ይህ አጠር ያለ ፅሁፍ በይበልጥ በዚ ወር ስለሚዘከሩ ትራንስ ወንድም እና እህቶቻችን ታሳቢ ተደርጎ የተፃፈ ሲሆን። የኩዊር ማንነቶችን እንዲሁም ስለ ፆታ ፣ ጄንደር እና ፆታዊ ማንነትን ጨምሮ ስለ ወሲባዊ ዝንባሌ ዳሰሳ የሚያደርግ ቀለል ያለ መጣጥፍ ነው። ጥላቻን ከሚያሳድጉ ነገሮች አንዱ አለማወቅ ነው። ይህ መጣጥፍ የጠለቀ ዘገባ የያዘ ባይሆንም ግን በሰው ልጅ የማንነት አውዶች ውስጥ ስላሉ ልዩነቶች መረዳት እንድንችል ትንሽ ብርሃን ያበራል የሚል እምነት አለን። ከዛ የተነሳ የተዘጋጀ ስለሆነ እንደሚማሩበት ትልቅ ተስፋ አለን።