i COVER iii ገፅ ሽፋን:- ዜማ ቅንብር:- ኦርዲነሪ ዛክ አናኒያ ቲ. አዘጋጅ:- የዲ ሚድያና ህትመት iv ቀደም ሲል የታተሙ ስራዎች: ኖር ቁጥር ፩ - የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ፌሽታ (2015/ 2022) ኖር ቁጥር ፪ - ስንኖር - ሆን ተብለው የተዘነጉ ማንነቶች (2016/ 2023) v መታሰቢያነቱ: ሁሌም በልባችን ውስጥ ለሚኖረው ቤን ዶሚኖስ! vi መቅድም በምስጋና የምናጭድበት ማሳ ነው።” የሚል አባባል አለ። በእርግጥ በጅምላ ሁላችንም ተመሳሳይ የሆነ የጓደኝነት ህይወት አለን ወይም ነበረን ለማለት ባልደፍርም ብዙ አንድ የሚያደርጉን ነገሮች ግን አሉ። ባህል እምነት እና ልማድ ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ በሚይዙበት ወግ አጥባቂ ማህበረሰብ ውስጥ መፈጠራችን ከሚያራርቁን ይልቅ የሚያቀራርቡን፣ ከሚያለያየን ይልቅ የሚያመሳስሉንን የህይወት ሰበዞች ሰጥቶናል። ይህኛውን የኖር እትም ለማዘጋጀት ስንነሳ ከእነዚህ የህይወት ሰበዞችን ውስጥ ጓደኝነትን መዘን ለማየት በማሰብ ነው። ኢትዮጲያውያንን እንደ ማህበረሰብ ከሚያመሳስሉን ነገሮች መሃል አንዱ ያለን የእርስ በእርስ መስተጋብር ነው። እንደ ማህበረሰብ ጥብቅ የሆነ ማህበራዊ ህይወትን ነው የምንመራው። ኖር ቁጥር ሦስት ይህ ያደግንበትን ሕይወት የሚዳስሱ የተለያዩ ታሪኮችን አካታለች። በመጽሃፉ ውስጥ ጓደኝነት ራስን ከመቀበል፣ ራስን ከመውደድ እና የራስንና የማህበረሰባችንን ጤና ከመጠበቅ አንፃር በተለያዩ ጸሓፊዎች የተጻፉ አንኳር አንኳር አርዕስቶች ተዳሰውባታል። ከውልደት እስከ ዕድገት በሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ የጓደኝነትን እና የጓደኞቻችንን ጉልህ ድርሻ ባጣፈጠ እና በተዋዛ መልኩ የሚተርኩ፣ በደብዳቤ መልክ የተጻፉ የምስጋና እና የሙገሳ ታሪኮችም አሉን። የፆታዊ ተማርኳችንን እና ወሲባዊ ዝንባሌያችንን የሚሰማንን ስሜት ለጓደኛችን የነገርንበት ታሪክም ተካቷል። ሁላችንም በያለንበት ይህን እትም እያነበብን ጓደኞቻችን ለእኛ፤ እኛ ለጓደኞቻችን ያለንን ቦታ በእርጋታ እንዳስስ ዘንድ ግብዣችን ነው። የዲ ሚድያ እና ህትመት vii ማውጫ ቀደም ሲል የታተሙ ስራዎች: - - - - - - - - iii መታሰቢያነቱ: - - - - - - - - - - iv መቅድም - - - - - - - - - - - v ማውጫ - - - - - - - - - - - vii የልደት ኬክ - - - - - - - - - - 3 የመንገዴ - - - - - - - - - - - 7 Chosen Family: The Lifeline of Queer Friendships in Repressive Ethiopia - - - - 10 ኤደን ባይዘዌ ቦይፍሬንድ አላት - - - - - - - 12 Meet Me in Kazanchis - - - - - - - - 15 Kennaa koo - - - - - - - - - - 21 Untitled - - - - - - - - - - - 22 ደብዳቤ በፖስታ - - - - - - - - - - 25 Ode to My Tenacious Ten-Timers - - - - - - 27 Waajabloo - - - - - - - - - - 33 ከልጅነት እስከ ዕውቀት - - - - - - - - 46 ጓደኝነት - - - - - - - - - - - 53 ቆይታ ከድምቡሼ ገላ ጋር - - - - - - - - 63 Afterword - - - - - - - - - - 79 1 2 ፩ 3 የልደት ኬክ JuJu he/ him Third Time Is A Charm ነው አይደል የሚባለው? የ “ኖር” አዘጋጅ ከሆኑት አንዱ Ordinary Zac ፣ ከዚህ በፊት ለነበሩት ቅጾች ያለኝን ታሪክ እንዳካፍል ሲጠይቀኝ የህይወት ሩጫ ዙሩ የከረረበት ሰዓት ነበርና ሁለቴም ሳይሳካልኝ ቀረ። ሦስተኛው ዙር ላይ ግን ከOrdi ጋር ላለመቀያየም እንዲሁም ደግሞ የታሰበው ርዕስ ባለፉት ሁለት ሦስት ዓመታት በጣም ሳሰላስለው የቆየሁት ነገር ነበርና ወግ ይድረሰኝ ብዬ ያለኝን ላካፍል ተነሳሁ። የመጀመሪያው ሰሞን: ዜግነቴን ተቀብዬ ሰው ለማግኘት ፍለጋ ስጀምር እንኳን እስከዛሬ ድረስ በህይወቴ ትልቅ ቦታ የሚኖራቸው ጓደኞች ይቅርና እኔን የሚመስል ሌላ ሰው አገኛለሁ የሚል ግምት አልነበረኝም። ዕድል ቀንቶኝ ሁለት ሦስት ተመሳሳይ sense of humor፣ የሙዚቃ እና የፊልም ዝንባሌ ያላቸው ጓደኞች አገኘሁ። ከዚህ ቀደም በነበሩኝ የቀጥ ጓደኝነት ውስጥ ያላየሁትን ነፃነት እና comfort ተሰማኝ። ተገናኝተን ማኪያቶ ወይ ድራፍት እየጠጣን ስለ ሙዚቃ፣ ፊልም ፣ celebrity እናወራለን። ካፌ/ ባር ውስጥ የምናያቸውን ወንዶች ውበት እናደንቃለን። ጠቃሚ መረጃዎችን እንለዋወጣለን። ደስ የሚል ግዜ! ግን ሁሌም ስንገናኝ ሁለት ቢበዛ ሦስት ነበር የምንሆነው። አንድ ቀን ከአንድ ጓደኛዬ ጋር መስቀል አደባባይ አከባቢ ያለ ሰፋ ያለ ካፌ ውስጥ ተቀምጠን አላፊ አግዳሚውን እያየን፣ ስለ Mariah Carey አዲስ ዘፈን፣ የዛን ሰሞን date ስላደረግናቸው ወንዶች እየተጨዋወትን ድንገት ከካፌው ወደ ኋላ ተቀምጠው የነበሩ ሰባት፣ ስምንት የሚሆኑ ወንዶች ተከታትለው ወደ በሩ ማቅናት ጀመሩ። ማን እንደሆኑ ለመገመት ግዜ አልፈጀብንም። በዜጋው Facebook አንዳንዶቹ ጓደኞቻችን ናቸው፣ chat እናደርጋቸዋለን። ግን እንደዚህ በቀን ተሰብስቦ በቡድን መጫወት ለእኛ የማይታሰብ ነበር። “ወይ ጉድ! Mini pride አስመስሉት እኮ! ከፊት ያለውን rainbow flag ቢያሲዙት ጥሩ ነበር!” እያልን ሙድ ያዝን። በውስጣችን ግን የዚያ ደስ የሚል ህብረት አባል ለመሆን እንደጓጓን ያስታውቅብን ነበር። 4 ታዲያ ፍርሃታችንን ወደ ጎን አሸቀንጥረን ይሄን ደስ የሚል ማህበር ስንቀላቀል ግዜ አልፈጀብንም። ከሥራ እንደወጣሁ Lapቶፔን እንደተሸከምኩ ቀጥታ ወደ ምንሰበሰብበት ካፌ አቀናለሁ። ለመጀመሪያ ግዜ boyfriend እንደያዘች ልጃገረድ ወደ እነሱ እየሄድኩ የልቤ ምት ይጨምራል። ያቁነጠንጠኛል፣ የሚጠብቀኝ ሳቅ ጨዋታ፣ judgment የሌለበት ነፃነት፣ acceptance ያጓጓኛል። እንደተገናኘን ጨዋታው ይደራል፣ date ላይ ያጋጠሙን ነገሮችን ያለምንም ሃፍረት በግልፅ ይወራሉ። አዲስ download የተደረጉ ዘፈኖች፣ ፊልም፣ መጽሃፍ፣ porn እንቀያየራለን። እንደዜጋ ጨዋታና ተረብ የሚችል መቼም አይገኝም። ተቀዛቅዞ የነበረውን ከቀጥ ጓደኞቼ ጋር የነበረኝን ግንኙነት ጭራሽ አይንህን ላፈር አልኩት። ከዚህ በፊት ተሰምቶኝ የማላውቀው ተቀባይነት፣ መወደድ እና ነፃነት ተሰማኝ። በጓደኞቼ ፍቅር አበድኩ። በካፌና በ lounge ውስጥ የነበረን ግዜ ጓደኞቻችን ቤት ሲከራዩ ወደ እዛ ተዘዋወረ፣ እነሱ ቤት ዓርብ ማታ ገብተን እሁድ ማታ መውጣት የተለመደ ሆነ። Date ማድረግ እራሱ አስጠላን። የ Rupaul’s drag race ከ A - Z ታየ፣ የ Lady Gaga እና Beyonce አልበም ተደነሰበት። We literally were drunk in love!! Newsweek በኢትዮጵያዊያን ዜጎች ላይ Cover story ሲሰራ በዋነኝነት feature ያደረገው እኛን ነበር። በዚህ ሁሉ መሃል ደግሞ ከሣቅና ከጨዋታ በላይ ችግር ሲገጥመን ፈጥነን ደራሽ እንደሆንን አየንበት። ከቤት ለመውጣት ለተገደዱ ጓደኞቻችን ድጋፍ በማድረግ፣ የቤተሰብ ሃዘን የገጠመውን በመድረስ፣ ተመላልሶ በማጫወት ፍቅራችን እውነተኛ መሆኑን አሳየን። የማይረሱ ሞመንቶች እንደዚህ ከጀማው ጋር ተሰብስበን መጫወት የጀመርን ሰሞን አንድ የምናዘወትረው ቤት Elephant walk ነበር። ቁጭ ብለን አፕሬቲቭ እየጠጣን የምናወራው ወሬ እውነት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ወይ የምኖረው ያስብል ነበር። ስለወንድ፣ ስለ sex በግልፅ የማይወራ ነገር አልነበረም። አሁን ሳስበው ዙሪያውን በቀጥ ተከበን እንደዛ መዳፈራችን ይገርመኛል። አንዴ ደሞ ከVictor Geta ጋር ዎክ እያደረግን ቦሌ ጫፍ አካባቢ ያለች ትንሽዬ ባር ዘው አልን። ወደ ማታ 3 - 4 ሰዓት ይሆናል። ቤቷ ከባልኮኒው ጀርባ ካለው አስተናጋጅ በስተቀር ባዶ ነች። የተከፈተው ሙዚቃ ደግሞ ያበደ ነበር። ዙሪያውን በከበበን መስታወት እራሳችንን እያየን በዳንስ ተውረገረግን። ከHollywood gay comedy movie የተወሰደ scene ነበር የሚመስለው። 5 የሆነ ግዜ ደግሞ የምናውቀው የውጭ ዜጋ የሆነሰው farewell party ጋበዘን። ተጋባዦቹ ዜጋም ቀጥም ቅልቅል ነው። ሳሎን ውስጥ እየቀመቀምን መጨፈር ጀመርን። የሆነ ሰዓት እንዴት እንደሆነ ሳላውቀው kitchen ውስጥ ካንዱ ልጅ ጋር ስሳሳም እራሴን አገኘሁት። በሩ ብርግድ ብሎ አንዱ ቀጥ “ምንድነው ይሄ?!” ምናምን እያለ መጮህ ጀመረ። በድንጋጤ ድርቅ ብዬ ቀረሁ። ጋባዣችን ሁሉንም አረጋግቶ አስወጣን። በድንጋጤው ምክንያት ረስቼው ከብዙ ዓመታት በኋላ ከሳምኩት ልጅ ጋር ስናወራ ነው ተመልሶ ትዝ ያለኝ። ለውጥ ታዲያ በዚህ ሁሉ መሃል ሕይወት ያልታሰበ አጋጣሚ ይዛ ከተፍ አለች። ይሄን ሁሉ ፍቅር ትቼ ወደ ባሕር ማዶ መሄዴ ግድ ሆነ። “ይሄን ሁሉ ፍቅር ትቼ ነው የምሄደው?” እራሴን ጠየኩ። የበረራ ሰዓቴ ትንሽ ሰዓት ቀርቶት ቦሌ የሚገኝ ስቱዲዮ ሄደን ከአሥራ አምስት ሰዎች በላይ ሆነን የተነሳነው ፎቶ የምንግዜም አንደኛዬ ነው። እንደዚህ ደስ የሚል የአብሮነት ስሜት ከዚህ በኋላ ይሰማኝ ይሆን? በድጋሚ ጥሩ መሠረት ያለው ጓደኝነት አስፈላጊ እንደሆነ ሕይወት አሳየችኝ። መጀመሪያ ሰሞን የማውቀውና ከእኔ የተወሰኑ ዓመታት ቀደም ብሎ የመጣ ወዳጄ፣ አዲሱን ሕይወቴን ለምጀምርበት ቦታ ቅርብ እንደሆነ ነገረኝ። በእሱ በኩል ደግሞ ሌላ ደስ የሚል ህብረት ውስጥ እራሴን አገኘሁት፣ በአዲስ ቦታ ግራ መጋባት ሲሰማኝ ድጋፍ የሚሆነኝ ቡድን፣ በባዕድ ሃገር “ሀ” ብዬ ለምጀምረው ሕይወት ማጣፈጫ የሚሆኑ ቅመም የሆኑ ጓደኞች። የጓደኝነት Ups & Downs ይሄ ሁሉ ሲሆን ታዲያ ሁሌም ፋሲካ ነው ማለት አይደለም። አንዳንድ ጓደኝነቶች በግዜ እና በቦታ ርቀት፣ በሁኔታዎች ይፈተናሉ። ቀለማቸው ይደበዝዛል። እየበሰልን ስንሄድ አንድ የሚያደርጉን ነገሮች እየሳሱ ይመጣሉ። የ ዜጋ Yahoo Group moderator የነበረው እና እስከዛሬም ጨዋታውን የምወድለት JAMES BOND በቅርቡ ተገናኝተን ስለ ጓደኝነት ሲመክረኝ “Darling, ከሁሉም ጓደኞችህ አንድ አይነት expectation አይኑርህ። ከአንዳንዶች ጋር የልብህን፣ የሚያስፈራህን፣ የሚያስደስትህን ታወራለህ። ከአንዳንዶች ጋር ደግሞ ላይ ላዩን ሳቅና ጨዋታ ብቻ ይሆናል። ከሁሉም 6 አንድ አይነት ነገር አትጠብቅ። ሁሉም እንደየራሱ አስፈላጊ ነው።” ያለኝ የምወደው ምክር ነው። ዋናው ነገር ከልብ የሚወደን ወዳጅ በቀላሉ በእኛ እጅ አይሰጥም። ወደኋላ ስንቀር ቆም ብሎ እየጠበቀ፣ ስንፈጥን “ኸረ ቀስ!” እያለ እስከመጨረሻው አብሮን ይዘልቃል። የወደፊቱ? ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጓደኞቼ የድንገቴ የልደት ፓርቲ አደረጉልኝ። ከአሥራ ሁለት ዓመት በፊት ደግሞ እነዚሁ ጓደኞቼ ተመሳሳይ ፓርቲ አድርገውልኝ የተነሳነውን ፎቶ ይህ Facebook memory አስታወሰኝ። በመሃከላቸው ሆኜ ኬኩ ላይ የነበሩት ሻማዎች ፀዳል ፊቴ ላይ አርፏል። ስጦታ የሰጡኝን “ሙሽራዋ አይጥ” የሚል መጽሐፍ ይዣለሁ። ሁላችንም እየሳቅን ነው። ከ12 ዓመት በኋላ ይህንን መድገም መቻል ምንኛ መታደል ነው? ዩኒቨርሲቲ Freshman ተማሪ ሆኜ፣ ሰው ማግኘት ሳልጀምር በፊት፣ አንድ ቀን ፒያሳ ብቻዬን ዎክ እያደረኩ የተሰማኝ የብቸኝነት፣ ያለመታየት፣ በዓለም ላይ እኔ ብቻ የቀረሁ ያህል የተሰማኝ ባዶነት በእንደዚህ አይነት ዘመን ተሻጋሪ ወዳጅነት ደስታ ይተካል ብትሉኝ ስቄባችሁ ነበር የማልፈው። የዛሬ አስር፣ አሥራ አምስት፣ ሃያ ዓመት ደግሞ በሌላ አይነት ዕድገት፣ ህብረት፣ መደጋገፍ ውስጥ ሆነን አብረን ስንስቅ ስንጫወት በዓይን ህሊናዬ እስላለሁ። ልቤም በደስታ ይሞላል። በቸር ለእዛ ያድርሰን!! ** መታሠቢያነቱ: - ሁሌም ከልባችን ፈገግታህ ለማይጠፋው Ben D.. Juju is an Ethiopian gay man who tries to live everyday by this quote from Maya Angelou. “My mission in life is not merely to survive, but to thrive; and to do so with some passion, some compassion, some humor, and some style.” 7 የመንገዴ በ - ጆይ አንቺ/ እሷ “ቶሎ ለመድረስ ሞክሪ፣ የተወሰነ progress መኖር አለበት!” የአለቃዬ ቀጭን ትዕዛዝ ነበር። እሺ ብዬ ስልኩን እንደዘጋሁ ነበር አንድ ዕድሜው ወደ እኔ የሚጠጋ የደስ ደስ ያለው ልጅ መኪና ውስጥ ከጎኔ እንደተቀመጠ ያየሁት። የሆነ ነገሩ ልብ እንድለው ቢያስገድደኝም ስለምሄድበት ከተማ አዲስነት እና ስለ ሥራ እያሰብኩ ስለነበር ትኩረቴን መሰብሰብ አልቻልኩም። ድንገት ጭልጥ ብዬ ከገባሁበት ሃሳብ የሱ የስልክ ጥሪ ቀሰቀሰኝ። አንስቶ “በቃ ባረፍድም እየመጣሁ አይደል? አትቆጪኝ!” ይላል። በተደጋጋሚ ከሚደወልለት ስልክ ጋር የሚያደርገውን conversation ልብ አለማለት እንዳልችል አደረገኝ። አነጋገሩ በተለምዶ ፋጤ አለባቸው እንደምንላቸው አይነት ወንዶች ነው። ሁኔታዎቹን መቃኘት ጀመርኩ። ቡጭቅ ጅንስ ቁምጣ በነጭ ሸሚዝ ለብሷል። የደስ ደስ ያለው፣ ሲያወራም ለዘብ ብሎ ከበድ የሚሉ ቃላትን የሚጠቀም ነው። ከአቀማመጡ እስከ እጅ አጣጣሉ የኛ ለመሆኑ ይመሰክራሉ። ይሄን እያሰላሰልኩ ነበር በአንዱ የስልክ ደውል አንቺ የምትባለው በወዲያኛው በኩል ያለችው ልጅ የወንድ ድምፅ እንዳላት ሰረቅ ብሎ ወደ ጆሮዬ የገባው። አረጋገጥኩ!! እሱም ሃሳብ ውስጥ ተመሳሳይ ጥያቄ እየተመላለሰ እንደሆነ ያስታውቃል። የሚያስበውን ሃሳብ እንዲያረጋግጥለት ሰረቅ እያረገ ያየኛል። እኔም የ communityአችን አባል ለሆነ ሰው ብዙም አጠራጣሪ አይደለሁም። የምለብሰው አለባበስ እና የምከተለው style እንደ አጠቃላይ የምሰጠው energy በቀላሉ አሳልፎ ይሰጠኛል። ቀስ አድርጎ ጨዋታ ጀመረ። በቃላት ባናስቀምጠውም ተነጋግሮ እንደተግባባ ሰው ስላለንበት ሁኔታ ስለ university ህይወታችን ብዙ አወራን። አርፋጅነቱን አስታኮ university ከብዙሃኖቹ የዕድሜ እኩዮቹ ተማሪዎች ለየት ስለሚል ከእነሱ ጋር እንደ ጓደኞች አብሮ እንደማይውል እና እራሱን ሚሆንባቸውን ጓደኞች ለማግኘት ሌላ ከተማ ድረስ እንደሚሄድ፣ ይህ ሁኔታ class መግባት እስኪጠላ ድረስ 8 ተጽኖ እንዳሳደረበት እና በጣም እየሰለቸው በግድ ገፍቶ እንደተመረቀ ነገረኝ። እኔም ከብዙሃኑ ለየት ማለት ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ እና በውጫዊ ሁኔታችን በቀላሉ እንድንገመት እንደሚያደርገን የራሴን የ university ቆይታ አስታውሼ እንድነግረው አደረገኝ። ምንም እንኳን እኔ በ Academic background ጥሩ የምባል ተማሪ ብሆንም ከምከተለው style አንፃር ብዙ መምህራንም ሆነ የግቢው ማህበረሰብ ያንን ከመቀበል ዱርዬ እና ከትምህርት የራኩ አድርገው በቀላሉ ይገምትቱኝ ነበር። ይህ ሁኔታ በዛ ዕድሜ ላይ ላለው አይምሮዬ ከትምህርቱ ባልተናነሰ ሌላ ማለፍ የነበረብኝ በጣም ከባድ ፈተና ነበር። በህይወቴ ላይም ተፅዕኖ አምጥቶ እንደነበር ነገርኩት። ነገር ግን የራሳችንን ማንነትና አቅም መረዳት እና ሰው ከሚለው አልፈን ዓላማችን ላይ ማተኮራችን የምንፈልገውን ግብ እንድንመታ ረድቶናል። መመረቃችን አንድ ነገር ሆኖ ሳለ፣ የነበረን ብርታት እና ጥንካሬ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ሰውን በውጫዊ ማንነቱ በመገምገም ብቻ አሉታዊ ነገር ሚያስቡትን አስተሳሰብን እንድናስቀይር እንደረዳን አወራን። ሁሉም ሰው ላይ ያለው የተለያየ አለመመቻቸት የሚያሳድረው ጫና እና ተፅዕኖ እንዳለ ሆኖ፣ እኛ በማንነታችን ምክንያት የሚመጣብን ተጨማሪ ተፅዕኖ ተቋቁመን መመረቃችን እጥፍ ስኬት ነው ብለን ተሞጋገስን። መዳረሻችን በቀረበ ቁጥር መግባባታችንም እየጠነከረ ሄደ። ያው ታውቁት የለ የኛን ነገር። የራሳችንን ሰው ስናገኝ ለመግባባት ይቀለናል። ካደራነው ጨዋታ ድንገት ቀና ስል መኪና ውስጥ ያሉ ተሳፋሪዎች ሁሉ ነገራቸውን ትተው የኛን ወሬ እያዳመጡ እንደሆነ ሲገባኝ ምሄድበትን ከተማ እንደማላውቀው እና ለሥራ ለመጀመሪያ ግዜ እየመጣሁ እንደሆነ ነግረው ወሬ አስቀየርኩ። እሱም የከተማዋ ነዋሪ እንደሆነና የሚረዳኝ ነገር ደስ እንደሚለው ነገረኝ። የኔ እና የአዲሱን ጓደኛዬ ቅርርብ በተለምዶ በኮሚኒቲአችን ውስጥ አለ የሚባለው የሌዝቢያን ሴቶችና ጌ ወንዶች የሻከረ ግንኙነት እና ከአንገት በላይ ቅርርብ አላየሁበትም። በድንገት በዕለት ተዕለት ኑሮዬ ላይ መገናኘትን፣ ጨዋታችን፣ የነበረን natural connection ተለየብኝ። በመሃል አንዴ እንኳን ስለ ማንነታችን ሳናወራ እንዲሁ ተግባብተን ስናወራ ከመዳረሻችን ደረስን። 9 ልክ ስንወርድ “ለጓደኛዬ ልደት ነበር የመጣሁት እና ጓደኛዬ እንዳንቺ አይነት ሴት በጣም ነው የሚወደው! ልደቱ ላይ ብትገኚለት በጣም ደስ ይለኛል” አለኝ። የሥራውን ሁኔታ አይቼ ከቻልኩ እንደምመጣ ነግሬው ወደምሄድበት ሸኝቶኝ ስልክ ተለዋውጠን ተለያየን። በዕለቱ በሰዓት መጣበብ ምክንያት በጓደኛው ልደት ላይ መገኘት ባልችልም በሌላ ቀን ተገናኝተን ጓደኞቹን እንደምተዋወቅ ከይቅርታ ጋር ደውዬ ነገርኩት። ተስማማን። በቀጠሮአችን ቀን አንድ ካፌ ተገናኘን። እሱ እና ሁለት ጓደኞቹን ጨምሮ መጣ። በአንዴ ተግባብተን ሳቅ ጨዋታውን አደራነው። ለሚያየን ሰው ለረጅም ግዜ ምንተዋወቅ እንጂ አሁን የተዋወቅን አንመስልም። ጭራሽ አንዱ ለረጅም ገዜ በ social media የማወራው ጓደኛዬ ሆኖ አረፈው። ደስ አለኝ። ጨዋታው መተራረቡ ሞቅ ሲል ከምንሳቀቅ ብለን ወጥተን ዎክ ማድረግ ጀመርን። በዛውም ብዙ ነገር አወራን። ሁሉም በጣም ቀና የሆኑና በተለምዶ በኛ community ውስጥ ከሚስተዋለው ድራማ የነጹ ውብ እና ንጹህ ነብሶች ናቸው። ይሄ ታሪክ እንደ ቀልድ ሦስት ዓመት የሆነው ቢሆንም በዚህ ሦስት ዓመት ውስጣቸው ብዙ ጥሩ ግዜያት፣ የማይረሱ ተነስተው ሚሳቅባቸው ታሪኮች ከምንም በላይ ደግሞ ቤተሰብ ብላቸው የማያንሳቸው ጓደኞች አፍርቻለሁ። እና በጣም እወደዋለሁ። እንደ እኔ መልካም ጓደኞች ያገኘ ምንኛ የታደለ ነው?! ጆይ መኖሪያዋን በኢትዮጲያ ያደረገች ሌስቢያን ፀሐፊ እና የሰብአዊመብት ተሟጋች ነች። ታሪኮችን በመንገር እና ውይይቶችን በማድረግ የታፈኑ እና የተጨቆኑ ኩዊር ኢትዮጲያውያንን ድምፅ ለማሰማት እሰራለሁ። ጥልቅ ውይይቶችና ተፈጥሮአዊ ቦታዎች ያዝናናኛል። ጆይ መኖሪያዋን በኢትዮጲያ ያደረገች ሌስቢያን ፀሐፊ እና የሰብአዊመብት ተሟጋች ነች። ታሪኮችን በመንገር እና ውይይቶችን በማድረግ የታፈኑ እና የተጨቆኑ ኩዊር ኢትዮጲያውያንን ድምፅ ለማሰማት እሰራለሁ። ጥልቅ ውይይቶችና ተፈጥሮአዊ ቦታዎች ያዝናናኛል። 10 Chosen Family: The Lifeline of Queer Friendships in Repressive Ethiopia By He/Him In Ethiopia, where queer identity is both criminalized and deeply stigmatized, queer friendships are more than just casual social bonds—they are lifelines. For many queer individuals like myself, friendships are often the first place we encounter real family, people who choose us, stand by us, and love us unconditionally, even when the world around us denies our existence. My friends, who I consider my chosen family, are a vital part of my life. The significance of these bonds became immediately clear for me when I was diagnosed with leukemia. I was plugged with the fear of accidentally outing myself to my biological family during chemotherapy, where hallucinations could blur my control. This pushed me to hide my illness in fear of being disowned and ostracized. I was faced with the dual burden of coping with leukemia while fearing the rejection of my identity. This was only bearable thanks to my circle of queer friends, I met my friends at different stages of my life. We solidified our bonds through shared experiences and trust we built around each other during life’s toughest challenges. In moments where I needed a sense of belonging and understanding, my friends stood by me. They accompanied me to hospital visits, held my hand during treatment, and stayed by my side in moments of weakness and fear. They became my 11 safety net, ensuring I never felt abandoned or isolated as I navigated this vulnerable period of my life. Queer friendships differ fundamentally from the more socially accepted heterosexual friendships. Heterosexual relationships are reinforced by societal norms and supported by family networks while queer relationships must be forged in secret, hidden from public view. The former exist within a framework of legal protections and social acceptance, in contrast, our friendships are shaped by shared experiences of marginalization, persecution, and resilience. We also have to create our own systems of care. And in times of illness, crisis, or social rejection, these relationships fill in the roles that biological families may not be able or willing to play. I will forever be grateful to the friends who taught me that family is not defined by blood but by those who stay when it matters most. That redefined the very concept of family and reshaped what it means to me to experience love. To have companions during the good times, and a hand to hold on to when the world seems to be falling apart. To have friends that take action. That sit by your hospital bed, cracking jokes to lift your spirits, Reminding you that you are not alone. This is my story. I am queer, survivor, brother, son, and, God willing, soon to be husband. With the grace of God and the unyielding support of my chosen family, I have lived to see another day—and I am ready for whatever comes next. Natthy is a human rights and health advocate working to improve the well-being of Ethiopia’s LGBTQ+ community through access to inclusive healthcare, mental health support, and sexual health education. 12 ኤደን ባይዘዌ ቦይፍሬንድ አላት ኤደን ሳሙኤል አንቺ/ እሷ የኖር ዕትም በጓደኛ ዙሪያ ያጠነጥናል ስባል በእሽቅድድም ነው ጊዜ ሰጥቼ ለመፃፍ የወሰንኩት። ምክንያቱም እጅግ የምወዳቸው እና ለዛሬ ማንነቴ ትልቅ ሚናን የተጫወቱ የቅርብ ጓደኞች ስላሉኝና ስለ እነሱ መጻፍ እፈልግ ስለነበር ነው። ብዙ ግዜ በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ የተቃራኒ ፆታ አፍቃሪዎችን ጓደኛ ማድረግ በይጠሉኛል ፍራቻ ይሁን በሌላ ሕሳቤ ቀላል አይሆንም። እርግጥም የምንኖረው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደመሆኑ ያለው ፍርሃት ዝም ብሎ የመጣ አይደለም:: በተቃራኒ ፆታ አፍቃሪያን ጓደኝነት ውስጥ ማንነታችሁን ደብቃችሁ ላላችሁ ትንሽ ተስፋን ለመጫር፣ እንዲሁም ለሁላችን ደግሞ ጥላቻ ዘማች ብቻ ሳይሆን እንዲህም አሉ ለማለት ስለሶስቱ የተቃራኒ ፆታ አፍቃሪ የቅርብ ጓደኞቼ ልንገራችሁ። ታዲያ ይሄ የኔ የግል ገጠመኝ እንጂ በምንም አይነት የሁሉም ገጠመኝ እንዲህ ይሆናል ማለት እንዳልሆነ ይሰመርልኝ። አንደኛዋን ዘሪቱ ልበላት። ዘሪቱ እና እኔ በሆነ ጉዳይ ምክንያት ነው የተገናኘነው። አስተዳደጋችን ፣ የፖለቲካ እይታችን፣ የፊልም ምርጫችን ሳይቀር ተመሳሳይ ስለነበር ለመግባባት ግዜ አልፈጀብንም። ገና የዩኒቨርስቲ ተማሪ እና የሴት የፍቅር ግንኙነትን ሀ ሁ እያልኩ የነበረበት ግዜ ነበር። በወቅቱ የነበረችኝን ፍቅረኛዬን ለማግኘት ያለ የሌለ ውሸት እየዋሸሁ ነበር የማሳልፈው። ሌላ ግዜ እንገናኝ ብላኝ ለምን መገናኘት እንዳልቻልኩ በቀላሉ እነግራታለሁ። ፍቅረኛዬን የማገኝበት ቀን ግን “በሬያችን ወልዳ እያረስኩ ነው” አይነት ነበር ምክንያቴ። በግዜው ስለ ማንነቴ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ አብሬያቸው ከሆንኳቸው ሰዎች ውጪ ማንም አያውቅም ነበር። “ምን ትለኝ ይሆን? ብትጠላኝስ? እንዴት ታስበኝ ይሆን?” የሚሉት ፍራቻዎች እውነታዬን እንድደብቅ አድርገውኝ ቆዩ። ከጓደኝነት በላይ ቤተሰብ መሆናችን እየገባኝ ሲመጣ ውሸቱም ይበልጥ ይከብደኝ ጀመር። ያየችውን እና የወደደችውን ወንድ ትነግረኛለች እኔ ያንን መንገር ስለማልችል በጣም አዝን ነበር። 13 ታዲያ አንድ ቀን ነገሩ ሲብስብኝ ድብብቆሹ ሲያስጠላኝ... በወሬ መሃል “እንትናን አፈቅራታለሁ!። እኔ ለወንድ ምንም አይነት ስሜት የለኝም” ብያት አረፍኩ። መደናገርም መደናገጥም አልነበረባትም... “ኧረ? እሺ” ብላኝ አለፍነው። አንድም ቀን ጥያቄ ሳታደርገው አሁን ላይ አስር ዓመታትን እየቆጠርን አብረን አለን... ከኔ አልፎ የእህቴም ምርጥ ጓደኛዋ ናት። ለእህቴ የእኔን መቀበል እና መረዳት ራሱ የዘሪቱ ትልቅ አስተዋፅዖ አለው። ሌላኛዋን ጓደኛዬን ደግሞ መክሊት እንበላት... ትውውቃችን በአንድ አጋጣሚ ነው። ራሴን ተቀብዬ እና አውቄ መኖር ከጀመርኩ በኃላ የቅርብ ጓደኞቼን አንድ በአንድ የመንገር ዘመቻ ውስጥ ነበርኩ 😅 ምናልባት አካባቢዬ ላይ ስለእኛ ማንነት ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች ናቸው ብዬ ስለማስብም ይሆናል። በይበልጥ ሃያዎቹ መጨረሻ አካባቢ ያበጠው ይፈንዳ ብዬ ነበር። ከመክሊት ጋር የተግባባነው ባለን መጽሃፍ ማንበብ ዝንባሌ እና ርዕሶችን እየተለዋወጥን በምንኮመኩማቸው የተለያዩ መፅሃፍት ነው። ፍቅረኛዬን በተለያየ አጋጣሚ የቅርብ ጓደኛ እያልኩ ማስተዋወቁ ያሳዝናል። ሁሉም ፍቅረኛዬ እያሉ የሚያወሩለት ወንድ አለ... እኔ ያንን ማድረግ ባለመቻሌ ያበሳጨኝ ነበር። የሆነ ቀን መክሊትን አንድ የምነግርሽ ነገር አለ ብዬ ሰሚራ ፍቅረኛዬ እንደሆነች ነገርኳት። “አውቃለሁ ካንቺ ይምጣ ብዬ እንጂ ያላችሁ ግንኙነት ከእኔና ከብሩክ ጋር በምን ይለያል” ብላ ገላገለችኝ። ቀለል አድርጋ መቀበሏ ሲገርመኝ አክብራ፣ ከራሷ ይምጣ ብላ፣ ያየችውንና የጠረጠረችውን ማቆየቷ አይደንቅም? ከሶስተኛዋ ጓደኛዬ ብርክቲ ጋር በስራ አጋጣሚ ተገናኝተን ሃገር መጎብኘትን እና መዞርን በመውደዳችን ተገጣጥመን አብረን በቻልነው እንንቀዠቀዣለን። የነገርኳት ቀን በደስታ ወይን ካልጠጣን ብላ፣ በወይን የኔን ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነት እንደምታከብር እየነገረችኝ አስሬ “ምንም ጠርጥሬሽም አላውቅ” እያለችኝ ስንስቅ አመሸን። የሆነ ጊዜ ላይ አንድ ቦታ አብረን ተጉዘን ያገኘናቸው የብርክቲ ጓደኞች መሃል አንደኛው ሊያሽኮረምመኝ ሲሞክር ከየት መጣች ሳልል “ኤደን ባይዘዌ ቦይፍሬንድ አላት ምን አይነት ምርጥ ልጅ እንደሆነ..” እያለች ከጎኔ ቆማ አሳልፋልኛለች። ከመቀበል አልፎ ከጎን እንዲህ ስለሚቆሙልኝ እና ስለእንክብካቤያቸው ብዙ አመሰግናቸዋለሁ።