር ቦታ አይዝም ...›› አሁንም ፈገግ አልን ወሬያችን ተጀመረ ‹‹ ሮቤል እባላለው ›› ‹‹ ዩኑስ እባላለው ›› ስሙ ሰምቼው ስለማላውቅ ‹‹ ምን ማለት ነው ›› ይህ የተለመደ ጥያቄዬ ነው የስም ትርጉም ማወቅ ራስን ከመግለፅ ጋር አገናኘዋለው ነገር ግን ዩሱፍ የስሙን ትርጓሜ ይወቀው አይወቀው እንጃ ‹‹ በናንተ ዮናስ ማለት ነው ›› ሲል ከስሜ በመነሳት ሃይማኖቴን በመገመት ተናገረ .... ትንሽ ቆም እያደረግን መልሰን ወሬ ሀሳብ ሲመጣልን ማውራት ጀመርን ‹‹ ወልቂጤ እየሄድክ ነው ..›› ሲል መድረሻዬን ጠየቀ ‹‹ ኖ ኖ አይደለም አንተስ ..›› ‹‹ ጅማ ነኝ የጊቢ ተማሪ ...›› ‹‹ ኦ እኔም እኮ ***-** ተማሪ ነኝ ምን ብሬክ መተህ ነው ....›› ‹‹ አዎ ለበኣል መጥቼ .....›› ‹‹ ምን እኛማ በኣሉም የለም ሰላም ስላልሆነ ገባን በዛው አክብረን እየመጣን ነው አንተ ግን ፋሲካ ....›› ስል የራሱን የቀደመ ታክቲክ ተጠቀምኩ ፈገግ ብሎ ‹‹ ምን ባክህ እድሏን ተጠቅሜ ልመለስ ብዬ ነው ›› ለብልሃቱ ፈገግታዬን አደልኩ አላቅም ስስቅ የሰዎች ፈገግታ እኔ ላይ እንደሚፈጥረው ያለ ተፅዕኖ ልፍጠር አልፍጠር አላቅም ብቻ መግባቢያ እና ቀለል ያልኩ ሰው ለመምሰል እጠቀመዋለው ... ‹‹ እና የት ነው የተማርከው ሻሸመኔ ...›› ስል በደንብ ወሬውን ለማስረዘም ጥያቄን ፈጠርኩ ‹‹ ኦ ኖ መጀመሪያሀዋሳ ነበርን 1 አመት ነው ፒፒ የተማርኩት 12 ኛ አንተስ ...›› ‹‹ እኔ ሉሲ ነበር የጨረስኩት ....›› ከዚ በመከተል እስከ ቡታጅራ ስለጊቢ የመምህራን አዛነት አለመመቸት ስለካፌው ስለትምህርቱ ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ስንቀባጥር ቡታጅራ ደረስን አዲስ መኪና ተሳፈርን እንዲው ስናወራ ወልቂጤ ደረስን ምሳ በልተን መነሳት ስላለብን እንደደረስን የጅማ መኪና አግኝተን ቦታ ያዝን እኔ ሻንጣ ይዜ ስነበር እሱን ከላይ አስጭኜ ዞር ስል ዩኑስ በአከባቢው የለም አይ ምሳ አብረን እንበላላን ብዬ አስቤ ነበር አይ ህልም ብቻ ነው የኔ ነገር ... ብዘም እንጀራ ነገር ስላስፈለገኝ የሚጠጣ እና የሚበሉ ኩኪስ ብስኩት ለኔም ለሱም ገዛውና እስኪመጣ እጠብቀው ጀመረ ጃኬቱ እኔ ከተቀመጥኩበት አጠገብ ተዘርግቷል አንድ 20-30 ደቂቃ ቆይቶ መኪናው ሲሞላ ከተፍ አለ ለ 4 ኛ ዙር ጎን ለጎን ጉዞ ተጀመረ ‹‹ ጠፋህ አኮ ይሄን ገዝቼ ነበር እንካ ...›› ስል የገዛውለትን የድርሻውን አወጣውና ከቦርሳዬ እጄን ዘረጋው A SHORT INTRO OR KICKER OF THE ARTICLE WILL GO HERE. THIS PART ACTS AS A BRIDGE BETWEEN THE HEADLINE AND THE ARTICLE ITSELF. ‹‹ ወይኔ እኔ እኮ ምሳ በላው የሙስሊም ስጋ ስለማትበሉ ....›› ጅልነቴ ገረመኝ እሱ ደግሞ ጥሎኝ በመሄዱ ጥፋት እንደተሰማው ለማስመሰል ይሞክራል አያቀኝ ነገር ለምን ይጠብቀኛል ለነገሩ .... ከዚ በኋላ ያለው መንገድ እስከአሁን ከመጣነው አቆራራጭ መንገዶች የበለጠ አድካሚ እና ረዥም ነው ጊቤ በረሃ አለ ይሃ የተፈነቃቀለ አስፓልት አይሉት እንደ ወተት ሊንጠን ነው ምሳ ሰዓትም በመሆኑ ሐሩር ፀሐይ በላብ እየጠመቀን ጉዞ ጀመርን ብዙም አላወራንም አሁን የዝምታ ጊዜ ነው ምሳ ተላያይተን ስለበላን ሳይሆን ስለ ደከመን ነው አልፎ አልፎ እንቅልፍ ካንገላጀጀው አይናችን ገለጥ ስናደርግ ፈገግታ አየተመጋገብን ጥቂት ነገሮች እናወራለን መንገዱ ብዙ አይርቅም ግን አድካሚ ነው 10 ሰዓት እንዳለፈ ጅማ ከተማ ገባን ከዚ ቀደም ቢሆን ከዚህም አምሽቼ ልገባ እችላለው፡፡ ያለኝ አማረጭ አልጋ ከመነሃሪው አከባቢ መያዝ ነበር እንደ ወረድን ‹‹ በል በቃ ሰላም ሁን .....›› ስል የስንብት ቃል አወጣው አብሬው ለነበረኝ ቆይታ አመስጋኝ ነኝ ምናልባት ስልክ ስለተቃያየርን ሰፈር አንድ ስለሆንን ቤት ስንመለስ ደውልለታለው ብዬ የራሴን ማደሪያ ለመፈለግ ነበር፡፡ ‹‹ ምን አሰብክ የት ነው ምትሆነው ....›› ለጥያቄዬ ምላሽ ሳይሆን ጥያቄን መለስኝ ‹‹ አልጋ ይዛለው ነገ በጠዋት እሳፈራለው ›› ‹‹ ኖ ኖ እኔ ጋር ጊቢ ግባና እደር እኔ በጠዋት ሸኝሃለው ...›› ትንሽ ከሱ ጋር ጊዜ ባሳልፍ ደስ ይለኛል አሁን ምሽቱን ሙሉ ከሱ ጋር ልሆን ነው ደስ አለኝ በዛ ላይ ጅማ ቴክኖ ጊቢውን ላይ ነው ‹‹ የምር እንዴ ዘበኞችስ ማለቴ መታወቂያ ምናምን .....›› ምን የሚሉት ነው ምናልባት እሱ በይሉኝታ ጠይቆኝ ቢሆንስ ባንዴ ሳላቅማማ እሺ አበስ ገበርኩ እንደ ሚል ‹‹ ባክ ጣጣ የለውም ጀለሶች ያመጣሉ ..›› ተያይዘን ጅማ ጊቢ መጓዝ ጀመርን ጓደኞቹ ቀደም ብለው በር ላይ ጠበቁንና መታወቂያ ሰጡኝ ላፕቶፔን በስሙ አስመዝግቦ እኔ ቀደም ብዬ ገባው ዘበኛ ሳጭበረብር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው አንዱ መረበሼን አይቶ ‹‹ አይዞሽ ነቄ አይሉም ዝም ብለው እኮ ነው ...›› ዩኑስ እና ሌላኛው ከጀርባቸን እየተከተሉን ነበር .... ለአፍታ ጅማ ጊቢን ማድነቅ ጀመርኩ በለው እኔ የት ነው ያለውት ጊቢ ነው ወይስ ወይ ጉድ ... የተማርኩበት ጊቢ ስለ ሰዎች እንጂ ሌላውን ነገር አስቦ ለማመስገን ፍቃድ አይሰጥም .... ዶርም እንደ ገባው ሁሉም ‹‹ ፒስ ነው ማን ...›› በለው መቀደድ ወሬኛ እና ጡዘተኛ እስኪመስሉ የአወራር ዘዬአቸው አስቸገረኝ ... በዛ ላይ ዶርሙ ዶርም ሳይሆን የቆሻሻ መጣያ ነው ሚመስለው በፈጣሪ ጉድ ምን ውስጥ ነው ያለውት እሱን ብዬ ምን ውስጥ መጣው ስለ ተከታተይ ፊልም መቀባጠር ጀመሩ ሁሉንም አስተዋወቀኝ ተጫዋችና ቀለል ያሉ ቢሆኑም ከእኔ ባህሪ ጋር አይገጥሙም ፡፡ የዩሱፍ ሎከር ተከፈተ ውስጡ ያሉት የዶዶራንት እና የቅባቶች ብዛት ፊቴ ልብሱን እያወላለቀ በቦክሰሩ ቁጭ አለ A SHORT INTRO OR KICKER OF THE ARTICLE WILL GO HERE. THIS PART ACTS AS A BRIDGE BETWEEN THE HEADLINE AND THE ARTICLE ITSELF. ‹‹ ውሃ አለች እንዴ ...›› ሲል ዶርም ውስጥ ካሉት ከለፊላፊዎች አንዱን ጠየቀው እንደሌለ ሲነግረው ‹‹ ሺት ማታ ቺኳን ሳልታጠብ ላገኛት ነው እንዴ .....›› ከገባው ያወራውት 3 ወይም 4 ነገር ብቻ ቢሆን ነው ወይ ምን አንቀልቅሎኝ መጣው ጨነቀኝ ምቾት አልተሰማኝም እንደገና ፍሬሽ የሆንኩ ያህል ጦጣ ሆንኩ ለነገሩ ፍሬሽ ሳለው ራሱ እንደዚህ ባይተዋርነት አልተሰማኝም ምናልባት ያለግዛቴ ስለተገኘው ይሆናል ... እንግዲህ ይህ ነው ምቾት በማንመደብብት ስፍራ አይገኝም፡፡ ፊልም ላይ የሚከራከሩት ከሚከራከሩለት ፊልም የቱ የተሸለ እንደሆነ ሃሳብ እንድሰጥ ጠየቁኝ ሳልመልስላቸው ክርክራቸውን ቀጠሉ ለነገሩ ያሉትን ፊልም እንደኔ ከሆነ 2 ቱም ያስጠላሉ በባህሪዬ ዶርም ስኖር በ 3 አመት ቆየታዬ ዶርሜ ቆሽሾ አያቅም ሁሌ ማፀዳው እኔው ነኝ ምክንያቱም ለአከባቢያችን ያለን አስተዋፆ እኛ አከባቢያችንን እንዴት መቅረፅ እንደምንፈለግ የሚያሳይ ነው እኔን ለማወቅ ሶስት ነገሮች ማየት አለባችሁ ሎከሬን ( ሁሌ የተቆለፈ ነው ) ዶርሜን ( ሁሌ ሲቆሽሽ በየለቱ እንዳፀዳውት ነው ) እና የሎከሬን ውስጥ ( ሁሌ በአግባብነት ስርዓት ይዘው እንደ ተደረደሩ ነው ) ሁሉም ውስጥ እኔነቴን እና የአመለካከቴ መገለጫዎች ናቸው በተቃራኒው ይህ ዶርም አስቀያሚ ነው የቆሸሸ ነው ..... እንዴት እዚ ውስጥ ላድር ነው ሁሉም ወጣ ወጣ እንዳሉ ዩኑስም መጣው ብሎ ትቶኝ ወጣ ዶርም ውስጥ እኔ ብቻ ቀረው ያለኝ አማራጭ ዶርሙን ማፅዳተ ነው ስለዚ ከላይ የተከማቸውን ፌስታሎች በመልቀም ጀመርኩ ዶረሙ መጥረጊያ እንኳ የለውም አሁን ከላይ ከላይ የሚታየውን ላንሳና ሌላውን ለበኋላ .. ብዙም አልቆየውም ዋቆ ወደ ውስጥ ሲገባ ባየው ነገር ተደናግጦ ፡፡ ‹‹ አረ በጌታ ምን ሆነሃል እኛ እናፀዳዋለን ›› ሲል ይከላከለኝ ጀመር እኔም ደረቅ አልሆንኩም ወጥቼ በለሊት እንደምሄድ ለራሴ ነገርኩና ተቀመጥኩ ..... ይህ ቀን በሂወቴ ምን አስተማረኝ እኔም አላቅም በትክክል ግን ስሜቴን መከተል እንዳልነበረብኝ ይህን ታሪክ መልሼ ስፅፈው ነው የተረዳውት .... ከዩኑስ ጋር እራት በላን ጋባዥ እሱ ነበር ከዛ ለሊቱን ሙሉ ዶርም ውስጥ ለብቻዬ ... ቆሻሻ ላይ እንዳፈጠጥኩ ቱሃን ከላዬ እንደ ዝናብ ነው የተንጠባጠበው ብቻ ምን ልበላችሁ አንድ ምሽት ከሱ ጋር እያወራው አመሻለው ያልኩት ሰውዬ እሱ ሴት ሊያጫውት ልሊቱን ሙሉ ውጪ 7 ሰዓት ሲሆን መተኛት በማልፈልገው የሰው አልጋ ላይ ስመጣ አለማሰቤ ራሱ ለራሴ ገረመኝ ምለብሰው ነገር አልነበረም ብቻ አቀማመጤ አልጋውን በመፀየፍ እንደሆን ያሳውቃል አሳይመንት ብለው ሁሉም ውጪ ናቸው ዋቆ ብቻ በቁም ነገር ጥቂት አጫውቶኝ ለአሳይመንቱ አመሻሽ ላይ ወጣ ... ጠዋት በለሊት እንደተነሳወው አንድ ሰው ጠቅልዬ የገፋውትን ብርድ ልብስ አልብሶኝ ነበር መቼም ዩኑስ ወይም ዋቆ ከሁለቱ ውጪ ሌሎቹ ቀልብም ያላቸው አይመስሉም ብቻ ... ዩኑስ ሲሰራ ያደረው ነገር በፈለኩት ሰዓት ከኣልጋ እንዳይነሳ ከልክሎታል አዳር ሙሉ ሲዘል ነው ያደረው መሰለኝ ቀስቀስ ባደርግው ትንሽ ቆይ እያለ 12 ሰዓት የተነሳውት ሰውዬ 3 ሰዓት ከጂማ ጊቢ ያለኝን ልብስ በሙሉ ደራርቤ ለብሼ ... ኦፊስ ሄጄ በሴቶች ፊት ለማውለቅ ተገድጄ በሰላም ከጊቢው ለመውጣት ችያለው ... አሁን ላይ ሰፈር ውስጥ እንተያያለን ሰላምታ እንቀያየራለን ይሃ የትም የማይደርስ ጅል ስሜቴ ሲያየው አየር ላይ አሁንም ይደንሳል፡፡ A SHORT INTRO OR KICKER OF THE ARTICLE WILL GO HERE. THIS PART ACTS AS A BRIDGE BETWEEN THE HEADLINE AND THE ARTICLE ITSELF. መቼም ለሰው መልክ መለያው አመለካከቱን አስቀድመው ከሚቀርፁት እንደ ቤተሰብ ያለ ማንም የለም የእኔም ቤተሰብ ድንቅ ነበሩ ፍፁም አይደለንም ፍፁም የሆነ ደስታም የለንም ግን አንዳችን ላንዳችን ሟች ነን፡፡ቤተሰብ የተሸለ የተከበረ የተወደደ ልጅ ሲኖራቸው የሚኮሩበት ልጅ ሲያገኙ አቤት ልጃቸው የሚባል ልጅ በቤታቸው ሲኖር እጅግ ደስ እንደሚሰኙ ሁሉችንም እናውቃለን፡፡እኔም ለቤተሰቤ ታዛዥ፤ወላጆቼን አክባሪ፤ሃላፊነት ተቀባይ የቤት ስራ ውስጥ ድርሻዬን የምወጣ በትምህርቴ ጎበዝ በሰፈር ስርዓቴ የተመሰከረልኝ ወላጆች ልጆቻችንን ምከር ብለው ወደ እኔ የሚልኩ አይነት ልጅ ሆኜ በብዙ ቤተሰቤን ለማኩራት የሞከርኩ ሰው ነኝ ላኮራቸው ብዬ ሳይሆን እንዲው በእኔ ውስጥ የሚፈስ ነበር፡፡ እንግዲ ጊቢ ገብቼ ቤተሰቤን በትምህርቴም እያኮራው ያለው የማዕረግ ተመራቂ ሆኜ ለመብቃት የቻልኩ ልጃቸው ነኝ ወንድም እህቶቼም እንደዛው ከእኔ የተሸሉ እንጂ ያነሱ አልነበሩም ፈጣሪ ወላጆቼን በልጅ ባርኳቸዋል አስተዳዳግስ እንደ እነሱ ነው ነው የሚባልላቸው፡፡ምንም የምንዋደድ ብንሆንም ግን እኔ ማልፍበትን ፈተና ልነግራቸው አስቤም አቅጄም አላቅም ነበር ምክንያቱም በእኔ ላይ ያላቸውን እያንዳንዱን እምነት እና ኩራት መሻር ሊሆን ስለሚችል ጭንቀቴን ለራሴ ፈተናዬንም ለግሌ ይዤ አመታት ዘልቂያለው ነገር ግን ራሴን ለመርዳት በምንም አልቻልኩም ነበር ከፍተኛ ጭንቀት እና ድብርት ነበረብኝ፡፡ ሜሪ እኔ ከምኖርበት አከባቢ ብዙ ርቃ አትኖር ነበር፡፡ጎረቤታም ከተሞች ናቸው ያለንበት እና አንድ ቀን ደውላ በሰፊው አስደነገጠችኝ እኔ ወደምኖርበት ከተማ ለአንድ ጉዳይ ልትመጣ እንደሆን ስነግረኝ ቤት መታ ወላጆቼን እንድትተዋወቅ ነገርኳት መልሷ ግን ልቤን አሸበረው ‹‹ ከመጣውማ ለእናትህ ሁሉን ነገር ነግሬ እርዳታ እንድታገኝ ነው ማደርገው ›› ስትልኝ ልቤ ያለልክ ነበር የመታው ወይ እዳ እኔ ለእሷ እንጂ ለቤተሰቤ እንድትናገር አይደለም ሚስጥሬን ሸክሜን ያጋራዋት፡፡ብቻ ቆጣ ብዬ ይሃን ማድረግ እንደማትችል ተናገርኳት፡፡ እሷም ቦታዋ እንዳልሆነ ስላወቀች ዝም አለች ያው ቤቴም እንድትመጣ ግብዣዬን አነሳው፡፡መቼም የምናልፍበትን ችግር ቤተሰባችን ከራሳችን ቢሰማው እንጂ ከማያቁት ባዳ መስማት ልባቸውን በሚስማር መውጋት ነው ነገሩ አስጨነቀኝ መናገር እንዳለብኝ አሰብኩ ግን ምን ተብሎ የነገራል ወንድ ሆኜ ከወንድ ፍቅር ይይዘኛል ሴትን መውደድ በሚገባኝ መንገድ ወንድን ወዳለው ነው ምላቸው አባቴ በስራ ጉዳይ ራቅ ያለ ቦታ ነው ሚኖረው እህቴ ዩንቨርሲቲ ነች ቤት ያለነው እኔና እናቴ ወንድሞቼ ናቸው፡፡ወይ ጉድ ብቻ ይህ ሃሳብም ሌላ ጭንቀት ፈጠረብኝ የስነ - ልቦና መቃወስ እየደረሰብኝ ነበር ድብርት ጭንቀት፤ማልረባ ነኝ ባይነት፤ተስፋ ማጣት፣ የመኖር ትርጉም መጥፋት ብቻ ብዙ ውድቅ ሃሳቦች ልቦናዬን እያስጨነቋት ነበር፡፡ አንድ ቀን ማታ እኔና እናቴ ሳሎን ተቀምጠን ወንድሞቼ ሲያጠኑ እናቴን እየፈራውና እያለቀስኩ የምነግርሽ ነገር አለ አልኳት እናቴ ሳልናገር ማልቀሴ ማንባቴ ይበልጥ አስደነገጣት ምንም ችግር እንደሌለው ደጋግማ ነገረችኝ ነገር ግን ምን ልላት እንደሚገባ አላወኩም ነበር እርዳታ ያስፈልገኛል የፍርሃቴ እና የጭንቀቴ ምንጭ ራሱ ቤተሰቤ ስለ ፆታዊ ስሜቴ ሲያውቁ የሚኖራቸው አመለካካት እንደሆነ ገምታለው፡፡ብቻ የሆነውን መንገር በጣም አስፈራኝ ነገር ግን አንዴ ጀምሪያለው ስለዚህ የሆነ ነገረ መናገር አለብኝ ... ምዕራፍ አምስት እኔ እና ቤተሰቤ