የሰው ልጅ ማንነታዊ ልዩነቶች መሶብ መፅሔት ህዳር 2018 አዘጋጅ እና ፀሀፊ - አቢጌል ሰላም እና ነፃነት ለሁሉም ! የኪዊር መብት ስብአዊ መብት ነው ኤልጂቢቲኪው + ፣ ፆታ ፣ ስርዓት - ፆታ እና ፆታዊ ዝንባሌ እና ማንነት ሲብራራ ለኢትዮጵያው አንባቢያን ማውጫ መግቢያ 01 ምዕራፍ አንድ - ፆታ 02 ምዕራፍ ሁለት - ስርአተ ጾታ 03 ምዕራፍ ሶስት - ሽግግረ - ፆታ 04 ምዕራፍ አራት ፆታዊ የፍቅር ዝንባሌ 05 ማጠቃለያ 06 የሥርዓተ - ፆታ ማንነት ስርዓተ - ፆታ አገላለፅ ምስጋና ህዳር 2018 በመጀመሪያ ይሄን ፅሁፍ ጀምሬ እስክጨርሰው ድረስ ብርታትን እና ጥበብን የቸረኝን ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ። በመቀጠል በዚህ የፅሁፍ ስራ ላይ ላገዙኝ ሰዎች በሙሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁሌም ከጎኔ የሆነውን አለውልሽ ብሎ ሲያበረታኝ የነበረውን እና የዚህን ፅሁፍ መነሻ ሀሳብ በማቅረብ ስለ ሁኔታው ያለኝን እውቀት በማስፋት የረዳኝን ውዱን ወንድሜን እና ጓደኛዬን ሮቢን እዮአብን አመሰግናለሁ። ለነገሮች ለመጀመሪያ ጊዜ አይምሮዬን እንድከፍት እና ሁሌም መልካም ሰው መሆን እንዳለብኝ የምትነግረኝን ጓደኛዬ ፣ እህቴ እና ፍቅሬ የሆነችውን አፍሮዳይትን አመሰግናለሁ። ስለዚህ ፅሁፌ ባያውቁም በጥሩ ስነ ምግባር እና ማንነት እራሴን እንድሆን አድርገው ያነፁኝን ቤተሰቦቼን አመሰግናለሁ። በመጨረሻም በዚህ እሾሀማ መንገድ ውስጥ አብራችሁኝ እየተጓዛቹ ያላቹ ልበ ብርሀናማዎቹ እና ጠንካራ የ LGBTQ+ እህት እና ወንድሞቼ ሁሌም ድጋፋቹ አብራችሁኝ በመሆኑ አመሰግናችኋለሁ። ሁላችሁንም ፈጣሪ ይጠብቅልኝ ፤ እወዳችኋለሁ !! መታሰቢያነቱ ለኢትዮጵያውያን ኤልጂቢቲኪው + ማህበረሰብ በተለይም ለደፋር በትራንስጄንደር ወንድም እና እህቶቻችንን ይሁን ! ህዳር 2018 መግቢያ ህዳር 2018 የሰው ልጆች እንደፀባያችን እና መልካችን የተለያየን እንደመሆናችን በመጠነ ስፋት ደግሞ አካላዊ ፣ስነልቦናዊ እና ማህበረሰባዊ አስተዳደጋችን እና አፈጣጠራችኝ አስተሳሰባችንን ይቀርፀዋል። ስለ አፈጣጠራችን ለመፃፍ አንዳንድ አማርኛ ቃላቶችን ማግኘት ከባድ ቢሆንም ከ English ጋር እየቀላቀልን እስኪስለ ፆታ (sex) ፣ ስርዓተፃታ (gender) ፣ስርዓተ ፃታ ማንነት (gender identity) ፣ ስርዓተ ፆታ አገላለፅ (gender expression) ፣ ሽግግረ - ፆታ (Transgender) እናየፆታዊ ፍቅር ዝንባሌ (sexual orientation) አንድ በአንድ እንመልከት። በእነዚህ ነገሮች ፣በትራንስ ጄንደር እና በጄንደር ልዩነቶቾ መሀከል ያለውን ነገር ማወቅ እና መረዳት የተሻለ እና ነገሮችን ጠልቆ መመልከት የሚችል ማህበረሰብ ለመፍጠር ያስችለናል። ይሄም ጥናታዊ ፅሁፍ ስለነዚ ነገሮች ጠልቀን እንድናውቅ እና ስለነዚህ ነገሮች ያለንን የተሳሳተ አመለካከት ለመቀየር የሚረዳን ነው። ይህ መፅሀፍ በሰው ልጆች የህይወት ኑሮ መካከል ስላለው ልዩነት የሚዳስስ በሳይንሳዊ ጥናቶች ላይ የተመሰረተ መጣጥፍ ነው። ምዕራፍ አንድ - Sex ( ፆታ ) ህዳር 2018 ትርጓሜ ፦ስንፈጠር ወይም ስንወለድ ያሉን አካላት (biologic organ) እና የአካላታችን ተግባር (physiological) ባህሪያት ላይ ተመስርቶ የሰውልጆችን እንደ ሴት ፣ ወንድ ወይም ሁለቱም (intersex) ብለን ስንገልፅ ያመላክታል። ለምሳሌ የወንድ የመራቢያ አካላት (biological or anatomical structure) ስንል ጥቂቶቹ ፦ Testicle( ቆለጥ ) - ለ Sperm እና hormone ምርት የሚያገለግሉ ከውጭ የሚታዩት ሁለት ፍሬዎች Penis( ብልት / ቁላ )- ለመሽኛነት እና ለፆታዊ ግንኙነት የሚጠቅም አካል ነው Scrotum ( የቆለጥ ከረጢት )- የውጫዊ ቆዳ ሆኖ ቆለጥን በመሸፈን የተመረቱትን ሆርሞኖች እና ስፐርሞች ሙቀት አመቻችቶ ሚያስቀምጥ ነው prostate gland ( የፕሮቴስት እጢ )- ከሽንት ማጠራቀሚያ በታች የሚገኝ ከስፐርም ጋር የሚቀላቀል ፈሳሽ አምራች አካል ነው። ህዳር 2018 የሴቶች ፦ Clitoris( ቂንጥር )- ጥቂት አካሏ ብቻ ከላይ የምትገኝ እና አብዛኛው gland ከተለያዩ ነርቮች ጋር ወደ ውስጥጠልቆ የገባ ቢሆንም በፆታዊ ግንኙነት ወቅት ስሜትን በመቀስቀስ ወሳኝ ሚናን የምትጫወት አካል ናት Vulva ( የውጭ ብልት )- አጠቃላይ ከውጭ ያለውን ( የእምስን ውጫዊ ቀዳዳዎች /vaginal opening እና ቂንጥርን ጨምሮ ) የመራቢያ አካል አቅፎ የያዘ ውጫዊ አካል Vagina( እምስ )- የሴት ልጅ የውስጠኛው አካሏ ሲሆን ቩልቫን እና የማህፀንን ጫፍ ወይም ማህፀንን የሚያገናኝ አካል ነው Uterus( ማህፀን )- በውስጡ እንደ cervix ፣ endometrium ፣ funds ፣ Fallopian tube ፣ ovary እናሌሎች ለተለያዩ ነገር የሚያገለግሉ አካላቶችን የያዘ የውስጠኛው የሴት አካል ሲሆን በዋናነት ለፅንስ ማደጊያ ፣ እንቁላል ማምረቻ (ovulation) ያገለግላል ከእነዚህ በተጨማሪም ለወንድ penis ( ቁላ ) ምንለው የሴት አካል አቻው clitoris( እምስ ) የምንለው ነው ማለትም ለወንድ ልጅ ቁላ ለሴት ደግሞ እምስ በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ስሜትን ለመቀስቀስ በዋናነትእጅጉን ጠቃሚ ሚባሉ ናቸው ። ( በአማርኛ ስማቸው ቢያስጠላም ቻሉት ) ህዳር 2018 ከነዚህ አካላት በተጨማሪም based on physiology ፦ ክሮሞሶም xx ከሆነ ሴቶች እና XY ከሆነ ደግሞ ለወንዶች ሆርሞኖች በዋናነት ከፍተኛ መጠን ኢስትሮጂን ለሴቶች እና ቴስቴስትሮን ለወንዶች ለመራባት እና ፅንስን ለመፍጠር እንቁላል ለሴቶች እና ስፐርም ለወንዶች አላቸው ከላይ የጠቀስኳቸው ላይ ተመስርተን በተለምዶ ወንድ , ሴት , ወይም ሁለቱም ( አንድ ሰው በሁለቱም ጾታዎች ወይም አሻሚ ብልቶች በባዮሎጂያዊ ባህሪዎች ሲወለድ ) ፆታ ያላቸው ብለን እንከፍላለን። እንዲሁም ወንዶች ከሴቶች ይበልጥ የረዘመ Urethra( ከሽንት ማጠራቀሚያ /bladder ወደ ውጫዊው መሽኛ /ureter ሽንትን የሚያስተላልፍ ትቦ ) አላቸው ይኸውም ወንዶች ቆመውእንዲሸኑ ያስችላቸዋል ይሄንንም እርዝማኔ ስንመለከት ሴትልጅ ከ 3-4cm እና ወንድልጅ ከ 17-22cm ይረዝማል በዚህም ምክንያት ሴትልጅ ይበልጥ ለሽንት መሽኛኢንፌክሽን (Urinary tract infection) ተጋላጭ ነች ፤በተጨማሪም ይህ Urethra ቱቦ ለወንዶች በግብረ ስጋግንኙነት ወቅት ከዘርጋር የተቀላቀለ ፈሳሽ (Semen) በመያዝ በቁላ በኩል እንዲረጭ ያደርጋል። ምዕራፍ ሁለት - Gender( ስርአተ ጾታ ) ህዳር 2018 ለ sex እና gender በአማርኛ የሚስማማ የተለያየ ስያሜ ማግኘት ከባድ ቢሆንም ከትርጓሜያቸው ልዩነታቸውን በደንብ እንደምትረዱት ተስፋ አለኝ Gender የሚያመለክተው ፦ ማህበራዊ እና ባህላዊ ፣ ባህሪያትን እና ሚናዎችን ላይ ተመስርተን ወንድ ፣ ሴት ወይም ሌሎችን (eg, non- binary) መሆንን ያመላክታል፤ የ Gender መገለጫዎች እንደ አከባቢያችን ባህል እና ወግ ቢለያይም አብዛኛው ተቀራራቢ ነው ። ለምሳሌ አረማመድ ፣ ስራ ክፍፍል ፣ ባህሪ ፣ አለባበስ ፣ ጭፈራ እና ወዘተ ... ላይ እንመሰረታለን። አብዛኛው ማህበረሰብ ውስጥ ይሄ አለባበስ ፣ አረማመድ ፣ አጨፋፈር እና ሌሎች ተግባራቶች የሴት / የወንድ ነው ብሎ ሲከፋፍለው gender እንላለን። Gender ን በሁለት መልኩ ሊገለፅ ይችላል : እነሱም ውስጣዊ (gender identity) ወይምውጫዊ (gender expression) ናቸው። የሥርዓተ - ፆታ ማንነት (Gender identity) ህዳር 2018 ማን ነሽ / ህ (Who are you) እና (How you feel inside) የሚል ጥያቄ ያቀርብልናል የሥርዓተ - ፆታ ማንነት (Gender identity) ውስጣዊ ማንነታችን ሲሆን በጥልቀት ወንድ፣ ሴት ፣ ሁለቱንም መሆንን ወይም አለመሆንን ስሜት የያዘ ነው። ሰውነታችን ምንም ይሁን ምን ( አካላችን የሴትም ይሁን የወንድ ) ከፈለጉት ፆታ ቢመድቡን የእኛ ውስጥ ግን የፈለገውን ነው። አንዳንዴ እንደ ሴት ለብሰን ውስጣችን ግን ወንድነትን ሊፈልግ ይችላል ወይም እንደ ወንድ ለብሰን ውስጣችን ሴትነትን ሊፈልግ ይችላል ስለዚህ gender identity ለሰዎች የምናሳየው ሳይሆን እኛ በውስጣችን የሚሰማን እና መሆን የምንፈልገው ስርአተ ፆታ ነው። ከነዚህም gender identity ውስጥ ጥቂቶቹን እንመልከት ፦ ሀ . Transgender አካላቸው ሴት ሆኖ ውስጣዊ ፍላጎታቸው እና ማንነታቸው ወንድ ሲሆን ወይም አካላቸው የወንድ ሆኖ ውስጣዊ ፍላጎታቸው እና ማንነታቸው የሴት ሲሆን ነው። ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው ሲወለድ የወንድ አካላትን ይዞ ነው ነገር ግን ውስጣዊ ማንነቱ የሚፈልገው እንደ ወንድ መልበስ ፣ መራመድ ወይ የወንድ ተግባራትን ማድረግ ሳይሆን ሴት መሆንን ይፈልጋል ህዳር 2018 ለ Cisgender አካላቸው እና ውስጣዊ ማንነታቸውን የሚገልፁበት ሁኔታ አንድ ሲሆን ማለትም የሴት አካል ያላት ሴት እራሷን ማህበረሰቡ ባስቀመጠው የሴትነት መስፈርት ስትገልፅ እና ሴት መሆን ስትፈልግ ወንድም እንደዛው :: ይሄማለት አካላዊ ማንታቸው እና ውስጣዊ ራሳቸውን የሚያዩበት መንገድ አንድ ሆኖ ሲገኝ ማለት ነው። ሐ . Nonbinary አካላቸው የወንድም ይሁን የሴት ... ውስጣዊ ማንታቸው በአንዱ ፆታ ብቻ የሚገደብ ሳይሆን በሁለቱም ጄንደር ፅንፎች ማንነታቸውን ሊያዩት የሚችሉ ወይም ከናካቴው ራሳቸውን በወንድም በሴትም ጄንደር ላይመድቡት የሚችሉ ሰዎች ናቸው።ነን - ባይነሪ ከሁለትዮሽ ፆታ መደብ ውጪ የሚመደቡትን በሙሉ አቅፎ የሚይዝ ቃል ሲሆን Agender, Bigender, Gender Fluid የተባሉትም በስሩ ሊካተቱ የሚችሉ ናቸው። ልብ ልንል የሚገባው የሰዎችን ጣዕመን (experience) ለመግለፅ የምንጠቀማቸው ቃላት እንጂ ሙሉ ለሙሉ የሰዎችን ጣዕመን ገልፀው የሚደመድሙ ቃላቶች አይደሉም ! ኩዊርነትን ለመግለፅ ይረዱን የነበሩ አውንታዊ ቃላቶች ስላልነበሩ በየዘመኑ አዳዲስ ቃላትን የመፍጠር ተግባር አንድ የኩዊር የትግል መለያችን ነው። መ . Gender fluid እነዚኛዎቹ ደግሞ አካላዊ ፆታቸው ምንም ቢሆን እራሳቸውን የሚሆኑበት መንገድ እንደ ውሃ ተቀያያሪ ነው ፣ አንዳንዴ ወንድ አንዳንዴ ደግሞ ሴት መሆንን ይፈልጋሉ ፤ ሁለቱንም ፆታ የመሆን ፍላጎታቸው ካሉበት ሁኔታ ፣ ሰዓት አንፃር ይቀያየራል ህዳር 2018 ሠ Agender ከስርዓተ ፆታ ውጭ ማለት ነው ፣ እራሳቸውን ሴት ወይም ወንድ ነኝ አይሉም በቃ gender neutral ናቸው ረ Bigender ከ gender fluid ጋር ተቀራራቢ ሲሆኑ ከነዛ ሚለያቸው ነገር እነዚኛዎቹ ሁለቱንም በአንዴ መሆንን ሊፈልጉ ይችላሉ፤ እዚህ ጋር ተቀራራቢ ስለሆኑት gender fluid እና Bigender ምሳሌ ላስቀምጥላቹ Gender fluid ፦አቢጌል አካላዊ ፆታዋ ሴት ቢሆንም በዚኛው ሳምንት ውስጧ ወንድ መሆንን ፈልጓል " አንተ " ተብሎ መጠራትን ፈልጋለች ፤ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ ሴት መሆንን " አንቺ " ተብሎ መጠራትን ትፈልጋለች ፤ በሌላ ቀን ደግሞ አቢጌል ሁለቱንም ፆታ መሆንን ላትፈልግ ትችላለች " አንተንም አንቺንም " አትፈልግም Bigender ፦ አቢጌል በተመሳሳይ ሰዓት ሁለቱንም መሆን ነው ምትፈልገው ፤ ውስጧ ወንድነትንም ሴትነትንም ይፈልጋል ፤ ምን አልባት ውስጧ አንዳንዴ ሴትነቷን ወይም ወንድነቷን አብልጦ ሊፈልግ ይችላል ነገር ግን ሁለቱም አሉ አንዱን ጥላ እና ለይታ መሆንን አትችልም ፣ ስርአተ ፆታዋ ሁለቱንም በአንዴ የያዘ እና ቋሚ ነው ስርዓተ - ፆታ አገላለፅ (Gender Expression) ህዳር 2018 እንዴት ስርአተፆታችሁን ለሰዎች ታሳያላቹ (How You Show It outside) ስርዓተ ፆታአገላለፅ (gender expression) - ሰዎችስርዓተ ፆታቸውን ለአከባቢያቸው የሚያሳዩበት ወይ የሚገልፁበት መንገድ ነው ይኸውም በአለባበስ ፣ በድምፅ ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ (body language) ወይም በሌላነገሮች ማህበረሰባቸው ይሄ የወንድ ወይም የሴት መገለጫ ነው ብሎ ባስቀመጠላቸው እራሳቸውን ለማህበረሰብ ያሳያሉ። ምክንያቱም ጄንደር ማህበረሰቡ በፈጠረው ክፍፍል መካከል የተወጠረ ከመሆኑ የተነሳ ወንድ ነህ ተብሎ ከተሰመረው ማዕቀብ የተለየ በሴትነት ጄንደር ውስጥ ያለውን መደብ ሆነነው ልንገኝ እንችላለን። ከሆነው የተለየ ሆነን ሳይሆን ማህበረሰቡ ባሰመረው መስመር ለመጥለቅ በምናደርገው ፍትጊያ የሚፈጠር ውስጣዊ አውድ ሊኖረው ስለሚችል ነው። ለምሳሌ ቀሚስ መልበስ ያለባት ሴት ናት የሚል የአለባበስ ክፍፍል አለ ነገር ግን አንድ ወንድ ይሃን አለባበስ በመልበስ ራሱን መግለፅ ሊፈልግ ይችላል ይሄ ማለት ወንድ አይደለም ማለት እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባል ራስን መግለፅ እንጂ ይሄ አገላለፃቸውምውስጣቸው የፈለገው ወይም ማህበረሰቡ እንዲ ሁኑ ስላላቸው ሊሆንም ይችላል ፤ ማለትም አንዳንዶች አካላቸው ሴት ሆኖ ማህበረሰቡ እንደ ሴት act እንዲያደርጉ ሲጠብቅእነሱ ግን እራሳቸውን እንደ ማህበረሰባቸው የሴትነት ወይም የወንድነት መስፈርት ይገልፃሉ ። ህዳር 2018 Gender expression ፦ ውጫዊ አገላለፅ እንደመሆኑ ከባህል ባህል ይለያያል ግላዊምነው (personal) እንዲህም ስንል ውስጣችን የፈለገውን (gender identity) በፈለግነው መንገድ ለማህበረሰቡ እናሳያለን ተለዋዋጭ ነው ለምሳሌ አቢጌል ዛሬ እንደ ሴት በመልበስ ፣ በመራመድ እራሷን ለማህበረሰቡ ማሳየት ልትፈልግ ትችላለች ፤ በሌላ ቀን ደግሞ እንደ ወንድ እራሷን ልታሳይ ትችላለች Note - Gender identity ውስጣችን የፈለገውስርአተ ፆታ ነው Gender expression ግን እኛ ለማህበረሰቡ ወይም ለሰዎች ማሳየት የምንፈልገው ነው። Gender identity እና expression ን ስቋጨውእና ወሳኝ ነጥቦችን ሳነሳ፦ Gender identity ሰዎች አካላዊ ፆታቸው (sex) ምንም ቢሆን እራሳቸውን እንደ ሴት ወይም ወንድ የተቀበሉበት መንገድ ነው ፤ Gender expression ግን ሰዎች ጄንደራቸውን ለአለም የሚገልፅቡት መንገድ ነው ይኸውም ከውስጣዊ ጄንደራቸው ጋር ላይመሳሰል ይችላል ማለትም በማህበረሰብ ጫና እንደፈለጉት እራሳቸውን ላይገልፁ ይችላሉ። ህዳር 2018 Gender identity ሊቀያየር የማይችል ውስጣዊ ፍላጎታችን ነው ፤ አንድ ሰው cisgender, transgender, fluid gender, nonbinary ወይምሌላ ከሆነ ሁሌም እንደዛው ነው ሊቀይረው አይችልም gender expression ግን በቀላሉ ባህል ላይ ወይም የኛ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ሊቀያየር የሚችል ነው ምዕራፍ ሶስት - ሽግግረ - ፆታ (Transgender) ህዳር 2018 ሽግግረ - ፆታ ቀጥተኛ የአማርኛ ፍቺ ስንወስደው ነው ኢንግሊዘኛውን ይህ ግን ምርጫ እንዳለበት ሊገልፅ የሚችል እንዳልሆነ ማስገንዘብ እፈልጋለሁ። ምን ያህል ቋንቋችን በቀጥት (hetero-normative) የተለወሰ ከመሆኑ የተነሳ ለኢትዮጵያውያን ኩዊር ግለሰቦች ቃላትን መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ ማከል እሻለሁ። ስለዚህ አንባቢያን ሽግግረ - ፆታ ስል ከቃላት እጦት አንፃር እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል ምክንያቱም ቃሉ ትክክለኛውን የትራንስ ሰዎችን ጣዕመን የሚወክል ስላልሆነ። እነኚ ሰዎች በተወለዱበት ወቅት ያላቸው ፆታዊ አካላቸው የእነሱን ውስጣዊ የፆታ ፍላጎት ሳይገልፀው ሲቀር ወይም አካላቸው እና gender identity ሳይመሳሰል ሲቀርነው። ይኽም ሲወለዱ ሴት ወይም ወንድ ናቸው ብሎ ሚያሳይ አካል ቢኖራቸውም ውስጣቸው እና ማንነታቸው ያንን ፆታ ሳይቀበለው ሲቀር እና በተቃራኒ መሆንን ሲፈልጉ ነው። እኚም ሰዎች Transwoman ወይም transman ሊሆኑ ይችላሉ፦ Tran’s woman - ሲወለዱ አካላቸው የወንድ ነው ነገር ግን ውስጣዊ ጄንደር ማንነታቸው የሴት ነው እንደሴት መኖርን የሚፈልጉ ናቸው። ህዳር 2018 ለምሳሌ፦ ዳንኤል ስትወለድ ወንድ ነበረች ነገር ግን ከልጅነቷ ጀምሮ ሴት እንደሆነች ይሰማታል እናም ሴት መሆንን ትፈልጋለች ስለዚህ ስታድግ ስሟን ዳንኤላ ብላ ቀይራው እንደ ሴት እየለበሰች እና ሴት ምታደርገውን እያደረገች አንቺ ተብላ ተጠርታ ትኖራለች እንዲሁም " አባ " ተብላ ሳይሆን " እማ " ተብላመጠራትን ትፈልጋለች። Tran’s man- ሲወለዱ አካላቸው የሴት ነው ነገር ግን ወንድ መሆንን የሚፈልጉ እና እንደ ወንድ መኖርን የሚፈልጉ ናቸው። ለምሳሌ፦ ሳምራዊት ሲወለድ የሴት አካል ይዞ ነው ነገር ግን ከልጅነቱ ጀምሮ ወንድ መሆንን እና " አንተ / ሳሚ " ተብሎ መጠራትን ይፈልጋል እንዲሁም እንደ ወንድ አባት ሆኖ " አባ " መባልንእንጂ እንደ ሴት ኖሮ " እማ " መባልንአይፈልግም። Note- Transman ወይም Transwoman አካላዊፆታቸውን ወይም መጠሪያ ስማቸውን መቀየር እንደነሱ ፍላጎት ይወሰናል እንጂ ሁሉም ትራንስ ሰዎች ለውጥ ያደርጋሉ ማለት አይደለም ፤ ትራንስ የሆኑት በአካላቸው ሳይሆን ሊቀይሩት በማይችሉት በማንነታቸው እና ውስጣዊ ፍላጎታቸው ነው። ይሁን እንጂ አንዳንድ እራሳቸውን እንደማንነታቸው የመግለፅ ድፍረቱ ፣ ፍላጎቱ እና አቅሙ ያላቸው ሰዎች ከማህበረሰብ (social adaptation) ፣ ከመንግስት (legal transition) እና ከአካላቸው አንፃር (medical and surgical transition) ስርአተ ፆታቸውንም (gender) ሆነ ፆታቸው (sex) ሊቀይሩ ይችላሉ። ህዳር 2018 ማህበረሰባዊ ለውጥ (Social transition) Trans የሆኑ ሰዎች በሚፈልጉት ፆታ እራሳቸውን በመግለፅ እና በማሳየት ማህበረሰባቸውን ማላመድ ሲጀምሩ ነው ፤ ይኸውም አረማመዳቸውን ፣ አለባበሳቸውን ፣ አነጋገራቸውን ፣ የሚጠሩበትን ስም ፣ ተውላጠ ስም ( አንተ / አንቺ ) እና ሌሎች የእነሱን ውስጣዊ ማንነት በሚገልፁ ነገራቶች እራሳቸውን ማሳየት ነው። ህጋዊ ለውጦች (Legal transition) የመታወቂያ ስማቸውን፣ ፆታቸውን፣ የውልደት ሰርተፊኬት እና ሌሎች በመንግስት ደረጃ ህጋዊ ለመሆን የሚያስፈልጋቸውን ወረቀቶች ሲቀይሩ ነው እንዲሁም Transwoman የሆኑ ሰዎች አንተ ተብሎ መጠራት ቀርቶ እንደ ሴት አንቺ ተብለው ይጠራሉ Transman ሰዎቸም እንደ ወንድ አንተ ተብለው ይጠራሉ ። አካላዊለውጥ (Anatomy and physiology transition) ትራንስ ጄንደር ለሆኑ ሰዎች ውስጣቸው የሚሰማቸውን ትክክለኛ የፆታ ማንነታቸውን እና ውጫዊ አካላቸውን ለማመሳሰል እና ምቾት ተሰምቷቸው ማህበረሰቡ እንዲቀባለቸው ለማድረግ የሚሰራ የለውጥ ሂደት ነው። ይሄም ለውጥ በሁለት አይነት መንገድ የሚገኝ ሲሆን እነሱም በመድሀኒት (medical/hormonal therapy) እናበቀዶ ጥገና (surgical transition) ናቸው። ህዳር 2018 አስተውሉ አካላዊ ለውጥን ጨምሮ ሁሉንም ለውጥ ማድረግ የትራንስ ሰዎችፍላጎት ነው ፣ሁሉም እኚን ለውጦች ላይፈልጉ ይችላሉ ፣በተለይ በብዙ ሰዎች ዘንድ ያስተዋልኩት ትራንስ የሆኑ ሰዎች በሙሉ አካላዊ ለውጥ ያደረጉ ናቸው የሚልነው ነገር ግን እውነታው እንደዛ አይደለም ፤ትራንስ ሰዎች በ medical/surgical መንገድ አካላዊ ለውጥ ማድረግ ሳይሆን ሲፈጠሩም ያላቸው ፆታእና አካላዊ ፆታቸው ያልተጣጣሙ ሰዎች ናቸው ለዚህም አንዳንድ ትራንስ የሆኑ ሰዎች ይሄን ለውጥ በራሳቸው ፍላጎት አድርገውት ውስጣዊ / ትክክለኛ ፆታቸውን ከውጫዊው አካላቸው ጋርየሚያመሳስሉት። ሀ መድሃኒት (Medical transition) ለትራንስ ሰዎች በኪንን ወይም በመርፌ መልክ በሚሰጥ መድሀኒት አካላትን መቀየር ነው። ለ Transwoman ( ከወንድ - ሴት ) የሴት አካላት እንዲኖራቸው ማለትም ጡትን ለማሳደግ ፣ ቆዳን ለማለስለስ ፣ ድምፅን ለማቅጠን ፣ ፀጉርን ለመቀነስ ሴቶች የሚያመርቱትን Estrogen እና Anti androgen ሆርሞንን ሲወስዱ ነው። ለ Transman ( ከሴት - ወንድ ) የወንድ አካላት እንዲኖራቸው ማለትም ጎርነን ያለ ድምፅ ፣ በፊታቸው እና ደረታቸው ላይ ፀጉር እንዲያበቅል ፣ ጡንቻ እና ደረታቸው እንዲሰፋ Testosterone የተባለ ወንዶች የሚያመርቱትን ሆርሞን በመድሀኒት መልክ ይወስዳሉ። ህዳር 2018 ለ ቀዶ ጥገና ለውጥ (Surgical transition) ቀዶ ጥገና በማደንዘዣ (Under anesthesia) የሚሰራ ሲሆን የተለያዩ ሰርጅን ሀኪሞችን ያካትታል እንዲሁም ከላይ (Top) እና ከታች (bottom) surgery ተብሎ ይከፈላል። 1. Top surgery የትራንስ ሰዎችን ፍላጎት በመንተራስ ከወገብ በላይ ሚሰራ ቀዶጥገና ሲሆንለትራንስ ሴትም ሆነለትራንስ ወንድ የሚደረግ ቀዶ ጥገና ነው። ለ Transwoman ለእነዚ ሴቶችከሆርሞኑ በተጨማሪ ጡታቸውን በደንብ ማሳደግ ከፈለጉ በ Breast augmentation ፕሮሰስ Silcon በተባለለስላሳ እና ከ silcon, oxygen, carbon እና ከ hydrogen በጥሩ ሁኔታየተገነባ ሰው ሰራሽ ጡት ከደረታቸው ጡንቻ (chest muscle) ወይም ከጡታቸውህዋስ ስር በጥንቃቄ በማስገባት ነው ። ይኽም Silcon በጄል፣ በፕላስቲክ ወይም በፈሳሽ መልክ ሊሰራ ይችላል። ይሄንን Silcon ተለዋዋጭ ፣ምቹ ፣ ፅኑ ፣ ከሌላው አካላት ጋር በመነካካት ችግር የማይፈጥር በመሆኑ እንዲሁም ሙቀትን እና ባክቴሪያን የሚከላከል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል። Silicon የማይገኝ ወይም ሰዎቹ የማይፈልጉ ከሆነ ደግሞ ከጡታቸው ህዋሳት ጋር ሚመሳሰል ስጋ ወይም Tissue ከሌላ አካላቸው ላይ በመቁረት ከጡታቸው ጋር በማገናኘት ንቅለ - ተከላ (implantation) ይካሄዳል