ያልተቋጨ ፣ በእንጥልጥል ልብ ላይ ከብዶ የቀረ ጥልቅ ስሜት የሚያሳይ ኩዊራዊ ደብዳቤ ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው ከአዝራኤል በማንነት ሚዲያ ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው ደብዳቤ በማንነት ሚዲያ | አዝራኤል 2 ለምን ? ምክንያቱም ስለምወድህ ፤ አንተ ግን እንደማትወደኝ ስለማቅ ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው። ይሄን ደብዳቤ ስታነበው ምን እንደሚሰማህ አላቅም። ግን እኔ ከተሰማኝ ስቃይ ግማሹንም እንደማይሰማህ እርግጠኛ ነኝ። ልቤን እንዳቆሰልክ ያንተም ልብ እንዲቆስል ምኞቴ ነበር። ግን እንዴት ብዬ አንተ ላይ ልጨክን። ታቃለህ መጀመሪያ ላይ አልወድህም ነበር። አረ እንደውም እጠላህ ነበር ብል ይሻላል። " ምን አድርጌው የትስ አግኝቼው ነው የጠላኝ ?" ብለህ ራስህን መጠየቅህ አይቀርም። ምክንያቴም ትንሽ ያስቅህ ይሆናል። ክፍል ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምህ ሲጠራ ስሰማ ነበር የተናደድኩት። ማን አባቱ ነው ከኔጋ ተመሳሳይ ስም ያለው ብዬ በገንኩ። ግን መምህሩ ድጋሜ አስተካክሎ ስምህን ሲጠራው ከኔጋ እንደማይመሰሰል እንደውም ከኔው ስም ቢቀራረብም ያንተ ግን የተሻለ fancier version ነበር። " አቤት " ሚል ድምፅ ወደ ሰማሁበት ቦታ ስዞር ነው በስም ብቻ ሳይሆን በመልክ በቁመናም ከኔ የበለጥክ እንደሆንክ ያየሁት፤ የሆነ ጢባራም መስለህ ታየሀኝ ጠላሁክ። እጅህ ላይ እንደሚጥለኝ መች አውቄ። በማንነት ሚዲያ | አዝራኤል 3 ይገርምሀል ሁሉም ሰው ስለፍቅር ሲጠይቀኝ ሁሉም ጥንድ ጥንድ ሆነው ሳይ ምን እንደምል ? " ፍቅር የልጅ ጨዋታ ነው። ፍቅር ሊይዘኝ አይችልም ምክንያቱም ፍቅር ተራ ስሜት ነው። እኔ ደሞ ለስሜቶቼ ተገዢ ሳልሆን ሁሉንም ስሜቶቼን በቁጥጥሬ ስር ያዋልኩ፤በምክንያታዊነት የማምን በልቤ ሳይሆን በአእምሮዬ የማስብ እና የልብ ዋነኛ ስራው ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችን ደም ማሰራጨት እንደሆነ ጠንቅቄ ስለማቅ፤ በልቤ ላፈቅር አልችልም። ባጠቃላይ ፍቅር ተራ fantasy መስሎ ነው ሚታየኝ። " ነው ምላቸው። " የምርህን ነው ወይስ እየቀለድክ ? የምር በፍቅር አታምንም ማለት ነው ?" ብለህ ብትጠይቀኝ ግን መልሴ ሌላ ነው። " ማህበረሰቡ እኔ ምፈልገውን አይነት ፍቅር ስለማይፈቅድ። እኔም fear of rejection plus insecurities ስላለብኝ እንጂ ፍቅርን እንዴት ልጠላው እችላለው ? ፍቅር እንዲይዘኝም እፈልጋለሁ። እንደ እድሜ እኩዮቼ ፍቅርን ማጣጣም እመኛለሁ። ከፍቅረኛዬጋ እጅ ለእጅ ተያይዘን ምሽት ላይ በጨረቃ ብርሀን ታጅበን የእግር ጉዞ ማድረግ፣ ሲኒማ ገብተን አንድላይ ፊልም ማየት፣ በዝናቡ ውስጥ ሆነን ስንሳሳም፣ አንድ ላይ ተቃቅፈን መተኛት እፈልጋለሁ። " እሱ ነበር ምኞቴ። አንተ ነበርክ ምኞቴ።ግን ምን ያደርጋል ምኞት ብቻ ሆነህ ቀረህ። 4 እስቲ እኔ ደሞ ልጠይቅህ። " ትልቁን ፍቅር ተወውና፤ የአይን ፍቅር ይዞህ ያቃል ?" ። ያንተን ባላቅም እኔ ግን እርግጥኛ ነኝ አውቀህ ይሁን ሳታውቅ ስንቱን ወንድና ሴት በፍቅርህ ጠብ እንዳረካቸው። ስንቶቹ ይሆን ድፍረት አግኝተው ስሜታቸውን የተናዘዙልህ፤ እግርህ ስር ተደፍተው የለመኑህ። ደሞም አለን የኔ አይነቶቹ ከሩቅ አይተን በሩቁ ወደንህ በሩቁ የተሰናበትንህ። " አትፍራኝ አትሽሸኝ ፡ ባንተ ያምራል አነጋግረኝ " በልባችን የቤተልሔም መኮንን " አነጋግረኝ " ዘፈን እያዜምን በሩቁ እንደተመኘንህ የቀረን ስንት እንሆን ? በማንነት ሚዲያ | አዝራኤል በማንነት ሚዲያ | አዝራኤል 5 ግንኮ አምና ሙሉ አመቱን አንድ ክፍል ውስጥ ስንማር ዞርም ብዬ አላየሁክም ነበር። ለነገሩ አምናማ አደለም ካንተጋ ልግባባ፤ የቡድን ስራ በተባለ ቁጥር ማንንም ስለማላወራ ሁሌም ያልሞላቹ አስገቡኝ ልመና አልነበር እንዴ። ደሞ የሚገርምህኮ ራሴው ነኝ ክፍል ቀድሜ እየገባው ከኋላ እየተቀመጥኩ ከዛም ቀድሜ ምወጣው፤ ከማንም ጋ የእግዜር ሰላምታንኳ ማልለዋወጠው። ያው እናንተ ባታቁኝም እኔ ግን ሁላችሁንም አውቃቹ ነበር። ክፍል ውስጥ ሲደብረኝ የሁላችሁንም ባህሪ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ ና የክፍል መስተጋብራቹን ነበር ምገመግመው። " እና እኔን ምን አይነት ሰው አርገህ ሳልከኝ ?" ብለህ ብትጠይቀኝ፤ " አንተና ጓደኞችህ special case ነበራቹ። ምክንያቱም አንድ ላይ ተሰብስባቹ ሳያቹ ብቸኝነቴን እንድጠላው ታረጉ ነበር ያው እቀናባቹ ነበር ብል ይቀለኛል። ደግነቱ ክላስም ሆነ ጊቢ ውስጥ ከስንት አንዴ ባያቹ ነው እድሜ ለዩኒቨርሲቲው ስፋት so ያን ያህል ከቁብም አልቆጥራቹም ነበር። ብቻ እሱ ሁለተኛ አመት እያለን አንተም ከሌሎቹ ተለይተህ አይኔ ውስጥ ሳትገባ የተፈጠረ ነው። ይሀው አሁን ሶስተኛ አመት ስንሆን ነው በህይወቴ አስቤው ማላቀው ነገር የተፈጠረው። አንተ አታስታውስ ይሆናል ግን ትምህርት ከተጀመረ ገና ወር ቢሆን ነው። እኔም እንደለመድኩት ስሜ ባይፃፍባትም ሁሉም የኔ እንደሆነች ሚያቃት ውዷ ቦታዬ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ። ያኔ አንተም መጥተህ ከጎኔ ያለው ወንበር ላይ ተቀመጥክ። ጎደኞችህም ተከትለውህ ከፊት ከጀርባዬ ከጎኔ ከባቹኝ ተቀመጣቹ። የምር በውስጤ ምን ያህል ስረግማቹ እንደነበር ብትሰማ ትገረም ይሆናል። ለኔ ግን ያቺ ቦታ ልዩ ነበረች ከማንም ጋ ስለማልገናኝባት። እና እልሀለው እኔ እንደሆንኩ እንደምታቀው በስርአቱ አልማርም በስልኬ ፊልም ወይም እድሜ ለግቢው ዋይፋይ ቲክቶክ ባይ ነው። አዝራኤል ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው ማንነት ሚዲያ 6 ግን ያን ቀን እድሜ ላንተና ለጓደኞችህ ፊልም እንዳላይ ምቾት ስለነሳቹኝ ቁጭ ብዬ በስርአቱ ተማርኩ። ግን ከትምህርቱ በላይ ትኩረቴን ምን እንደሳበኝ ታቃለህ ? ከፊት ለፊትህ የተቀመጠውን ጓደኛህን ለቀልድ በእስክርቢቶ እየወጋህ አንገቱንም እየመታህ ስትረብሸው፤ ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ በደንብ አስተዋልኩህ። ያው እኔም ጓደኛዬ ጋ አንድላይ ስንማር እንዲ ነበር ምበጠብጠው። እናም ያን ቀን ነው ላንተ ያለኝ ስሜት መቀየር የጀመረው። For the first time I saw you for who you truly are, a handsome boy with a beautiful soul መለሎ ቁመትህ፣ የመልክህ ቅላት ( ከስምህ በመነሳት ክልስ ሳትሆን አትቀርም እንጂማ ሀበሻ አደለህም የሚል ግምት አለኝ ) ፣ የሰውነትህ ቅርፅ፣ አረማመድህ ግርማ ሞገስን የተመላ፣ ስታወራ የድምፅህስ ማማሩ እነዚህ ሁሉ ውብ ፀባይህ ላይ ተደማምረው ከልቤ ዙፋን ላይ አስቀመጡህ። አዝራኤል ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው 7 እንግዲህ ከዛች ቀን ጀምሮ ላንተ ያለኝ ስሜት ቀን በቀን እያደገ መጣ። እኔም የምችለውን ያህል ራሴን ለማረጋጋት ብሞክርም አልቻልኩም። ቀን ከሌት ስላንተ ነበር ማስበው። አንድ ክላስ መሆናችን ሳያንስ ደሞ ዶርማችን አንድ ብሎክ ላይ መሆኑ ፤ ያው አንተ ሶስተኛ እኔ አራተኛ ወለል ላይ ብሆንም ብዙ ጊዜ ደረጃ ላይ ስትወርድ ስትወጣ ማየቴ ነገሩን አባሰው። ግን ቀኑ ደረሰና ይሀው ዛሬ ስሜቴን ልናዘዝልህ ወሰንኩ። የሚካያን " ላንተ ስል " ዘፈን እየሰማው እኔም እራሴን ላንተ ስል ቀየርኩኝ ልበልህ። ሁለት አመት ሙሉ ዩንቨርስቲ ውስጥ ስንማር እንደምታየኝ በዚ ቅጥነቴ ሳምንት ሙሉ አለባበሴ ቱታ ሱሪ በቲሸርት በነጠላ ጫማ ባንዱ እጄ ደብተር በሌላው እጄ ስልኬን ይዤ መንከዋከው ነበር ስራዬ። ግን ላንተ ስል አለባበሴን አስተካከልኩ ጅንስ ሱሪ፣ ሸሚዙን ቲሸርቱን፣ ጃኬት ከሁዲ ጫማውንም እያማረጥኩ በየቀኑ እየቀያየርኩ መልበስ ጀመርኩኝ። ድሮ ከእንቅልፍ ተነስቼ ፊቴን ላለመታጠብ ቁርሴን እዘል የነበርኩ ልጅ ጠዋት ጠዋት መስታወት ፊት ቆሜ እየተቀባባው መውጥት ጀመርኩ። የሽቶውን ነገርማ አትጠይቀኝ እንደ ሀይላንድ ከፍቼ እላዬ ላይ ማፍሰስ ነው የቀረኝ። የዶርም ልጆች ጉድ እስኪሉ በጠዋት እየተነሳው ሜዳው ላይ ባይህ ብዬ ስፖርት መስራት ጀመርኩ። አዝራኤል ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው ማንነት ሚዲያ 8 ጓደኛዬ ፍቅረኛውን ሊያገኛት ምሽት 1 ሰአት ላይ ሲወጣ እኮንነው እንዳልነበር ይሀው እኔው ግን በውድቅት ለሊት አንተን ፍለጋ ጊቢውን እዞረው ጀመርኩ። እኛጋ ውሀ የለችም፣ ሀይል የላትም እያልኩ እናንተጋ ጠዋት ጠዋት መምጣቴ ፤ የኛን ሻወር መክፈቻ ገነጠሉት እያልኩ የናንተን መጠየቄ ፤ በሰበብ አስባቡ እናንተ ዶርም መመላለሴ አንተን ለማየት ምክንያት መደርደሬ ነበር። ሰው ቀና ብዬ ላለማየት ስልኬ ላይ አፍጥጬ ምራመደው ልጅ አሁን ግን አንገቴን ቀና አድርጌ በአይኔ ከዛ ሁሉ ሰው መሀል አንተን ፍለጋ ሆነ ስራዬ፤ መለሎ ቁመትህም ስራዬን አቀለለልኝ። ባጠገብህ ባለፍኩ ቁጥር ሰርቄ እያየሁክ አልፈሀኝ ስትሄድ እኔም ዞሬ አንተን በአይኔ ስሸኝ ሳላይ የውሻውን ጭራ ረግጬ እየጮሀ ያባረረኝን እንዴት እረሳዋለው። ሁለት ሴክሽን አንድ ላይ ተቀላቅለን ስንማር ጀለስን ክጄ ካንተ አጠገብ መቀመጤ፤ ትምህርቱን ትቼ አንተ ላይ ማፍጠጤ። ሚድ ተፈትነን ስንወጣ ስሜን እየጠራህ " ፈታኙ ስምህን አልፃፍክም ተመለስ እያለህ ነው። " ስትለኝ ፤ ግን ስሜን መፃፍ የረሳሁት ፈታኙ አንተን ከፊቴ አስቀምጦህ በስትክክል ማሰብ ቢሳነኝ እንደሆነ ማን በነገረህ። ያንተ እይታ ውስጥ ለመግባት ያላረኩት ጥረት የለም። ምናልባት የጥበብ አድናቂ ከሆንክ ብዬ ደብተሬ ላይ እነዛን ስእሎችን መሳሌኮ ያንተን አድናቆት ፍለጋ፤ አንተ አይተህ ወደሀቸው እንድታወራኝ ነበር። ግን አድናቆቱን ከሌሎች ነበር ያገኘሁት " ስእሎችህ ለየት ያሉ ናቸው። " " በጣም ነው ሚመስጡት " " ትምህርቱን ትተህ ስእል ላይ ብታቶክር ይሻልሀል። " " በናትህ እኔን ሳለኝ። " ይሄ ሁሉ ተብያለው። ግን እኔ የፈለኩት ያንተን የአንድ ቃል አድናቆት መስማት ነበር የነዛ ሁሉ ሰዎች ንግግር ለኔ ከቢንቢ ጩሀት በምንም አልተለየም። አዝራኤል ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው ማንነት ሚዲያ 9 ጆሮዬም ልቤም አንተጋ ነዋ። ላንተ ያለኝን ስሜት ይገልፁልኛል ያልኳቸውን ቃላት ደርድሬ ግጥም ብፅፍልህ ማን ያንብብልህ። ደብተሬን አውቄ አንተ አጠገብ ብጥለውም አንተ ግን ትንሽ ለማየት እንኳ ሳትሞክር ወዲያው አንስተህ አቀበልከኝ። እንግዲህ መድረክ ላይ ወጥቼ እንዳልዘፍንልህ ድምፄ ከየድረሱልኝ ጩሀት ትንሽ ነው መለስ ሚለው። በጣም አሞኝ የቀኑን ክላስ ቀጥቼ ተኝቼ ውዬ ምሽት ላይ የዶርም ልጆች " ና ወጣ እንበል ትንሽ ቢቀልልህ " ብለውኝ አይ ይለፈኝ የራስ ምታት ኪኒን ውጬ ልተኛ ነው ብዬ እነሱን ሸኝቼ ውሀ ልገዛ ከዶርም ስወጣ ፤ ፌድ ያረገው ነጭ ጅንስህ፣ በጥቁር ቆዳ ጫማህ አንገቱ ላይ ፈር ካለው ጥቁር ሌዘር ጃኬትህጋ አርገህ በደረጃው ስትወርድ ባይህ ዶርሙን ሳልቆልፍ ልብስም ሳልደርብ ከስድስት ኪሎ አራት ኪሎ ቀጥሎም ፒያሳ ድረስ ሳታየኝ እንደ ቅጥር ነፍሰ ገዳይ አንተን መከተሌ። አረ ስንቱ ተዘርዝሮ ያልቃል ብለህ ነው። ከሁሉ በላይ ግን ተስፋ የሰጠኝ ምን እንደሆነ ታቃለህ። ልቤን በውሸት ተስፋ የሞላኝ። የተለመደውን ቀለበት አድርጌ አውቄ አንተ እንድታየው እያረኩ ስፈታተንህ አንተም ከሆነ ጊዜ በኋላ ተመሳሳይ ቀለበት ማድረግ መጀመርህ። በቃ ያኔ ልቤ በሀሴት ተሞላች። ምክንያቱም እኔን ሚሰማኝ ስሜት አንተጋም ያለ እና ምልክት እየሰጠኸኝ ነበር የመሰለኝ። ሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ትምህርት ሲጀመር የክላስ አለቃችን ጓደኛህ ስለሆነ የኛ ቡድን እንዲፈርስ አድርገህ ከኔጋ አንድ ቡድን መሆን መፈለግህ እኔን ልትቀረብ ፈልገህ ነበር የመሰለኝ። አዝራኤል ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው ማንነት ሚዲያ 10 አሳይመንት ተከፋፍለን ስንሰራ አንተ የራስህን ድርሻ ስላልጨረስክ እኔው ያንተንም ሰርቼ ማስረከቤ፤ አንተም መንገድ ላይ አስቁመህ ሰላም እያልከኝ አሳይመንቱን እንዴት አረጋቹት እያልክ ስትጠይቀኝ ፤ እኔን ለማውራት ሰበብ ፈልገህ ይመስለኝ ነበር። ከሆነ ጊዜ በኋላ አንተን ሳይ አንተም በምላሹ እየዞርክ ስታየኝ አይን ለአይን ስንጋጭ ፤ እኔ አፍሬ ዝቅ ስል አንተ ግን እኔን ማየትህን ስትቀጥል። ደሞም የዶርም ደረጃ ላይ ስንገናኝ ለትንሽ ደቂቃ ተፋጠን መቆማችን ፤ ሳስበው ዝምብዬ እየቃዠሁ ነበር አንተ እኔን ከነመፈጠሬም ትዝ አልልህም ነበር። ግን የምር ይሄ ሁሉ ማረገው እንደወደድኩህ እንደሆነ ስላልገባህ ነው ወይስ አንተ የምትፈልገው አይነት ሰው ስላልሆንኩ ? ብዬ ብጠይቅህ በወደድኩ። ግን እኔም እውነታውን መጋፈጥ ስለፈራሁ ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው። አዝራኤል ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው ማንነት ሚዲያ 11 I loved you, I really did love you, to be honest I still love you and I will continue to love you, I know u won't love me, I know I'm not your type, I know I don't have the looks, maybe that's why you never bothered to talk to me ለዛም ሲባል ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው cause it hurts less to know that you didn't love me because you are straight, instead of me not being your type. ይሄ ሁሉ አንተን ለመሳብ ያረኩት ሙከራ ያልተሳካው ቀጥ ስለሆንክ እንጂ እኔን ባላየ እያለፍክ አይደለም ብዬ ራሴን እንዳፅናና አንተንም እንዳልጠላህ፣ እኔ አጥቼህ ሌላ ወንድም ከሚያገኝህ በድጋሜ ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው ። I hate how much I love you. ÆZRÃÊL ማንነት ሚዲያ አዝራኤል ዜጋ እንዳትሆን ከልቤ ተመኘው ማንነት ሚዲያ መሰረቱን በበይነ መረብ ያደረገ በኢትዮጵያውያን ኩዊር ግለሰቦች የተመሰረ ለኢትዮጵያውያን LGBTQ+ ኮሚኒቲ አንድነት ፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ ጤንነት እና የአመለካከት ለውጥ እና ግንዛቤ እና ታይታን ለመፍጠር የሚንቀሳቀስ ፕላትፎርም ነው። ይህ ደብዳቤ በማንነት ሚዲያ የድምፀተ ዜጋ መርሃግብር የተቀናጀ ሲሆን ድምፀተ ዜጋ የኩዊር / ዜጋ ማህበረሰብን ትግል ፣ ተሞክሮ ፣ አስተሳሰብ እና ናፍቆት ስሜት እና ህይወታዊ ዳራ ከእራሳቸው ከባለታሪኮቹ ቃላት አንፃር የሚያስዳስስ ነው። ድምፀተ ዜጋ ከዜጋው ማህበረሰብ ስለዜጋ የሚናገር ፣ ራስን የመግለጥ ፣ ራስን የመተረክ እና በፈጠራ እና በአርቲስቲክ ስራዎች ራሳችንን የምናሳይበት ሲሆን በዚህ ፕሮግራም የዜጋ ይዘት የተላበሱ የህይወት ተምክሮዎች ፣ ትግሎች ፣ አኗኗራችንን ከማህበረሰቡ እየሰበሰብን እናቀርባለን። ድምፅ እናሰማ ታሪካችንን እንናገር ! maninetmedia@gmail.com Facebook page: Maninet Media Telegram Channel: @maninetlgbtq1